2014-01-10 16:09:48

ብፁዕ ካርዲናል ደ ፓውሊስ፦ ስቓያችሁ አንጽቷችኋል አዲስ ልብ ይኑራችሁ



RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 8 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በለጀናሪዮም ክሪስቲ ልዩ የበላይ ተጠሪ በመሆን ማህበሩ ወደ መንጻትና ሕዳሴ በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ውሳኔ መሠረት ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሲመሩ የቆዩት ብፁዕ ካርዲናል ደ ፓውሊስ፦ ማኅበሩ ጠቅላይ አለቃና የማኅበሩ የሐዋርያዊ አመራር መማከርት ምርጫ ብሎም አዲስ የማኅበሩ ደንብ አርቆ እንዲያጸድቅ የተጠራው ጠቅላይ ጉባኤ ለማስጀመር በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ “ስቃያችሁ አንጽቷችዋል ልባችሁ በማደስ በስላችሁ መጪውን ዓለም በእማኔና በተረጋጋ መንፈስ ተመልከቱ” እንዳሉ የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።
“በሚገባና በደንብ የሚጸድቅ መመሪያ አስፈላጊ ነው፣ ሆኖም አዲስ መንፈስ ከሌለ ደንብ ወይንም ሕግ ለብቻው በቂ አይሆንም” በማለት ማኅበሩ የተያያዘው የኅዳሴ ጎዳና ካለ መታከት እንዲቀጥልበት አደራ ማለታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ፦ “በቤተ ክርስቲያንም ይሁን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በቀረበባችሁ ወቀሳና ክስ በጎሪጥ መበታየታችሁ ምክንያት በተሰማችሁ ኃፍረት ተሰቃይታችኋላ፣ ይኸንን ሁሉ ለጥሪያችሁና ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ለማኅበራችሁ ባላችሁ ፍቅር በፍቅር ተቀብላችሁ በመሳቃየት ሁሉን ችላችሁ በጌታ ፈቃድ የመንጻትና የኅዳሴ ጸጋ ተቀብላችኋል፣ ይኽ ስቃይ አንጽቷችዋል፣ በሳል አድርጓችኋል የጌታ ፍቅርና ጸጋውን እንድትኖሩ ምክንያት ሆኖላችኋል በመስቀልና በስቃይ ሥር በሚያልፈው በመዳን እቅድ ተሳታፊ እንድትሆኑ አድርጓችዋል” የሚል ጠንካራ ቃልና ሃሳብ የሰፈረበት የብፁዕ ካርዲናል ደ ፓውሊስ ማኅበሩ የስቃዩን ሁነት ጸጋ ይሆናችሁ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን በጸሎቷ እንደምትደግፋቸው በመመስከር፣ “ወንጌል የሚገልጠው የመዳን እቅድ፣ ከክፋት መንፈስ ገዛ እራሱን የሚያሸሽ ወይንም የማይጋፈጥ ሌሎችን በማውገዝ የሚከወን ሳይሆን የሌላውን ኃጢኣት በፍቅር የገዛ እራስ በማድረግ በውስጡ እንዲነጻ የስቃይ ተካፋይ በመሆን ነው” ብለው ይኽ የሚካሄደው የማኅበሩ ጠቅላይ ጉባኤ የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ የሚመርጥ አዲስ የማኅበሩ ደንብ የሚያጸድቅ መሆኑ በማብራራትም፦ “አዲስ ደንብ የሕግ አንቅጽ የተደረደረበት ሳይሆን የማኅበሩ የጋራ ጥሪ የአንድ መንፈሳዊነት የተልእኮ ውህደትና የጋራ ቅድስና መግለጫ ነው። ስለዚህ የደንቡ አንኳር የማኅበሩ መንፈሳዊ መርሆ ዓላማና መንፈሳዊ ሃብት የሚል ነው። የማኅበሩ መንፈሳዊ መርሆ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በጊዜው በሰጡት መርህ ቃል መሠረት መጤንና መኖር አለበት። ያልታደሰ መንፈስ ከሌለ ደንብ ለብቻው በቂ አይሆንም” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ በማያያዝ የብፁዕነታቸው ምዕዳን የታደሰ መንፈስ ላይ ያነጣጠረ መሆኑም ገልጠው፣ የማኅበሩ አባላት ማኅበሩን ሊመሩ በሚመረጡት በመራጮችና በማኅበሩ አባላታ ዘንድ አዲስ መንፈስ እንጂ ምቀኝነት የብቀላ ስሜት የሌለበት ከዚህ ሁሉ አሉታዊ ዝንባሌ በጠቅላላ አይንና ልብን ከሚያሳውረው የስቃይ ምክንያት ሊሆን ከሚችለው ተከስቶ ከነበረው ግድፈት ከሚመነጭ ተዘክሮ ነጻ መውጣት ወሳኝ መሆኑ እንዳስገነዘቡ አስታውቀዋል።
“እናንተ ስቃይ ካልተለየው የፈጸማችሁት ረዥም የኅዳሴና የመንጻት ጉዞ ዛሬ በተረጋጋና በእምኝነት መንፈስ ለጠቅላይ ጉባኤ ደርሳችኋል፣ እዚህ ላደረሰው እግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል፣ ይኸንን የመረጋጋትና የእማኝነት መንፈስ በእናንተ ውስጥ ያኖረው ጌታ፣ እርሱ ነው የመራችሁ፣ በዚህ አዲስ ጉዞ ከእናተንተ ጋር ነው አብሯችሁ እየደገፋችሁም ይጓዛል፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ማኅበሩ አጋጥሞት በነበረው ከባድ ችግርና ስቃይ ተውጦ እንዳይቀር በመታመን በኅዳሴና በጌታ ታማኝነት ላይ በጸና እምነት ተገፋፍተው ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ላይ ያላት እምነት በመመስከር ለመንጻትና ለኅዳሴ ያነቃቁ ናቸው፣ አሁን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቅርባችሁ ናቸው፣ ዛሬ ለዚህ ላበቃን እግዚአብሔር በማመስገን ደስ ሊለን ይገባል፣ በዚህ ቅዳሴ ሕይወታችሁን ለማደስ ለክርስቶስ መሥዋዕት ለማቅረብ ዝግጁ ናችሁ” በማለት ያሰሙት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.