2014-01-08 15:34:37

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ፦ ሁላችን ለአስፍሆተ ወንጌልና ከዓለም ጋር ለመወያየት የተጠራን ነን


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በብራዚል በዡዋዘሮ ዶ ኖርተ ከተማ “ፍትሕና ነቢይነት ለሕይወት አገልግሎት” በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ላለው 13ኛው ብሔራዊ መሠረተ ማኅበረ ክርስቲያን ጉባኤ “አስፍሆተ ወንጌል የመላይቱ ቤተ ክርስቲያንና የመላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ተቀዳሚ ግዴታ ነው” በሚል ቀዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዚህ እ.ኤ.አ. ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚጠናቀቀው ጉባኤ ባስተላለፉት መልእክት፣ ሁላችን በጥጋ ጥግና ውጫዊ የከተማ ክልሎች የወንጌል ሃሴት ለእናንዳንዱ ዜጋ የምናደርስ ነጋድያን መሆን እንደሚገባ በማሳስብ፣ ተጋባእያኑና ጉባኤው ለቅድስት ድንግል ማርያም ዘአፓረሲዳ አወክፈው፣ የዚህ የመሠረተ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ሚና የቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊ ልኡክነት የሚል መሆኑ ገልጠው፣ ወንጌላዊ ሃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን ዋቢ በማድረግ የልኡከ ወንጌላዊነት በአዲስ መንፈስ የሚያነቃቁና ቤተ ክርስቲያን ከዓለም ጋር ለመወያየት ያላት ብቃት እንዲታደስ የሚያደርጉ እንዲሆኑም አደራ እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ አሁንም ሐዋርያዊው ምዕዳን በመጥቀስ፦ ይኽ የቤተ ክርስቲያን መሠረተ ማኅበረሰብ ሃብታም የሆነው የቁምስና ተጨባጭ ሥፍራ ጋር የሚኖራቸው ግኑኝነት ሳያቋርጡ የሚኖር መንፈሳዊነት በክልላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጋር በማዋሃድ መኖር ይጠበቅባቸዋል” ብለው በመጨረሻም ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በጻፈው መልእክቱ ዘንድ የተኖረው ሐዋርያዊ ምዕዳን እርሱም ወንጌልን ሳላበስር ብቀር ወዮልኝ” በሚለው ቃል ሥር ያስተላለፉት መልእክት በማጠቃለል ለሁሉም ሐዋርያዊ ቡራኬ ማስተላለፋቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.