2013-12-23 16:13:01

ኢራቅ፦ ብፁዕ አቡነ ሳኮ፣ በዓለ ልደት ጦርነትና አመጽ በተሞላበት መካከለኛው ምሥራቅ ብቸኛው እውነተኛ ተስፋ


RealAudioMP3 በኢራቅ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ ስቃይና መከራ የአገሪቱ ክርስቲያን ማኅበርሰብ የተጋረጠበት አቢይ መከራ በጠቅላላ የአገሪቱ ሕዝብ በሰላምና መረጋገት እጦት ተነክሮ ባለበት ወቅት ብቸኛው እውነተኛው ተስፋና አንድነት ወንድምማችነትና መከባበር መቀባበል እንዲኖር በኢራቅ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በባጋዳድ የከላዳዊ ሥርዓት ለሚከተለው ሰበካ ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ልዊስ ራፋኤል ሳኮ ምዕዳን በማቅረብ፣ የሚወለደው ሕፃን ለሁሉ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች የወንድማማችነትና የመቀራረብ ምልክት ይሆን ዘንድ መማጠናቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ሳኮ በበዓለ ልደት ምክንያት ለምእመናን በዓለ ልደት ሁሉም ድንበር አልቦ የሆነው የላቀው ከሃሌ ኵሉ ህላዌነት እውቅና የሚሰጥበት የሁሉም በዓል ሆኖ እንዲከበር ካህናትና ምእመናን የአገልግሎት በዓል መሆኑ ተገንዝበው ተስፋ ፍቅርና እምነት በማነቃቃት ወንድማማችነትና አንድነት በኢራቅ ይነገሥም ዘንድ በዚሁ መንፈስ እንዲያገለግሉ ጥሪ እንደሚያቀርቡ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ከወዲሁ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.