2013-12-23 16:10:26

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኢጣሊያ ያላት ባህላዊ ቅርስ ድርብ እድል ነው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታሕሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅድስት መንበር የረፓብሊካዊት ኢጣሊያ ልኡከ መንግሥትና ሠራተኞች የልኡከ መንግሥት የግኑኝነት ሥነ ሥርዓት ፈጻሚ አካል በጠቅላላ ሠራተኞችን በላቲን ሥርዓት የሚከበረው በዓለ ልደት ምክንያት ተቀብለው የመልካም በዓለ ልደት ምኞች መግለጫ አዘል ንግግር ማሰማታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶስቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት ንግግር የኢጣሊያ ልኡከ መንግሥትና ሠራተኞች ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊና ከኅየንተ ቤተ ጳጳስ ጋር ለሚያሳዩት የትብብር መንፈስ አመስግነው፦ “የሥነ ግኑኝነት ስልት ሠራተኞች ተልእኮ የመቀራረብ የመገናኘት ባህል ማመቻቸት ነው። ስለዚህ በተለያዩ አገሮች ልኡካን መካከል፣ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ልኡካን ጋር ፍርያማ ግኑኝነት እንዲኖር የምታገለግሉ ናችሁ፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ ያለባችሁ ኃላፊነት በቀላሉ የሚገመት አይደልም” እንዳሉ ጂሶቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን የእርስ በእርስ መከባበር ላይ የጸና መቀራረብ መተዋወቅ የጋራው ፍላጎት ለሆነው የልማት ጎዳናና ሰላም ላይ ያተኮረ አወንታዊ ግኑኝነት ማበበ እንደሚኖርበት ሲያሳስቡ፦ “ኢጣልያ ያላት ባህላዊ ቅርስ ለኢጣሊያ ድርብ ሃብት መሆኑና ለኢጣሊያ የሥነ ግኑኝነት ዘይቤ አቢይ ድጋፍ ነው። ኢጣልያ የሚል ቃል በመላ ዓለም ባህል ሥነ ጥበብና ሥልጣኔ ከሚለው ቃል በተምሳይ የሚገለጥም ነው። ስለዚህ ይኸንን ታላቅ ዕድል ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የፍቅር ስልጣኔ በማለት የገለጡት የጋራው ጥቅም ቅድሚያ አገልግሎት እንዲውልና በሥነ ግኑኝነት ዘርፍ አቢይ አስተዋጽዖ አለው። ከዚህ በመንደርደር ኢጣሊያ ያላት ባህል በቂና አቢይ ግምቲ ሊሰጠው ይገባል” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው በዓለ ልደት ዘእግዚእነ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የግኑኝነት በዓል፣ እርሱም በገዛ እራሱ መሆን ግኑኝነት እውን ያደረገው ሕፃን እንደተሰጠን የምናከብርበት ዕለት መሆኑ ሲያብራሩ፦ የጌታችን ኢየሱስ ልደት ክርስቲያን ላልሆነው ጭምር አቢይ ጥያቄ ነው፣ ሁላችን ይኸንን አቢይ የፍቅር ምሥጢር በጋለ ስሜትና መንፈስ እንድንኖረው አደራ፣ የአግልግሎታችን ሕይወትም ይሁን” ብለው ያሰሙት ሥልጣናዊ ምእዳን እንዳጠቃለሉ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.