2013-12-23 16:04:14

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማ ዘሕፃነ ኢየሱስ የሕፃናት ሕክምና ቤት
“ኢየሱስ ዘወትር ቅርባችሁ ነው፣ ከእናንተ ጋር ልዩ ውህደት አለው”


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ዘ ሕፃነ ኢየሱስ የሕፃናት ሕክምና ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው፣ እዛው ከሚገኙት ገና መድኃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቁትን ሕፃናት ጋር ተገናኝተው፦ “ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ልዩ ውህደት አለው፣ ዘወትር ቅርባችሁ ነው” በማለት እያንዳንዱን በሕክናው ቤት የሚገኙት ሕፃናትና ወላጆቻቸውን ሰላም በማለትና በመሳም እዛው በሕክምናው ቤት ሕሙማንና የሕክምና ባለ ሙያዎችና በጠቅላላ ከሕክምናው ቤት ሠራተኞች ጋር በመገናኘት የሁለት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ሐዋርያዊ ጉብኝት መፈጸማቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
ቅዱስነታቸው በዚህ በፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት በታመሙት ሕፃናት ልብና እንዲሁም በልጆቻቸው ከባድ ሕማም ምክንያት የስቃዩ ተካፋዮ በሆኑት ወላጆች ዘንድ ዳግም ተስፋ ፍቅርና እምነት በማነቃቃት የሚኖሩት ሕይወት በቅርብ ተካፋይ መሆናቸው በማረጋገጥ፦ ኢየሱስ ለእናንተ እጅግ ቅርብና ከእናንተ ጋር ውህደት አለው” ያሉት ቅዱስ አባታችን በእውነቱ ወንጌል በቃልና በሕይወት አብሳሪ እዛው በሕክምናው ቤት በሚገኘው ቤተ ጸሎት የጽሞና ጸሎት ፈጽመው እንዳበቁ፣ ሕክምና ቤቱን ባርከው፦ “ብርሃንንና ድኅንነትን የሚሰጠኝ እግዚኣብሔር ስለሆነ፣ ማንንም አልፈራም እግዚኣብሔር ከአደጋ ሁሉ ስለሚጠብቀኝ ከቶ አልደናገጥም (መዝ. 27)” ጠቅሰው ይኽ መዝሙር በእያንዳንዱ ታማሚው ሕፃን ከንፈር በሕይወት የሚደገም ቃል መሆኑና እዛው የተገኙት ልጆቻቸው በማይድን በሽታ ታመው በሕክና ቤቱ ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ሕፃናት ወላጆች ለቅዱስ አባታችን ሕጻናት እንደ መላእክት የሚል ምስክርነት አዘል የመልአክ ትንሽ ሐውልት ገጸ በርከት እንደተለገሰላቸውና የሕክምናው ቤቱ ዋና አስተዳዳሪ ጁዘፐ ፕሮፊቲ በሕክምናው ቤት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በካሪታስ የሚጠራው በሮማ ሰበካ ቅርንጫ ጋር በመተባበር በጠና የታመሙት ሕፃናትና ወላጆቻቸው የሚስተናገዱበት አንዲስ የተሠራው ሕንፃ በማስጎብኘት ባሰሙት ንግግር፦ “ይኽ አዲስ ሕንፃ ቅዱስ አባታችን ለበአለ ልደት ለእርስዎ የምንሰጠው ገጸ በረከት ነው፣ እንዲባርኩትና የቤቱ የአዱሱ ሕንፃ መጠሪያም ስምም “ቤተ ፍራንቸስኮ” የሚል ነው” እንዳሉም የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፒየትሮ ፓሮሊኒና እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ 1942 ዓ.ም. ሕክምናውን ቤት በመልካም አሳቢነትና ቸርነት በማሠራት ለቅድስት መንበር የለገሱት ቤተሰብ ማሪያ ግራዚያ ሳልቪያቲ ታጅበው ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት መሆኑ ደ ካርሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ስላደረጋችሁልኝ አቀባበልና እንዲሁም ስለ እኔ ለምታቀርቡት ጸሎት አመሰግናችዋለሁ። እያንዳንድችሁ ለእኔ ያቀረባችሁት የጸሎት ጥያቄ የተኖርበት ቅርጫት በመያዝ ሁላችን አብረን የሚያስፈልገንን በሙላት ቀድሞ ለሚያውቀው ጌታ ለማቅረብ በሆስፒታሉ በተተከለው በቅድስት ድንግል ማርያም ሐወልት ፊት ሆነን በእርሷ አማላጅነት ሰላም ላንቺ ይሁን በሚል ጸሎት እናቅረብ” ብለው ጸሎት ሰላም ለኪ መርተው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው ማጠናቀቃቸው ደ ካሮሊስ አመለከቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.