2013-12-20 16:07:38

ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል፦ አቢይ ተስፋ የተጣለበት የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ልኡክነት


RealAudioMP3 የመላ ሩሲያና ሞስኮ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል በሩሲያ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካሄዱትን ጳጳሳዊ የክርስቲያኖች ውህደት የሚያነቃቃው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. መኖሪያቸው የዳኒሎቭስክይ ገዳም ተቀብለው ማነጋገራቸው ሲገለጥ፣ በተካሄደው ግኑኝነት በካቶሊካዊትና በሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ መሪነት ሥር ብዙ ተስፋ የተጣለበትና በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው የጋራው አስተሳሰብ በበለጠ የሚያጎላ እደሚሆን ያላቸው እምነት እንደገለጡ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ካስራጨው ዜና ለማወቅ ተችለዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በሩሲያ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ማጠናቀቃቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው በሩሲያ ከምትገኘው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከመላ ሩሲያና ሞስካ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ የውጭ አቢያተ ክርስቲያን ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ሂላሪዮን ከሩሲያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ልኡካን አበይት አካላት ጋር የተገናኙ መሆናቸውም የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ በሁለቱ እህታማቾች አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነት በዚህ ታሪካዊ በሆነው በአሁኑ ወቅት ስለ ሰላም ስለ መካከለኛው ምስራቅ የክርስቲያኖች ስደትና መከራ እንዲገታ፣ ሰብአዊ ክብር የሕይወት ባህል ቤተሰብ የተሰኙትን ለማክበር በሁሉም ተከብሮና ተጠብቆ እንዲኖር ለማድረግ በጋራ የሚያካሂዱት የጋራ ጥረት ጠቅሰው በቅድስት መንበርና በመላ ሩሲያና ሞስካ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ መካከል ያለው ግኑኝነት በተለያየ የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የበላይ አካላት አማካኝነት የተከናወነና የሚከናወን መሆኑ እ.ኤ.አ. ህዳር ወር 2013 ዓ.ም. የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ አባላት ብፁዕ ካርዲናል ፖውል ፑፓርድ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮሎ ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ ጋር የተካሄደው ግኑኝነት ማስታወሳቸውም ያመለክታል።
ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ በበኩላቸውም ባሰሙት ንግግር ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በዚህ በአሁኑ ወቅት ለከፋ አደጋ ተጋልጦ የሚገኘው ቤተሰብ ምሥጢረ ተክሊል የሕይወት ባህል የመሳሰሉትን ክብሮችን ለመከላከል በጋራና በተናጥል በተለያየ መስክ ተሰማርተው የሚሰጡት አገልግሎትና ሕንጸት እንደጠቀሱ የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አያይዞ፣ ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ ከሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ምክትል አለክሰይ መሽኮቭ ጋር ተገናኝተው በፈደራላዊት ሩሲያና ቅድስት መንበር መካከል ያለው የጋራው ግኑኝነትና ትብብር ርእስ ሥር መወያየታቸው ጠቁመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.