2013-12-20 16:03:05

ብፁዕ አቡነ ትዋል፦ መካከለኛው ምስራቅ አለ ክርስቲያን መሆን የለበትም


RealAudioMP3 በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉኣድ ትዋል ሁሌ በየዓመት በበዓለ ልደት ምክንያት የሚያስተላልፉት መልእክት መሠረት፣ ይኸው ዘንድሮ ሊከበር በመቃረብ ላይ ያለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓል የዓለም ሁሉ ዓይኖች ወደዚያ የትስብእት ምሥጢር ክዋኔው የተረጋገጠበት ቤተ ልሔም እንዲተኩር የሚያደርግ ነው የሚል ሃሳብ ማእከል ያደረገ መልእክት ማስተላለፋቸው በእየሩሳሌም የፍራንቸስካውያን የመገናኛ ብዙኃን ማእከል ጋዜጠኛ አናሊዛ ኮንሶሎ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ብፁዕ አቡነ ትዋል በዚህ ባስተላለፉት መልእክት በሶሪያና በጋዛ ያለው አሳሳቢው ሁኔታ ላይ በማተኮር፣ በሶሪያ አለ ምንም ቅድመ ሁነት የቶክስ አቁም ስምምነት እንዲረጋገጥ ጥሪ በማቅረብ፣ ማናኛውም ዓይነት አመጽ ከምን ይሁኑ ከየትም ሊወገዝ ይገባዋል፣ የፖለቲካ አካላትም እልባት ያጣው አሰቃቂው ውጥረት እንዲገታ እውነተኛ መፍትሔ ለማፈላለግ እውነተኛ ጥረት ያደረጉ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው አናሊዛ ኮንሶሎ ገልጠዋል።
ብፁዕ አቡነ ትዋል ባስተላለፉት መልእክት በቅድስት መንበርና በእስራኤል መካከል የተረጋገጡት ስምምነቶች ይኽም በእስራኤል የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በእስራኤል ከግብር ክፍያ ነጻ ትሁን የሚል ስምምነት አንዱ እንደ ምክንያት ጠቅሰው፣ በፊሊፒንስ ያጋጠመው የተፈጥሮ አደጋ፣ እንዲሁም የእምነት ዓመት ፍጻሜ ጠቅሰው ቅድሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በሮማ በተካሄደው የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ምክንያት ከሁሉም ተጋባእያን ብፁዓን ጳጳሳት ጋር በመገናኘት የሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳንም ዘክረው መካከለኛው ምስራቅ አለ የክርስትናው መንፈሳዊነት ሆና እንዳትቀር መካከለኛው ምስራቅ አለ ማኅበረ ክርስቲያን እንዳይቀር የሁሉም ኃላፊነትና ጥረት የሚጠይቅ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ያሰመሩበት ሃሳብ ጠቅሰው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2014 ዓ.ም. በቅድስት መሬት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያከናውናሉ የቢባለው እቅድ በእውነቱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅድስት መሬትን ይጎበኙ ዘንድ የመላ መካከለኛው ምስራቅ ፍላጎት መሆኑ አብራርተው፣ ሁሉም በጸሎት እንዲሸኛቸውም አደራ ብለው፣ መልእክቱን ክርስትያን አይሁድና ሙስሊም በሚኖርት መንፈሳዊነትና ሃይማኖት የጋራ አካፋይ የሆነው ክብር ለይተው ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ለማረጋገጥ እንዲተጉና፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰላም ለሁሉ ሰዎች ያስጥ የሚል ጸሎት ማሳረጋቸው አናሊዛ ኮንሶሎ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.