2013-12-18 16:05:29

ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ ለሐዋራዊ ጉብኝት በሩሲያ
በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል አቢይ ትብብር አለ


RealAudioMP3 የክርስቲያኖች ውህደት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኾ በሩሲያ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ብፁዕነታቸው ትላትና በመላ ሩሲያና ሞስካ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ የውጭ አቢያተ ክርስቲያናት ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ሜትሮፖሊታ ሂላሪዮን ጋር መገናኘታቸው ገልጦ፣ ዛሬ በሞስካ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል ከመላ ሩሲያና ሞስካ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር መገናኘታቸው አስታወቀ።
የዛሬ አንድ ወር በፊት እ.ኤ.አ. ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ሜትሮፖሊታ ሂላሪዮን እዚህ በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ ጋር በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ መገናኘታቸው ብፁዕ ካርዲናል ኩኽ አስታውሰው ከመላ ሩሲያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ጋር እንደሚገናኙ ከቫቲካን ረዲዮ የፖሊሽ ቋንቋ ስርጭት ክፍል ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።
የሚያካሂዱት ጉብኝት በተለይ ደግሞ ከፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል ጋር የሚፈጽሙት የጋራው ውይይት በሁለቱ ማለትም በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነት የሚያጎለብት ለጋራ ጥቅም ያለመው የጋራው ግኑኝነት ፍሪያማነቱ ከፍ የሚያደረግ እንደሚሆን ያላቸው ተስፋ ገልጠው የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ግኑኝነት ብዙ እድገት ማሳየቱንም አረጋግጠዋል።
ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን መንበረ ጥበብና እንዲሁም በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የመሠረተ እምነት ቲዮሎጊያና የሥነ ወንጌላዊ ተልእኮ መምህር አባ ጀርማኖ ማራኒ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ እ.ኤ.አ. ይኽ 2013 ዓ.ም. በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና በሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግኑኝነት አቢይ እድገት የታየበት ዓመት መሆኑ ጠቅሰው፣ በሩሲያ የመገናኛ ብዙኃን ስለ ኵላዊት ቤተ ክስርቲያን በአወንታዊ መንፈስ የሚሰጡት የተለያየ ዜናና ሰነዳዊ ጥናት ይመሰክረዋል፣ በተለይ ደግሞ ብዙ ባይነገርም ባይባልም በጸጥታና በትዕግሥት የሚካሄዱት ግኑኝነት አመርቂ ውጤት እያስጨበጠ መሆኑ የሚያረጋግጥ ተጨባጭ ሁነት ነው።
በመጨረሻም በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በመላ ሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መካከል በተለያየ ሐዋርያዊ ኃላፊነት ሥር በመካሄድ ላይ ያሉት የተለያዩ ግኑኝነቶች በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.ና በፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል መካከል ታሪካዊ ግኑኝነት እንዲረጋገጥ መንግድ እያሰናዳ ነው ወይ ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፦ “በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚካሄደው ግኑኝነት አመርቂ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ለሁም ግልጽና ተጨባጭ ነው። በመጨረሻም በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና በመላ ሩሲያና ሞስኮ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ መካከል ታሪካዊ ግኑኝነት ቢጨበጥ ደስ የሚያሰኝና የሆሉም ፍላጎት ነው። ስለዚህ ይኽ ግኑኝነት እንዲረጋገጥ የሁሉም ተስፋ ነው። ስለዚህ በሚካሄዱት ግኑኝነቶች ርእሰ ስለ ጉዳይ ሃሳብ ለሃሳ መለዋወጥ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ግኑኝነት ተጀምረዋል ተጨባጭ አመርቂ ውጤትም እያሳገኘም ነው” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.