2013-12-16 15:44:24

ብፁዕ ካርዲናል በርተሎ፦ የገና ጥድ ሕይወታችንን የሚያበራ የመብራት ትእምርት


RealAudioMP3 በላቲን ሥርዓት ለሚከበረው ለዓለ ልደት ምክንያት ዘንድሮ ከጀርመን ባቪየራ ክፍለ ሃገር የተለገሰው የገና ጥድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በዚያኑ ዕለት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር የተገናኙት የባቪየራ ልኡካን በተገኙበት መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተባርኰ እንዲበራ መደረጉ ሲገለጥ፣ ከበዓለ ልደት በኋላ ይኽ 25 ሜትር እርዝማኔ ያለው የጥድ እንጨት ተጠርቦ በድኽነት ለተጠቁት ቤተሰብ ሕፃናት መጫወቻ መሥሪያ እንደሚውል ከወዲሁ ሲታወቅ የገና ዛፍ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለትርኢት ከሚቀርበው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የሚያወሳው ግርግም አጠገብ ለማቆም በተደረገው መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የተሳተፉት የአገረ ቫቲካን መሥተዳድር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ በርተሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በየዓመቱ ከተለያዩ አገሮች የሚለገሰው የገና ዛፍ እንዲቆም የማድረጉ መንፈሳዊው ባህል ደስ የሚያሰኝ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚገኙት ብቻ ሳይሆን መላ ዓለምን የሚወክል ነው። ከጀርመን ባቪየራ ክፍለ ሃገር የገና ጥድ ሲለገስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑም አስታውሰው፣ የገና ጥድ በሁሉም ባህሎች የሕይወት የሕዝቦች ጉዞ የሚያበራ የብርሃን ትእምርት ነው። ለእኛም ሕይወቱን ለሰጠው በልባችን ልንቀበለው ለሚመጣው ጌታችን ልደት የማሰናዳጃ ምልክት ነው፣ ሕይወት ሊሰጠን የሚመጣው ጌታ በልባችን ተቀብለን በብርሃኑ በርተን ብርሃኑን ወደ ዓለም ለማድረስ እንድንችል ለሚያነቃቃ ጸጋው መንፈሳዊነት ትእምርት ነው” ብለዋል።
የገና ጥድ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለማቆም በተካሄደው መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የተሳተፉት ለባቪየራ ክፍለ ሃገር ከኤውሮጳ የግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ በአተ መርክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “የገና ጥድ የወዳጅነት ምልከት ነው። በጀርመንና በቅድስት መንበር መካከል ያለው ወዳጅነት የሚመሰክር ነው ምክንያት ይኽ ዛፍ የዛሬ 60 ዓመት በፊት በዶማዝሊቸና ዋልድሙየንሽን አዋስኝ ድንበር በነበረው ጫካ የተተከለ ሲሆን፣ የሚለያየው ድንበር ተወግዶአል ለማለት፣ ስለዚህ የአዲስ ግኑኝነትና አንድነት ምልክት ነው። አንድነት ጸጋ ነው፣ ስለዚህ የገናው ጥድ እንዲህ ባለ መልኩ አስተንትኜዋለሁ” ብለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንዳሉት የገና ዛፍ የደስታ ምልክት ምክንያት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ የላቀው የፍጹም ደስታ ተጨባጭ ምልክት ነው፣ ስለዚህ በዓለ ልደት የሚለው ደስታ ነው በማለት የገለጡት ሃሳብ መርክ አስታውሰው፦ “በዓለ ልደት ከሚሰጠው ደስታ ጋር የሚስተከል ደስታ የለም ሊኖርም አይችልም” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.