2013-12-16 19:34:01

ቤተ ክርስትያን የያዘኑ ሰዎች ዋሻ አይደለችም፤ የደስታ ቤት ናት፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ም እመናንና ነጋድያን በተለይ ደግሞ ለበዓለ ልደት ግርግም መዘጋጃ የሕጻናት ምስሎች ለማስባረክ በአደባባዩ ለተገኙ ብዙ ሕጻናትን ልዩ ሰላምታ በማቅረብና ስለር.ሊ.ጳ እንዲጸልዩ አደራ ሲሉ አሳስበዋል፣
በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ትናንትና ሶስተኛው የምጽ አት እሁድ ሲሆን በዕለቱ ከተነበበው ቃለ እግዚአብሔር እጅግ ደስ ይበላችሁ ጌታ ይመጣልና! የጌታ መምጣት ቅርብ ስለሆነ ደስ ይበላችሁ! የሚሉ ጥቅሶችን በመጥቀስ የትናንትናው እሁድ የደስታ እሁድ ብለው ሰይመውታል፣ ይህ የምሥራች ዜና የክርስትያን መል እክት ነው መል እክቱም ለሁሉ ስለሆነ ሁሉ ደስ ይበለው፣
“ቤተ ክርስትያን የኃዘንተኞች ዋሻ አይደለችም ቤተ ክርስትያን የደስታ ቤት ነው፣ የወንጌል ደስታ እንደማንኛው ደስታ አይደለም እግዚአብሔር እንደተቀበልህና እንዳፈቀረህ ከማወቅ የሚወጣ ደስታ ነው፣ ሊያድነን ይመጣል በተለይ ደግሞ በልቦቻቸው ከእርሱ እጅግ ለራቁ ወደእርሱ ለመሳብ ይመጣል፣
“የእርሱ በመካከላችን መምጣት ያጸናናል ብርታትም ይሰጠናል ምድረበዳውንና የደረቀውን እንዲያብብ ያደርጋል፣ ሕይወታችን በትለያዩ ምክንያቶች ደርቃ ስትገኝ እርሱን ያገኘት እንደሆነች ትድናለች፣ ለምን መንፈሳዊ ድርቀት እንደሚሰማን ታውቃላችሁን! የሕይወት ወኃ የሆነው ቃሉና የመንፈሱ ፍቅር ያላገኘን እንደሆነ ነው፣ ስለዚህ የዛሬው ጥሪና የጌታ መምጣት መቅረብ የሚያበስረን ለጸጋውና ምሕረቱ ምስጋና ይድረሰውና እንደገና ለመጀመር እንነሳ እንታደስ ቃሉን እንስማ መፈሳዊ ፍቅሩን እንቀበለው፣ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው ሕጻናቱ ያመጡትን የልደት ግርግም ማስታወሻ ምስሎች ባርከው ለሕጻናቱ እንዲህ ሲሉ አደራ ብለዋል፣ “ውድ ሕጻናት በጌታ ልደት ማሳሰቢያ በረት ፊት ቆማችሁ ስትጸልዩ እኔንም አስታውሱ እኔም አስታውሳችኋለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ መልካም ልደት ይሁንላችሁ፣ ብለው ተሰናብተዋቸዋል፣ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን ደግሞ! “እየውላችሁ የክርስትያን ተስፋ፤ መጻኢያችን በእግዚአብሔር እጆች ነው” ሲሉ አጭር መልእክት ጽፈዋል፥







All the contents on this site are copyrighted ©.