2013-12-16 15:59:05

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ የዋህነት (ርህራሄ) መቼም ቢሆን ሊያስፈራን አይገባም


RealAudioMP3 በኢጣሊያ ላ ስታምፓ ከተሰየመው ዕለታዊ ጋዘጣ ጋዜጠኛ የስነ ቫቲካን ሊቅ አንድረያ ትርኒየሊ ጋር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ለእኔ በዓለ ልደት ተስፋና ርህራሄ ማለት ነው” የሚል የበዓለ ልደት ትርጉም የገለጡት አንድ ሰዓት ተኩል በፈጀው ቃለ ምልልስ፣ የሕጻናት ስቃይ በዓለም ስለሚታየው እርሃብ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በሌሎች አቢያተ ክርስቲያን ያለው ግኑኝነት ምሥጢረ ተክሊል እንዲሁም በ2014 ዓ.ም. እንዲካሄድ የጠሩት የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ዲኖዶስ የሚወያይበት ቤተሰብ ስለ ተሰኘው ርእስ በማደገፍ ከጋጠኛው ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በመስጠት፦ “ይኽ በዓለ ልደት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሲያከብሩት የመጀመሪያቸው መሆኑ አስታውሰው፦ “ከኢየሱስ ጋር መገናኘት፣ በዓለ ልደት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝበት ተጨባጭ ሁነት ከመሆኑም ባሻገር አጽናኝ ሁነትም ነው። ስለዚህ የማጽናናት ምሥጢር ነው። ተስፋና ርህራሄ ማለትም ነው፣ ቤተ ክርስቲያን ከቀዘቀዘ በራዳ ሕይወት ይኽም ከዓለማዊነት ከተለያዩ ፖለቲካዊ ርእዮትና በዓለ ልደት በዓለማዊነት መንፈስ የአከባበር ባህርይ ተላቃ ጥልቅ እውነተኛው ደስታ የምትኖርበት ሁነት መሆን አለበት፣ ዓለማዊ ደስታ በራዳ ነው” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ የቅድስት መሬት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዙሪያ ጥልቅ አስተንትኖ እንደሚያቀርቡ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ወንድሜ በማለት ከገለጡዋቸው የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ አንደኛ ጋር ለመገኘተት የሚያስችላቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማካሄድ ፍላጎቱ እንዳላቸው ከገለጡ በኋላ የንፁሓን ሕፃናት ስቃይ በምንም ዓይነት ተአምር ምክንያታዊ ለማድረግ የማይቻል ነው። ስለዚህ ኢምክኒያታዊ መሆኑ አብራርተው፣ በእርሃብ የሚሰቃዩት ሕፃናት በዓለም ለሚታየው አባካኝነትና ቸልተኝነት ምስክር ነው። ስለዚህ የሁሉም ኅሊና የሚነካ ጉዳይ ነው። መለወጥ እንዳለብን የሚጠራ ተጨባጭ ሁነት መሆኑ ገልጠው፣ ለዚህ ሁሉ መርህ ወንጌላዊ ሃሴት በተሰኘው ሐዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ ያሰመሩበት የቤተ ክርስቲያን የኅብረሰብአዊ አንቀጸ እምነት ትምህርት ነው። ኤኮኖሚያው ቀውስ ባልነበረበት የኤኮኖሚ ብልጽግና እየተኖረም ይኸንን እርሃብ ለማጥፋት አልተቻለም፣ ስለዚህ ችግሩ የኤኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአኗኗር ሥልት ጥያቄ ነው ብለው ጋዜጠኛ ማርክሲሳዊ የሚል መግለጫ ቢሰጠዎት ምን ይሰማዎታል ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፦ “ማርክሳዊነት የተሳሳተ ርእዮት ነው፣ ሆኖም ግን ብዙ መልካምና ደግ ማርክሳዊያን የሆኑ ሰዎች አውቃለሁኝ ስለዚህ ማርክሳዊ ብለው ቢገልጡኝ አያስቀይመኝም” ብለዋል።
የክርስቲያኖች ውህደት-አንድነት ተቀዳሚ ዓላማ ነው፣ የሰማዕትነት ውህደት በተለያዩ አገሮች በክርስትና እምነታቸው ምክንያት ለሞት የሚደረጉት የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ማኅበረ ክርስቲያን ምስክርነት በቀላሉ የሚገመት አይደለም፣ የእነዚህ ሰማዕታት ደም የአንድነት ጸጋ ያሰጠን ምክንያቱም አንድነት ውህደት ጸጋ ነው ብለው፣ ምስጢረ ተክሊል ስላፈረሱ ስለ ተፋቱና ዳግም ስለ ተዳሩ ሰዎች በማስመልከትም ስለ ፍችና ዳግም ቃል ኪዳን ስለ ማሰር ጉዳይ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ምንም አይነት ያላቸው የግል አቋም ሳይገልጥ፣ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. በሚካሄደው የመላ ብፁዓን ካርዲናላት ጉባኤና እንዲሁም በዚያኑ ዓ.ም. ጥቅምት ወር ለሚካሄደው የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጉዳይ በማስተላለፍ በቤተ ክርስቲያንና በፖለቲካ መካከል ቅን ግኑኝነት በሚለው ሃሳብ ዙሪያ ሲመልሱ፣ የፖለቲካውና የቤተ ክርስቲያን ተልእኮና ኃላፊነት የተለያየ መሆኑ በቅድሚያ ገልጠው ለሕዝብ ጥቅምና ድጋፍ በሚል እሴት የሚገናኙ ናቸው፣ ጳውሎስ ስድስተኛን ጠቅሰው ፖለቲካ ክቡር ዋጋ ነው፣ ይኽም ግብረ ሠናይ የሚፈጸምበት ተግባር ነው፣ ለግል ጥቅም ማስፈጸሚያ ስንገለገልበት እንሳሳታለን፣ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን አቢይ ክብር ሊሰጣችው ይገባል እንጂ ክህነታዊነት በሚል ሃሳብ መገምገም የለባቸውም እንዳሉ ጋዜጣውን የጠቀሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.