2013-12-16 16:05:23

ማረሊ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሰላም መልእክት በዓለም ተሰሚነት እንዲያገኝ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን ለመላ ዓለም የሚተላለፈው በቅርቡ በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል በሚገኘው ሕንፃ መግለጫ የተሰጠበት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሰላም መልእክት በማስደገፍ በምግብ እራስን የመቻል ሉአላዊነት ኮሚቴ በኢጣሊያ ተጠሪ ሰርጆ ማረሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የሰላሙ መልእክት ወንድማማችነት የሚል ነው ይኽም ወድማማችነት ሊፈቀር ሊበሰርና ሊመሰከር እንደሚያስፈልገው የቅዱስ አባታችን መልእክት ያመለክተዋል፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ወድማማችነት በጠቅላላ በዓለም ያለው ችግር ውጥረት እርሃብ ለመቅረፍ ብቻ ሳይሆን የእነዚህ ችግሮች ቀንደኛው ምክንያት የሆኑትን ጨርሶ እንዳይኖር የሚያደረግም ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ ወንድማማችነት ያለው አንገብጋቢነት ለመገመቱ አያዳግትም ብለዋል። ስለዚህ የበለጠው ዓለምና መጻኢ ለመገንባት ወድማማችነት መሠረት መሆኑ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ያሰመረበት ሃሳብ እውነት ነው በዓለም ሰላም ለመገንባት ወንድማማችነት ማርጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚጠቀሙበት ቋንቋ ለሁሉም ግልጽ ብቻ ሳይሆን በዙዉን ጊዜ በእለታዊ ሕይወት የምንዘነጋቸው ተራ የሚመስሉት እሴቶች በዓለም ለሚታዩት ጭግሮች የመፍቻ ቁልፍ ናቸው፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በተሰኘው ዓዋዲ መልእክታቸው በዓለም እንደ አርአያ የምንከተላቸው የልማት ሥልቶች በመዳሰስ ጥልቅ አስተያየት እንደ ሰጡበት ሁሉ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም መለስ ብለው እነዚህን የልማትና የእድገት ሥልቶችን በማጤን ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመላቀቅ ልንከተለው የሚገባንን መንገድ ይጠቁማሉ፣ ስለዚህ ለፖለቲካው ዓለም በጠቅላላ ሰላምና ምሉእ ብልጽግና ለማረጋገጥ መርህ መሆን የሚገባውን ያመለክታሉ፣ ዓለም አቀፋዊ መስተዳድራዊ ሥልት ያስፈላጋል፣ ይኽም የዓለም የሕዝቦች ጥቅም ለማስቀደም ያለመ እቅድ አንዱ የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ኅብረተሰብአዊ ትምህርት አስተሳሰብ ነው። ትኩረት ቢደረገበት በእውነቱ በዓለማችን ለሚታዩት የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚቻል ነው፣ እኩልነት በሁሉም መስክ፣ የዓለም ሃብት በእኩል ማዳረስ፣ የእደ ጥበብ ብልጽግና የተስተካከለና ፍትሃዊ አጠቃቀም ማነቃቃት የእርሻ ልማት ሥልቶችን ማረም፣ የመሳሰሉት በመልእክቱ በኢቀጥታዊ የተመለከቱት ነጥቦች ማጤን እጅግ አስፈላጊ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.