2013-12-11 16:10:44

የኤውሮጳ የገንዘብ ሃብት ምንጭ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ መግለጫ


RealAudioMP3 በኤውሮጳ ክልል አገሮች የገንዘብ ሃብት ምንጭ ለመቆጣጠር የወንጀል ቡድኖች አሸባሪያን ያካበቱት ሕገ ወጡ የገንዘብ ሃብት ህገ ውጥነቱን ለመሰወር በሕጋዊ የልማት ዘርፍ በማዋል ህጋዊነት ለማልበስ የሚያደርጉት ሽርጉድ የሚቆጣጠር ኮሚቴ በኤውሮጳ አገሮች ባንክ ቤቶች መዋቅሮች ግልጽ አሰራር እንዲኖር የሚያቀርበው መመሪያ እንደ ተለመደው በቅድስት መንበር ተቀባይነት ከማግኘቱም አልፎ ለግልጽነት አሠራር የምትከተለው መንገድ እድገት እያሳየ መሆኑ በሰጠው መግለጫ ሥር የቅድስት መንበር የቁጠባ የማስተዋወቂያና የመረጃ ባለ ሥልጣን አስተዳዳሪ ረነ ብሩልሃርት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የኤውሮጳው የገንዘብ ሃብት ምንጭ ተቆጣጠሪው ድርጅት ያካሄደው ምሉእ ጉባኤ በሰጠው ሁለተኛ የገንዘብ ሃብት ግልጽነት ሰነድ ቅድስት መንበር በዓለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብ ሃብት ምንጭ ለመቆጣጠር የሚያስችል መመዘኛ በላቀ አሠራር የምታከብር መሆንዋ እንዳሳወቀ ገልጠው በዓለም የገንዘብ ሃብት ምንጭ ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ቀጣይ መሆን አለበት ብለዋል።
የገንዘብ ሃብት ምንጭ የመቆጣጠሪያ ደንብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወንጀል ቡድኖች አሸባሪያን ሕገ ወጡ የገንዘብ ሃብታቸውን ሕገ ወጥነቱን ለመሰወር በተለያዩ የኤኮኖሚ ዘርፍ በማዋል የሚፈጽሙት ኤኮኖሚያዊ ብከላ ተግባር የሚቅጣጠር ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ሃብት ምንጩ ከየት ለሚል ጥያቄ መልስ የሚያሰጥም ነው። ስለዚህ ይኸንን ደንብ ማክበር ሥነ ምግባራዊና ግብረ ገባዊ ግዴታ መሆኑ በማብራራት፣ ቅድስት መንበር በዚህ ዘርፍ የጨበጠቸው አመርቂ ውጤት ላይ ሳትጣጠር ዘወትር ለበለጠ መሻሻል አወንታዊ ግፊት እንደሚሆናት አያጠራጥርም በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.