2013-12-11 16:07:24

የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር የሚያቅፈው ካርቲታስ ኢንተርናዚዮናሊስ “ሰብአዊ ቤተሰብ፣ምግም ለሁሉም” የጸረ ረሃብ ዘመቻ መርሃ ግብር


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. እስከ 2025 ዓ.ም. ባለው የአመታት ገደብ ውስጥ ከዓለም እርሃብ ጨርሶ ለማስወገድ አንድ ሰብአዊ ቤተሰብ፣ ምግብ ለሁሉም” በሚል መርህ ቃል ትላትና ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብትና ክብር ዕለት ታስቦ በዋለበት ዕለት የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራትን የሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ማኅበር የጸረ ርሃብ ዘመቻ እቅድ ማቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የሰው ልጅ ምግብ ማግኘት መሠረታዊ መብት መሆኑ ያሳሰበው የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ የጸረ እርሃብ ጥሪ በዓለም የሚታየው ምግብ የማብከን ተግባር የሆነው አቢይ ሰብአዊ ጉድለት ሁሉም ተገንዝቦ ይኽ አንዱ የርሃብ መሠረት መሆኑ ታምኖ በተለይ ደግሞ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ነቅቶ ምግብ የማባከን ባህል በመቅረፍ ምግብ ለሁሉ በሚል ዓላማ ተግቶ እንዲገኝ ምዕዳን የሚያቀርብ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ ከካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ ሚሸል ሮይ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የተሰመረበት ሃሳብ መሆኑ ገልጠው፣ ሮይ ይላሉ፦ “አለ ምግብና የሚጠጣ ውኃ ለመኖር አይቻልም፣ መሠረታዊ እውነትም ነው፣ ይኽ እውነት የዛሬ 65 ዓመት በፊት በጸደቀው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትና ክብር ውሳኔ ዘንድ አቢይ እውቅና የተሰጠው መብት ነው። ሆኖም እውቅናው በዓለም አቀፍ ደረጃና በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ሕግ ሆኖ ምግብ ለሁሉም ግዴታ ነው ማለት ይጠበቅበታል፣ ምግብ ማግኘት ሰብአዊ መብት ነው። ስለዚህ ርሃብ ጸረ ሰብአዊ መብትና ክብር ነው። በመሆኑም ሁሉም አገሮች የሕዝቦቻቸው ምግብ የማግኘት መብት እንዲከበር የማድረጉ ኃላፊነት ቅድሚያ ሊሰጡበት ይገባል። ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ይኸንን ማእከል በማድረግ እርሃብ አቢይ እንቅፋት ነው። እንዴት የሰው ልጅ ይቅር አንድ ጊዜ በቀን ከዛም ባነሰ እድል መኖር ይችላልን? ምግብ ያለ ማግኘት ችግር ለሁሉም አገሮችና መንግሥታት አቢይ ሃፍረት ነው” ብለዋል።
የምግብ እጥረት ወይንም እርሃብ የፖለቲካ አካላት ያስከተሉት መዘዝ ነው እየተባለ የፖለቲካ አካላት ብቻ መወቀሱ ቀላል ኃላፊነት አልቦ ስሜት መግለጫ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚታይ ተግባርም ነው። ስለዚህ ችግሩ ሁላችን የሚመለከት በመሆኑም የምንከተለው የኑሮ ስልት፣ የአኗኗራ ዘይቤ እና አርአያ መመልከቱ የእያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነት መሆኑ ያብራሩት ሮይ አክለው፣ ትብብርና መደጋገፍ መተሳሰብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ለማኅበራዊ ኑሮ መሠረት ነው። ስለዚህ የትብብር መንፈስ ኵላዊው ወድማማችነት ያነቃቃል በመሆኑም እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን መልእክት ወድማማችነት በሚል ርእስ ሥር እንዲመራ መወሰኑ አለ ምክንያት እንዳልሆነም አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝም በሰነጋል ለካሪስታስ ኢንተርናዚዮናሊስ አመራር አካላት ዋና ጸሐፊ አምብሮይሰ ቲነ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ አፍሪቃ የሰው ልጅ ክብርና ሁሉም የሰው ልጅ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲረጋገጥለት ከዚህ መብትና ክብር ጥበቃ ማንም መነጠል እንደሌለበት ሁሉም የተከበረ ኑሮ እንዲኖር መሠረታዊ መብቱ ተጠብቆለት የተሟላ መረጃና ማስታወቂያ የማግኘት መብቱ ጭምር ተከብሮለት እንዲኖር በእውነቱ እንደ ነልሶን ማንዴላ የመሰሉ ባለ ራዕይ መሪዎች ያስፈልጉዋታል። በአፍሪቃ የሚታየው የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ፣ የአፍሪቃ ሃብት በጥቂቱ እጅ ቁጥጥር ሥር ሆኖ ማየቱ አቢይ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ነው። እንዴት አንድ ቤተሰብ በርሃብ ቸነፈር እየተሰቃየ ደህና እንደር እንደምን አደርክ ለማለት ይቻላል፣ በርሃብ እየተሰቃየ ደህና ማደርና ደህና መዋል ይቻላልን? ይቅር ማደሩና መዋሉ በሕይወት መኖርም ያሰጋል፣ የዓለም አቀፍ በተለይ ደግሞ የአፍሪቃ መንግሥታት ሰብአዊነት የተካኑ ጭምር መሆን አለባቸው፣ ኃብታም የኅብረተሰብ ክፍል የሚባለው ሰብአዊነት የተካነ መሆን እንደሚገባው ካሳሰቡ በኋላ በሳሄል ክልል አገሮች በርሃብ የሚሰቃየው ዜጋ በዓለም ምግብ የማባከኑ ተግባር ሲያይ። ምግብ የሚያባክኑ ሰዎች በርግጥ ሰብአውያን ናቸውን የሚል ጥያቄ ነው የሚያቀርበው፣ እንዱ በርሃብ ለሞት አደጋ ሌላው ጠግቦና ተትረፍሮለት ምግብ ሲያባክን ማየቱ ኢፍትሃዊነት ነው። ምግብ ለሁሉም በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.