2013-12-04 18:59:45

የር.ሊ.ጳ ሳምታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


“ኢየሱስም ለማርታ እንዲህ አላት። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።” (ዮሐ 11፤24-26)
ውድ ወንድሞችና እኃቶች! እንደምን አደራችሁ! ዛሬ “በትንሣኤ ሙታን አምናለሁ” ወደሚለው የጸሎተ ሃይማኖት ክፍል እንደገና እመለሳለሁ፣ ይህ ዓንቀጽ ቀላል አይደለም ሆኖም ግን ግልጽም ነው ምክንያቱም በዚሁ ዓለም ጠልቀን ስንኖር ስለሚመጣው ሕይወት መረዳት ቀላልም አይደለም፣ ነገር ግን ወንጌል ያብራረዋል፤ የእኛ ከሞት መነሣት ከክርስቶስ ትንሣኤ ሙታን ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው፣ የእርሱ ከሞት ተለይቶ መነሣት የሙታን ትንሣኤ መኖሩን ያረጋግጥልናል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤና የእኛ ትንሣኤ ግኑኝነትን የሚመለከት አንዳንድ ነገሮች ለማመልከት እወዳለሁ፣ እርሱ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በዚህም ምክንያት እኛም እንነሳል፣
ከሁሉ አስቀድመን የተመለከትን እንደሆነ ቅዱስ መጽሓፍ ለትንሣኤ ሙታን ሙሉ እምነት የሚመራን ብዙ ነጥቦች ያቀርብልናል፣ ይህ የሚገልጠው ነገር እንዳለ እግዚአብሔር ንፍሳችንና ሥጋችን መላውን ሰው የፈጠረና ነጻ የሚያወጣ መሆኑን ነው፣ ይህ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገውን ኪዳን እንደሚጠብቅና ለቃሉ ታማኝ መሆኑን ይገልጥልናል፣ ነቢይ ሕዝቅኤል ስለ እስራኤል ትንሣኤ በተገለጠለት ራእይ በምዕራፍ 37 ላይ በደረቀ አጥንቶች ሸለቆ በሞቱት ላይ ትንቢት ሲናገርና ዐጥንቶቹ ሕይወት ሲዘሩ ያያል፣ ይህም በስደት የነበሩ እስራኤላውያን እንደገና በመንፈስ ቅዱስ እንደሚነሡ በዚህም ያ የተሸነፈውና በስደት ሲማቀቅ እና ራሱን ዝቅ እንዲያደርግ የሆነው የሕዝበ እራኤል ትንሢኤ መሆኑን ያመልክታል፣
ኢየሱስም በአዲስ ኪዳን ይህን ትንቢት ፍጻሜ ላይ ያደርሰዋል፣ ያንን ትንሣኤ ከገዛ ራሱ ጋር በማያያዝም “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ” (ዮሐ 11፤25) ይላል፣ እንደእውነቱም ከሆነ በመጨረሻው ቀን በእርሱ ባመኑ ጊዜ ከሙታትን ተለይቶ የሚነሣው ኢየሱስ እንደሆነ ታይተዋል፣ ኢየሱስ በመካከላችን መጣ ከኃጢአት በስተቀርም በሁሉ እኛን መሰለ እንዲህ በማድረግም ወደ አባቱ ሲመለስ እኛ ሁላችንን ከእርሱ ጋር አነሳን፣ እርሱ ሥጋ የለበሰ የእግዚብሔር ቃልና ለእኛ ሞቶ የተነሣ እና ለምንጠባበቀው የክብር መንግሥት ቀብድ የሆነው መንፈስ ቅዱስን ለሓዋርያቱ ሰጥተዋል፣ ያ የምንጠብቃትን የምንንከባከባት ተስፋችን ምንጭና ምክንያትም ይህ መጠባበቅ ነው፣ ይህች ተስፋችን የተንከባከብናትና የጠበቅናት እንደሆነ የሕይወታችን ታሪክንና ጉዞን እንዲሆም የማኅበሮቻችን ታሪክን ሳይቀር ታበራለች፣ ማስታወስ ያለብን እኛ የማን ተክታዮች መሆናችንን ነው፣ የዛው የመጣና እየመጣ ያለ ወደፊትም የሚመጣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቶች መሆናችንን እናስታውስ፣ ይህንን እውነት በኅልናችን ለማኖር ከቻልን በየዕለቱ የሚያጋጥሙንን ድካሞች በማሸነፍ ከዚሁ ዓለም አስተያየት እስር ልንላቀቅ እና በድህነት ጐዳና በመሓሪ ልብ ለመጓዝ ይረዳናል፣
ሌላ ነጥብ ያነሣን እንደሆነ ደግሞ ከሙታን ተለይቶ መነሣት ማለት ምን ማለት ይሆን! ትንሣኤ ሙታን የእኛ ሁላችን ትንሣኤ ሙታን በመጨረሻው ቀን ዓለም ሲጨረሽ በእግዚአብሔር ከሃሌኩሉነት ስጋችንን ከነፍሳችን ጋር አንድ በማድረግ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ይጸማል፣ የዚሁ መሠረታዊ መግለጫም ይህ ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ስለተነሣ እኛም እንነሣለን፣ እርሱ የትንሣኤ በርን ስለከፈተልን ለዚሁ ትንሣኤ የሚሆን በርን ስለከፈተልን እኛ በትንሣኤ ሙታን ተስፋ አለን፣ በዚህም ይህ አሁን የምንገኝበት መጠባበቅ በትንሣኤ ሂደት ላይ ስላለን የሥጋችን መለወጥ ከኢይርሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን መገናኘት ይከናወናል! ይህም በምሥጢራቱ በተለይ ደግሞ ምሥጢረ ቍርባንን በመሳተፍ እውን ይሆናል፣ በዚህ ዓለም ሳለን ሥጋውንና ደሙን የተመገብን እኛ ሁላችን በእርሱ አማካኝነት ከእርሱ ጋር ከሙታን ተለይተን እንነሳል፣ ኢየሱስ ከሰነቱ ጋር እንደተነሣው ሆኖም ወደ ምድራዊው ሕይወቱ እንዳልተመለሰ ሁሉ እኛ በክብር ከተለወጠው ሥጋችን ጋር እንነሣለን፣ መንፈሳዊ ሰውነት ይዘን እንነሣለን፣ ይህ ውሸት አይደለም እውነት ነው! ኢየሱስ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሳ እናምናለን! በአሁኑ ሰዓት ኢየሱስ ሕያው መሆኑን እናምናለን! እናንተስ ኢየሱስ ሕያው መሆኑን ታምናላችሁ ወይ! አታምኑም እንዴ! ታምናላችሁ ወይስ አታምኑም! ኢየሱስ ሕያው ከሆነ እኛን ሞተን እንድንቀር ሳንነሣ እንደንቀር ሊያደርግ ይችላል ወይ! አይደለም! እርሱ እየተጠባበቀን ነው፣ እርሱ ከሙታን ተለይቶ ስለተነሣም ከሙታን ተለይቶ በተነሣበት ኃይል ለኛ ለሁላችን ከሙታን ያነሣናል፣ ገና በዚህ ምድር ላይ እየኖርን በክርስቶስ ትንሣኤ መሳተፍ እንችላለን፣ ኢየሱስ በዓለም መጨረሻ ከሙታን የሚያነሳን ከሆነ በአንድ በኩል ከእርሱ ጋር ድሮ ከሙታን እንደተነሣን እውነት ነው፣ ዘለዓለማዊው ሕይወት በዚሁ ጊዜ ሊጀምር ይችላል፣ በዚህ ዓለም እየኖርን በመጨረሻ ዓለም በሚሆነው ትንሣኤ ላይ ስንጠባበው ትንሣኤ እዚ ይጀምራል፣ ድሮ ተነስተናል፣ እንደእውነቱ ከሆነ ምሥጢረ ጥምቀት በተቀበልንበት ጊዜ ከኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ገብረትናል በዚህም በአዲስ ሕይወት እንሳተፋለን ይህም ከእርሱ ጋር በመኖር ነው. ስለዚ የመጨረሻውን ቀን ስንጠባበቅ የትንሣኤ ዘር በውስጣችን ይዘናል፣ ይህም እንደ ውርሻ ለምንቀበለው ለዘለዓለማዊው ሕይወት ጅማሬ ነው፣ ስለዚህ የእያንዳንዳችን ሰውነት የዘለዓለማዊ ሕይወት ድምጽ ስለሚያስተጋባ በክብር መጠበቅ አለበት የሚሰቃዩ ሰዎች ሕይወትን ማፍቀር አለብን ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት መቅረብን ሊያጣጥሙና ከሥቃይ ሕይወት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲያተኵሩ ይረዳቸዋል፣ ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ተስፋ ይሰጠናል፣ በትንሣኤ ሙታን ጐዳና እየተጓዝን ነው፣ ደስታችንም ይህ ነው፣ አንድ ቀን ኢየሱስን እናገኛለን ሁላችንም በኅብረት እንገናኛለን በዚሁ አደባባይ ሳይሆን በሌላ ቦታ ከኢየሱስ ጋር እንደሰታለን፣ የመጨረሻው ሕይወታችንም ይህ ነው፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.