2013-12-04 15:58:44

ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ፦ ለውህደት ያቀና ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የሚደረገው የጋራ ውይይት ባህርይ ያለው ሐዋርያዊ ጉብኝት


RealAudioMP3 የክርስትያኖች ውህደት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኮኽ በዋና ጸሐፊያቸው ብፁዕ አቡነ አንድረያ ፓልሚየሪ ተሸኝተው እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚያጠናቅቁት በሮማኒያ የክርስቲያኖች ውህደት ባህርይ ያለው ሐዋርያዊ ጉብኝት እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. መጀመራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፅዕ ካርዲናል ኮኽ በዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በሮማንያ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለውህደት ታልሞ የሚካሄደው የጋራው ውይይት ያሰጠው አመርቂ ውጤትና የጋራው ውይይት የደረሰበትን ደረጃ እንደሚገመግሙና በሮማንያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዳኔል ጋር እንዲሁም በሮማኒያ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሉሲያን ሙረሳን እንዲሁም ከቡካሬስት ሊቀ ጳጳሳት የሮማኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዮአን ሮቡ ጋር እንደሚገናኙ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በሮማኒያ በአልባ ዩሊያ የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ግዮርግይ ጃኩቢኒና በችሉይ ጀርላ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍሎረንቲን ክሪሃልመኑዋ ጋር እንደሚገናኙ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.