2013-12-04 15:56:18

ብፁዕ አቡነ ፓሮሊን፦ ዛሬ እንክብካቤ ከሚደረግለት ሕፃን የነገ ደስታ ይወለዳል


RealAudioMP3 ዛሬ ሕፃናት በተለይ ደግሞ በጠና በሽታ የተጠቁትን በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙትን ሕፃናት በመንከባከብ ሰላም የተካነውን መጻኢ መጠባበቅ፣ ማለትም የነገው ደስታ የሚወለደው የዛሬው ሕፃን ከመንከባከብ መሆኑ የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ፒየትሮ ፓሮሊን ትላትና በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ የሕፃን ኢየሱስ ሕክምና ቤት ለመደገፍ ታልሞ የቀረበው የጥዑም ውሁድ ሙዚቃ ትርኢት ፍጻሜ ባሰሙት ንግግር ገልጠው፣ የአንድ ኅብረተሰብ ሥነ ምግባራዊ ተክኖ የሚመዘነው ለሕፃናት የኅብረሰብ ክፍል የሚሰጠው እንክብካቤ ነው የሚለውን የቲዮሎጊያ ሊቅ ቦንሆፈር ጠቅሰው በማብራራት፣ የዚህ ዓይነት የሙዚቃ ትርኢት ለሕፃናት ጉዳይ ታስቦ የሚቀርብ በመሆኑም ያለው ክብር የላቀ ነው፣ ሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት የሥነ ምርምር ማእከልና የሥነ ሕክምና ጥልቅ ምርምር የሚከናወንበት የሚደነቅ ሕክምና ቤት ነው፣ ሆኖም ተደናቂ የሚያስብለው የላቀው ክብር ለሕፃናት የሚሰጠው የህክምና እንክብካቤ መሆኑ በመግለጥ፦ “ለሕፃን ትውልድ በተለይ በጠና ታመው ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ ለተጠቁትና በልጆቻቸው ህመም በስቃይ ለሚኖሩ ወላጆች መሠረታዊ የሆነው ሁሉ ማቅረብ የአንድ ኅብረተሰብ ወይንም የአገር ለመረጋጋት ምክንያት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዚህ ሕክምና ቤት በሕክምና ቤቱ ለሚገኙት ሠራተኞች የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ለህሙማን በተለይ ደግሞ ለሕሙማን ሕፃናት ቅርበታቸውንና ጸሎታቸውን አረጋግጣለሁ፣ እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ሕክምና ቤቱን ይጎበኛሉ” ካሉ በኋላ፦ “የጨቅላነት እድሜ እንክብካቤ ሲደረግለትና ስለ ሕፃናት እንክብካቤ ቅስቀሳ ሲደረግ ለተስተካከለ ለተረጋጋ መጻኢ ተስፋ ከፍ ያለ ይሆናል፣ ስለዚህ የብሩህ የተረጋጋ መጻኢ መለኪያው ዛሬ ለሕፃናት የኅብረተሰብ ክፍል የሚሰጠው እንክብካቤ ነው። ይኽ የቀረበው የውሁድ ጥዑም የሙዚቃ ትርኢት ካለው ዓለማ አንጻር ሲታይም የላቀ በመሆኑ በእውነቱ ክቡር ትርኢት ነው። በጠና ለታመሙት ሕፃናት ድጋፍና የእነርሱና ለወላጆቻቸው የሚወለደው ኢየሱስ ሕፃን አርአያ ነው” በማለት ለሁሉም የሙዚቃውን ትርኢት ላዘጋጁት አመስግነው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ቡራኬ ለሁሉም በማረጋገጥ ያሰሙት ንግግር እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.