2013-12-04 15:55:19

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አልቦ ፍስሃ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ማሰብ ፈጽሞ የማይቻል ነው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ፦ “አልቦ ፍስሃ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ለማሰብ ፈጽሞ የማይቻል ነው። ክርስቶስን በፈገግታ ማወጅ” በሚል ሃሳብ ዙሪያ ባሰሙት ስብከት፦ “ዘወትር ኢየሱስ አዲስ ቃል ሲያውጅ፣ ሲያስተምር ሲፈውስ በመገድ ሲጓዝ፣ በመጨረሻ እራት በደቀ መዛሙርት ተሸኝቶም እያለ እናስባለን፣ ሆኖም ግን ፈገግታና ፍስሃ የተሞላው ኢየሱስ ማሰብ የሚሳነን ሆነን እንገኛለን። ኢየሱስ ደስታ የተሞላው ደስተኛ ነው፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ደስ ይሰኛል አባቱንም ይወድሳል፣ ይኽ ደግሞ ኢየሱስ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለው ግኑኝነት የሚገልጥ ነው። የእርሱ ዘለዓለማዊና ውስጣዊ ደስታና ለእኛም ለግሶልናል” ካሉ በኋላ ቀጥለውም ይኽ ደስታ እውነተኛ ሰላማችን እርሱም ሥነ ውበትና ኪነ ጥበባዊ ሰላም እንዲሁም ዝምታ ማለት ሳይሆን ደስታ ማለት መሆኑ አብራርተው፦ “አልቦ ፍስሃ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ማሰብ ፈጽሞ የማይቻል ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ደስታም ኢየሱስን ማበሠር ነው። እርሱ ጌታ ነው፣ እርሱ ሙሽራዋ ነው። እርሱ ያድነናል አብሮ ከእኛ ጋር ይጓዛል ብሎ ማበሠር ነው የቤተ ክርስቲያን ደስታ፣ ቤተ ክርስቲያን የእርሱ ሙሽራ መሆንዋ በሚሰጣት ደስታ አማካይነትም እናት ትሆናለች፣ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የቤተ ክርስቲያን ደስታ ወንጌል ማስፋታትና ለሁሉም ማዳረስ ነው፣ በዚህ ጉዞ በመራመድ ስለ ሙሽራዋ መናገር ነው። እርሷ ይኸንን ደስታ ለምትወልዳቸውና ለማደግ ለምትንከባከብቸው ልጆችዋ ታስተላልፋለች” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
“ነቢይ ኢይሳያስ የሚናገረው ሰላም የሚንቀሳቀስ ደስታና ምስጋና መሆኑ ይገልጥልናል፣ አንገብጋቢና ጥብቅ በሆነ ጊዜም ቢሆን ኢየሱስ አለ ደስታ የሚኖር አይደለም፣ ቤተ ክርስቲያና ደስተኛ ነች፣ ሙሽራዋ ከእርሷ በተለየና ጋለሞታ ሆና በሚሰማት ወቅትም ደስታ ክእርሷ አይለይም፣ በተስፋ ደስተኛ ነች፣ ለሁላችን ጌታን ይኸንን ደስታ ይለግሰን፣ እግዚአብሔርን በመንፈስ የማመስግን ኢየሱሳዊውን ደስታ ያድለን፣ ወንጌልን ማስፋፋትና ማወጅ የእናታችን ቤተ ክርስቲያን ደስታ ነው” ብለው ያሰሙትን ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለስጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.