2013-11-29 17:38:51

እምነት የግል ጉዳይ አይደለም! ክህደትና ስደት ቢበዛም እግዚአብሔር እስከመጨረሻ ማምለክ ያስፈልጋል፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና በቅድስት ማርታ ቤተ መቅደስ ባሳረኩት መሥዋዕተ ቅዳሴ “በዓለማችን ውስጥ ሃይምኖትን የግል ጉዳይ ለማድረግ የሚሹ ዓለማዊ ሥልጣኖች አሉ፤ ነገር ግን ዓለምን ያሸነፈው እግዚአብሔር በእምነትና በመተማመን እስከመጨረሻ ይመለካል” ሲሉ ክርስትያኖች በዘመናችን ምንምኳ በስደት የሚገኙ ቢሆን ይህ ስቃይ የመጨረሻውን የኢየሱስ ድል የሚያመለክት ፈተና መሆንን ገልጠዋል፣
የዚሁ ሳምንታት ሥርዓተ አምልኮ የሚያሳስበን በእግዚአብሔርና በጸላኤ ሠናያት መካከል በሚካሄደው የመጨረሻ ፍልምያ ሲያሳስበን በዘመናችን ታላቅ ችግር እንዳለና ይህንም በቅዱስነታቸው አገላለጽ ዓለም አቀፍ ፈተና ተብሎ እንደተጠራ ተመልክተዋል፣ ይህ ፈተና በእግዚአብሔር ላይን በእርሱ በሚያምኑ ላይ ለረዥም ዘመናት የነበረውን መተሳሰርና መተማመን ለመቍረጥ እየታገለ ነው፣ ሆኖም ግን አማኝ የሆነ ሁሉ መከተል ያለበት ጥርት ያለ አስተማማኝ ማመልከቻ አለ፣ ይህም የኢየሱስ ታሪክ ነው፣ በምድረበዳ ጾምና ፈተና የሚጀምረው የኢየሱስ ሕይወት በምድራዊ ሕይወቱ ብዙ ፈተናዎች ሕሜታዎችና ተቃውሞች በመጨረሻም እስከ መስቀል ያደረሱት ጥላታዎች ሲገኙበት በመጨረሻ ይህ የዓለም ንጉሥና የሰላም መስፍን የሆነው ክርስቶስ በትንሣኤው ዓለም ተሸነፈ፣ ሲሉ በዕለቱ የተነበበው ከሉቃስ ወንጌል 21፡27-28 “በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።” የሚለውን አስደሳች ዜና አስቀድሞ ያለው የመጨረሻ ዓለም ምልክቶች አመልክተውም እንዲህ ብለዋል፣
“ኢየሱስ ስለ የዓለም ማለቅ ሲናገር መጀመርያ የቤተ መቅደስ መርከስ የእምነት መርከስ እንዲሁ የሕዝቦች ስደትና ሞት ብቸኛነትና ችግር እንደሚያጋጥም ይናገራል፣ የዚህ ትርጉም ምን ይሆን? የዚህ ዓለም መስፍን ያሸንፍ ይሆን! እግዚአብሔር ይሸነፋልን! ብለን የጠየቅን እንደሆነ እንደሚመስለኝ የመጨረሻው ፈተና አንኳር ይህ ነው፣ ለጥቂት ጊዜ የዚህ ዓለም መስፍን በዚሁ የመጨረሻ የፈተና ጊዜ ሥልጣን ሊያገኝ ነው፣ በትንቢተ ዳኒኤል እንደተመለከተው ነቢይ ዳኒኤል በእምነቱ ምክንያት ለአንበሶች ሲሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳያመልክ ሲከለከል ይህንን ሁኔታ ያመልክታል፣ ምንም እንኳ ከአንበሶች አፍ ቢያድነውም ግን እስከ ሕይወት መሥዋዕት ለማቅረብ ያለውን ቍርጠኝነት ለመግለጥ አታምልክ አትስገድ የሚለውን ሕግ በመጣስ በቀን ሶስቴ ስግደቱና አምልኮውን ያቀርብ ነበር፣ ይህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚነግረን በመጨረሻ ሰዓት የሚከሰተውም የዚህ ዓይነት ነው የዚህ ዓለም ባለሥልጣኖች እንዳታምልኩ እንዳትሰግዱ ብለው የሚያስገድዱበት ጊዜም ሊኖር ነው፣
“ስለሃይማኖት ለመናገር አይፈቀድም! ሃይማኖት የግል ጉዳይ ነው! በሕዝባዊ ቦታዎች ስለሃይማኖት አትናገሩ! የእምነት ምልክቶች ስህተት ናቸው! ከዓለም ባለሥልጣናት ለሚሰጡ ት እዛዞች ማክበር አለባችሁ! ብዙ መልካም ነገሮች ለማድረግ ነጻነት አለ እግዚአብሔርን ማምለክና ለእርሱ መስገድ ግን አይፈቀድም፣ የሚሉ ሁኔታዎች እያየን ነው፣ ይህም የመጨረሻ ቅርበትን ያመልክታል፣ የዚሁ አረመናዊ ዝንባሌ ድል በሰፊው ከተገለጠ በኋላ ያኔ ጌታ በክብር ይመጣል፣ የሰው ልጅ በታላቅ ኃይልና ክብር በደመና ተጭኖ ሲመታ ያያሉ፣ ብዙ ስደትና መከራ የሚቀበሉት ክርስትያኖች እንዲሁም ለእግዚአብሔር አምልኮና ስግደት እንዳያቀርቡ የሚከለከሉ ክርስትያኖች የዚሁ ትንቢት ምልክት ናቸው፣ ስለዚህ የከሓዲዎች እና የዚህ ዓለም ባለሥልጣናት ጊዜ ያበቃለትና የኢየሱስ ክርስቶስ ድል አድራጊነት ስለተቀራበ ራሳችን ከፍ የማድረግ ጊዜ ደርሰዋል፣
“አንፍራ! እርሱ የሚጠይቀን ነገር ካለ መተማመንና ትዕግሥት ነው፣ እንደ ዳኒኤል ነቢይ ታማኞች እንድንሆን ይፈልገናል፣ ዳኒኤል ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር እስከ መጨረሻም ለእግዚብሔር ስግደትና አምልኮ አቅርበዋል፣ ት ዕግሥትም ያስፈልገናል ምክንያቱም በት ዕግሥት የተጠባበቅን እንደሆነ ከጠጉሮቻችንም ምንም የሚወድቅ የለምና፣ ጌታ የሰጠን ተስፋና የገባልን ቃል ይህ ነው፣ በዚሁ ሳምንት ስለ አጠቃላይ ክህደት እናስተንትን ይህ የአጠቃላይ ክህደት ጌታን ማክበርንና ማምለክን የሚከለክል ነው፣ እስቲ ወደ ገዛ ራሳችን መለስ ብለን ጌታን አመልካለሁን! ወይስ እንዲያው ግማሽ ግማሽ ዓይነት የዚሁ ዓለም መስፍን አግባብ እከተላለኡ! ጌታን እስከ መጨረሻ በእምነትና በመተማመን ማምለክ ያሰፈልጋል ጌታ ይህንን ጸጋ እንዲሰጠን እንለምነው፣ ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
ይህ በእንዲህ ሳለ ቅዱሳችን ዘወትር እንደሚያደርጉት ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን የመገናኛ ብዙኃን ፖስታቸው “ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች መሆንን እንማር በዚህም ሁሌ ለሚናገረን አስደናቂው የጌታቃልን ለመቀበል ዝግጁ እንሆናለን” ሲሉ አጭር መል እክት ጽፈዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.