2013-11-27 16:05:17

ጳጳሳዊ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሚከታተለው ምክር ቤት ጉባኤ


RealAudioMP3 በአገረ ቫቲካን “የተለያዩ የሃይማኖት ባህሎች አባላት በኅብረተሰብ” በሚል ርእስ ዙሪያ እንዲወያይ ጳጳሳዊ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሚከታተለው ምክር ቤት የጠራው ይፋዊ ምሉእ ጉባኤ እየቀጠለ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዣን ባፕቲስት ኮካኘ ገለጡ።
ጳጳሳዊ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሚከታተለው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን በዚህ አጋጣሚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአሁኑ ወቅት በተለይ ደግሞ በኤውሮጳ ሃይማኖት እንደ ችግር የሚታይ እየሆነ መምጣቱ እጅግ የሚገርም ነው። ሃይማኖት ለኅብረሰብ አቢይ ሃብት እንጂ ችግር አይደለም ብለው፣ የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች ሲገናኙ ለኅብረተሰብ መልካም እርሾ ይሆናሉ፣ ስለዚህ መገናኘት እያንዳንዱ ሃይማኖት ከገዛ እርሱ ለተለየው ሃይማኖት ክፍት መሆን የማዳመጥ የመረዳዳት የመስማማት እድልና ሥፍራ በጋራ መገንባት የሚልና ይህ ዓይነቱ ግኑኝነት በተረጋገጠበት አገር የሚታየው አመርቂ ውጤት ለሁሉም ግልጽ ነው። ስለዚህ የሃይማኖት ግኑኝነት የሰላም መሣሪያ ነው። ለሰው ልጅ ብልጽግናና የተሟላ አድገት ሃይማኖት የሚሰጠው አስተዋጽኦ ለመካድ ፈጽሞ የማይቻል እውነት ነው ብለዋል።
የተለያዩ ሃይማኖች መካከል የሚካሄደው ግኑኝነት በቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖቶች ዘንድ በማነቃቃት ስለዚሁ ጉዳይ የሚከታተለው ልዩ ተቋም መዋቅር እንዲመሠረት በማድረጉ ምክንያት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ከመተዋወቅ ከመቀራረብ የመነጨ ግኑኝነት ያለው አስፈላጊነት እጅግ ትኩረት እየተሰጠበት ነው። ይኽ ዓይነቱ ውሳኔም በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከሩቅ የመጣ የቆየ ባህል መሆኑ በማረጋገጥ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.