2013-11-27 18:45:48

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በጸሎተ ሃይማኖት ላይ እያስተማሩት ያሉትን ትምህርት በመቀጠል “ስለ ትንሣኤ ሙታን” ሰፊ ትምህርት አቅርበዋል፣ ቅዱስነታቸው ትምህርቱን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች ከጻፈው መልእክት 15፡12 “ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ የሚሰበክ ከሆነ ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ። ትንሣኤ ሙታን የለም እንዴት ይላሉ? ትንሣኤ ሙታንስ ከሌለ ክርስቶስ አልተነሣማ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤” የሚለው ጥቅስ በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ የሚከተለውን ትምህርት አቅርበዋል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች እንደምን አደራችሁ! ዛሬ ባለፈው ዕለተ እሁድ የተደመደመዉን የእምነት ዓመት ምክንያት በማድረግ ለረዥም ጊዜ ያደረግሁትን ስለጸሎተ ሃይማኖት ያደረግሁትን ትምህርተ ክርስቶስ ለማጠቃለል እወዳለሁ፣ በዚሁ እና በሚመጣው ሳምንት በምናደርገው ትምህርተ ክርስቶስ ስለ ሥጋችን ከሞት መነሳት ለመናገር እወዳለሁ፣ ለዚህም በአዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ሃይማኖት ላይ እንደተመለከተው በክርስቶስ ስለመሞታችንና በክርስቶስ ከሙታን ተለይተን ስለመነሳታችን ለመናገር እወዳለሁ፣ በዛሬው ትምህርት በመጀመርያ ነጥብ ላይ ከክርስቶስ መሞት ስለሚለው ነጥብ ለማስተንተን እወዳለሁ፣
    ሞትን የምንመለከትበት አንድ የተሳሳተ ዝንባሌ አለ፣ ሞት ሁላችንን ይመለከታል፣ ጠለቅ ባለ መንገድም ይጠይቀናል በተለይ ወደ እኛ እየተቃረበ በመጣበት ወይንም ሕጻናትን ሲቀዝፍ አንዳንዴም ምንም መከላከያና መጠለያ የሌላቸውን ሲጨርስ እንደ ዕንቅፋትም ይሆነናል፣ በግሌ ብዙ ግዜ የሚያስጨንቀኝ ጉዳይ ያለ እንደሆነ ሕጻናት ለምን ይሰቃያሉ? ሕጻናት ለምን ይሞታሉ? የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው፣ ሞትን የሁሉ ነገር መጨረሻ አድርገን የተረዳን እንደሆነ ሞት ያስፈራል ያሳዝናል ያለንን ሕልምና ዕቅድ ይደመስ ስልናል ያለንን ግኑኝነት ይበጣጥሰዋል የምናደርገው ማንኛው ጉዞ አችንን ያቋርጠዋል፣ ይህ የሚከሰተው የሕይወት ዘመናችን በሁለት ሁኔታዎች ብቻ የታጠረ መሆኑን ማለት በልደትና በሞት መካከል ብቻ የታጠረ መሆኑን ከዚሁ ሕይወት ባሻገር ሌላ አድማስ መኖሩን የማናምን ከሆነ እግዚአብሔር እንደሌለ በማሰብ የምንኖር ከሆንን ነው፣ ይህ ዓይነት አስተሳሰብ በእግዚአብሔር መኖር በማያምን አተይስት ያለ ነው፣ ይህ ዓይነት ሰው ኑሮን እንደ አንድ አጋጣሚ ወይንም ዕድል የሚመለከትና ጉዞ አችን ደግሞ ወደ ባዶሽ ነው የሚል እምነት አለው፣ ነገር አንድ ተግባራዊ የሆነ ሌላ እምነተቢስነትም አለው ይህም ለገዛ ራስ ጥቅም ብቻ እና ለምድራዊ ነገሮች ብቻ መኖር ነው፣ ሞትን በዚሁ ዓይነት አስተሳሰብ የተመለከትን እንደሆነ ስለሞት ከማሰብ መሸሽና እንደሌለ አድርጎ መኖር ነው ይህንን የምናደግበት ምክንያት ደግሞ ፍራቻ እንዳይሰማን ነው፣
    ነገር ግን ይህ ዓይነት የውሸት ኑሮ በሰው ልጅ ልብ ቦታ አያገኝም ምክንያቱም እኛ ሁላችን ያለን ፍላጎት ለዘለዓለም ለመኖር ነው ሁላችን የዘለዓለማዊ ሕይወት ይናፍቀናል፣ የሞት ክርስትያናዊ ትርጉም ምንድር ነው ብለን የጠየቅን እንደሆነ፣ በሕይወት ዘመናችን ያጋጠሙንን አሳዛኝ ሁኔታዎች የወላጆች ወይም የወንድም ወይንም የእኅት እንዲሁም የልጅ ወይንም የቤተሰብ ሞት ሲያጋጥመን ያኔ እንዲህ ባለ የኃዘን ሁኔታ ልባችን ውስጥ የሚሰማን ነገር ሕይወት በእንዲሁ ሊፈጸም የማይሆን ነገር ነው የሚል ስሜት እንዲያው ያ የተቀበልነው መልካም ነገር እርባና ቢስ እንዳልሆነ ይሰማናል፣ በኅልናችን ውስጥ ሕይወታችን በሞት እንደማይጨረሽ የሚነግረን አብሮን የተወለደ ስሜት እናገኛለን፣
    ይህ ለዘለዓለም የመኖር ጥማት በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሙታን እውነተኛና ታማኝ መልስ አገኘ፣ የኢየሱስ ትንሣኤ ከሞት ባሻገር ሕይወት እንዳለ ብቻ አይደለም የሚያረጋግጥልን ነገር ግን የእያንዳንዳችን ሞት ምሥጢርንም ይገልጥላናል፣ ከኢየሱስ ጋር አንድ የሆንን እንደሆነ ለእርሱ ታማኞች ከሆንን የሞት ሽግግርን በተስፋና በተረጋጋ ሁኔታ ለመቀበል እንችላለን፣ ለዚህም ቤተ ክርስትያን “የሞት እርግጠኝነት ቢያሳዝነንም ቅሉ የወደፊቱ ትንሣኤ ሙታን ያጽናነናል” በማለት ትጸልያለች፣ ይህ እጅግ ደስ የሚል የቤተ ክርስትያን ጸሎት ነው፣ እያንዳንዱ ሰው እንደሕይወት ጉዞው ይሞታል፣ ለምሳሌ ያህል የሕይወት ዘመኔ ከጌታ ጋር የተጓዝኩ እንደሆነ ማለትም በጌታ ወደርየለሽ ምሕረት ተማምኜ የተጓዝሁ እንደሆነ በምሞትበት ጊዜ ሁሉንም ነገር በጌታ እጅ በመተው እንደሚቀበለኝ እና ከእርሱ ጋር ፊት ለፊት ቆሜ ገጽታውን እንደምመለከት አውቃለሁ፣ ሊያጋጥመን የሚችለው ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነገር ማለትም ጌታን ፊት ለፊት እያዩ ፍጹም በሆነ ብርሃኑና የተሟላ ፍቅሩ ምሕረቱን እናጣጥማለን፣ ጉዞ አችን እስከዚህ ነው፣ ጌታን ለማየት እንድንበቃ ዘንድ፣
    በዚህ አመለካከት ያ ጌታ የሚያዘን ነገር እውን ለማድረግ ማለትም ሁሌ ዝግጁ ሆነን መጠባበቅ እንዳለብን በማወቅ በዚህ ዓለም ለመኖር የሰጠን የሕይወት ዘመናችን ለመጪው ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመዘጋጀት መሆኑ እናውቃለን፣ ስለዚህ ሞትን ለመጋፈጥ እርግጠኛ መንገድ አለ ይህም ለኢየሱስ ቅርብ በመሆን ለሞት መዘጋጀት ነው፣ የእምነታችን እርግጠኝነትም ይህ ነው፤ በኢየሱስ ጐን በመሆን ለሞት እዝጋጃለሁ፣ እንዴት ሆነን በኢየሱስ አጠገብ ወይም ጎን ለመሆን እንችላለን ያልን እንደሆነ፤ ጸሎት በማዘውተር ምስጢራት በመሳተፍና ምግባረ ሠናይ በመፈጸም ልናደርገው እንችላለን፣ እርሱ በደካማዎችና በኆች እንዳለ እናስታውስ፣ እርሱ ራሱ በወንጌሉ በመጨረሻ ፍርድ ስለሚሆነው ነገር ሲያስተምረን ከድኆችና ችግረኞች ጋር በመሆነ “ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና … ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።” (ማቴ 25፡35-40) ስለዚህ የዘለዓለማዊ ሕይወት እርግጠኛ መንገድ ክርስትያናዊ የፍቅር ሥራን ማዘውተር ነው ያለንን ሁሉ ከወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጋር በመካፈል በተለይ ደግሞ የወንድሞቻችንና የእኅቶቻችን ስጋዊና መንፈሳዊ ችግሮችን ማቃለል ነው፣ የወንድሞቻችንና የእኅቶቻችን ችግሮችን በመካፈል በልቦቻቸው ተስፋ በምንዘራበት ጊዜ ያ ለኛ የተዘጋጀውን መንግሥት ለመውረስ እንደቅድመ ሁኔታ ያገልግለናል፣ የምሕረት ሥራ የሚያደርግ ሁሉ ሞትን አይፈራም፣ ይህንን እሰቡበት፤ የምሕረት ሥራ የሚያደርግ ሁሉ ሞትን አይፈራም፣
    ትስማማላችሁ ወይ እስኪ በኅብረት እንድገመው የምሕረት ሥራ የሚያደርግ ሁሉ ሞትን አይፈራም፤ ለምንድር ነው ሞትን የማይፈራው ያልን እንደሆነ ደግሞ፤ የወንድሙን ቍስል ፊት ለፊት ይገጥመዋል ይህንን ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ያሸንፈዋል፣

የሕይወታችንና የልባችን በር ለትናንሽ ወንድሞቻችን የከፈትን እንደሆነ ያኔ ሞትም ያ በተስፋ የምንጓዝበት የብፅ ዕና አገር ወደሆነችው ለዘለዓለም ከሰማያዊ አባታችንና ከኢየሱስ እንዲሁም ከእመቤታችን ድንግል ማርያምና ከቅዱሳን ለዘለዓለም በደስታ ወደ ምንኖርበት ወደ ሰማያት የሚያደርሰን መንገድ ይሆንልናል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.