2013-11-27 15:59:32

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አፍታ የሰው ነው፣ ጊዜ ግን እግዚአብሔር በጥበቡ የሚያበራው የእርሱ ነው።


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት እንደ ተለመደው ጧት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፦ “አፍታ የሰው ነው፣ ጊዜ ግን እግዚአብሔር በጥበቡ የሚያበራው የእርሱ ነው” በሚል ጥልቅ ሃሳብ ዙሪያ ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከስት፣ ሰው የአፍታ ጌታ ወይንም ገዥ ነኝ ብሎ ገዛ እራሱን ሊያሳምን ይችል ይሆናል፣ ሆኖም ግን የጊዜ ጌታ ክርስቶስ ብቻ መሆኑ በማብራራት፣ አላፊው የአሁኑ ጊዜ ፍሰት ተገንዝበን ለፍጻሜው ግዜ ለመሰናዳት እንዲቻል እያንዳንዱን ተናጥል የሕይወት አፍታ ለማስላትና ወደ እግዚአብሔር ያቀናና ያተኮረ እንዲሆን የሚረዳን በጸሎትና በተስፋ የተሸኘ መሆን እንደሚገባው መክረው፣ ተስፋ የግልም የጋራው ሕይወት መድረሻ የሆነውን ለይቶ ቦግ የሚያደርግ የረዥም መብራት ብርሃን ነው ይኽ ደግሞ የጊዜ ፍጻሜ ማለትም የግዜ ሥነ ፍጻሜ ትርጉም የሚመለከት መሆኑ የዕለቱ ንባበ ወንጌል መሠረት በማድረግ ኢየሱስ ለምእመናን ከሰብአዊ የፍጻሜ ጊዜ ቀድሞ ስለ ሚሆነው በማስመልከት በቤተ መቅደስ ሆኖ እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ የሚያኖር ለቀቢጸ ተስፋነት የሚዳርጉት መከራዎችም ቢያጋጥሙት እንኳ ያለው እርግጠኛነት ከሰጠው ትምህርት ላይ በማስተንተን ቅዱስ አባታችን የሰጡት አስተምህሮ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲገልጥ፣ በዚህ ወደ ፍጻሜ ባቀናው መንገድ የእኛ፣ የእያንዳንዳችን የጠቅላላ ስብአዊ ተራምዶ በአፍታና በጊዜ የሚኖር መሆን እንዳለበት ኢየሱስ ይመክረናል፦ “ክርስቲያን በአፍታና በጊዜ መኖርን የሚያውቅ ነው። አፍታ እያንዳንዳችን አሁን በእጃችን ያለ ነው። ሆኖም አፍታ ጊዜ አይደለም፣ ምክንያቱን አላፊ ነውና፣ አንዳንዴ የአፍታ ጌቶች ሆነን ሊሰማን ይችል ይሆናል የጊዜ ጌታ ሆኖ መሰማት ግን እራስን ማታለል ነው። ምክንያቱም ጊዜ የእኛ አይደለም፣ የእግዚአብሔር ነው፣ አፍታ በእጃችን ነው፣ እንዴት ልንጨብጠው የሚቻለን በነጻነታችን ዘንድ ያለ ነው፣ የአፍታ ገዥ ሆነን ሊሰማን ይችል ይሆናል ነገር ግን የጊዜ ጌታ አንድ ብቻ ነው። እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ኢየሱስ በአፍታ እንዳንታለል የሰጠውን ትምህርት መሠረት በማድረግ፦ እውነተኛ የጊዜ ምልክቶችንና በአሁኑ አፍታዊ ወቅት ልንከተለው የሚገባን መንገድ ለመገንዘብ ለይቶ በትክክል የተገባውን መርጦ የመቻል ጸጋ ያስፈልገናል ይኽ ደግሞ በጸሎት የሚከወን ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ጌታው ለሆነው ጊዜ ጌቶች ሆነን መገኘት ሰብአዊ ባህርይ አይደለም። ስለዚህ ጊዜን የመመልከቱ ብቃት ወይንም ባህርይ ከጌታ የሚሰጥ ጸጋ ነው፣ ይኽ ደግሞ ተስፋ የሚል ነው። ተስፋ አፍታና ጊዜ ጸሎት ማድረግንና ለይቶ ለመገንዘብ ይደግፈናል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የለገሱት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “ክርስቲያን በእያንዳንዷ አፍታ ጌታን መጠባበቅን ያውቃል፣ የአፍታና የጊዜ ሰው የጸሎትና የመገንዘብ የተስፋ ሰው ነው። በዚህ ጉዞ ጌታ ጥበብን ይስጠን በአፍታው ሁነት ለመጸለይና ለይቶ ለመገንዘብ የሚደግፈን ጥበብ ይስጠን፣ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ጊዜን በተስፋ እንዲኖረው ዘንድ ይደግፈን” በማለት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.