2013-11-27 16:14:32

ሶሪያ፦ ስለ ሰላም ጸሎት፣ ዓውደ ጥናትና የትብብር ዘመቻ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በሮማ ጥንታዊው ጎዳና ተብሎ በሚጠራው ክልል በሚገኘው ቅድስት ማርያም ዘ ኦርቶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሶሪያ በጠቅላላ በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲረጋገጥ ብሎም በሶሪያ እስከ አሁን ድረስ ታግተው የሚገኙት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ፓውሎ ዳሊዮና በጠቅላላ ሌሎች ታጋቾች ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ ያቀረበ ለታገቱት ነጻነት በጦርነት ለሚገኙት ሰላም ግጭት በሰላማዊ የውይይት ባህል መፍትሔ ያግኝ የሚል ስለ ሰላም የጸሎት ስርአት መከናወኑ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ይኽ የሮማ ሰበካ የስድተኞች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተለው ጽ/ቤት ስለ ሰላም የጸሎት ቀን የውይይትና የግኑኝነት ባህል ላይ ያነጣጠረው ዓውደ ጥናት ያጠቅላለለው መርሃ ግብር ለመካከለኛው ምስራቅ መስኮት ከተሰኘው ማኅበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ እንደነበር የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ “ሶሪያ፣ ታርክ ጦርነትና ሰው” በሚል ርእስ ሥር የሮማ ሰበካ የተራድኦ ጽ/ቤት ለሶሪያ ሰላም የዘመቻ እቅድ መወጠኑ አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሶሪያ በተቀጣጠለው ግጭት ሳቢያ ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ የሚገመቱ የአገሪቱ ዜጎች ለሞት ሌሎች ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚገመቱትም ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡ ሲር የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.