2013-11-25 16:13:06

ብፁዕ ካርዲናል ማራዲያጋ፦ “አለ ሥነ ምግባር ልማት አይኖርም”


RealAudioMP3 የሆንዱራስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የተጉቺጋልፓ ሊቀ ጳጳስ የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት የሚያቅፈው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ማኅበር ሊቀ መንበር “አለ ሥነ ምግባር ልማት አይኖርም” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ በኤሚ ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ መብቃቱ ሲገለጥ፣ በዚህ መጽሓፍ ዘንድ፦ “ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ እንዲሁም አለማዊነት ትሥሥር ሰብአዊነት የተካነው በማድረግ ኵላዊነት እቅድ እንዲሆን ወቅቱ በዓለምች የሚታየው አቢይ እንቅፋት የሆነው እርሃብና ኢፍትኃዊነት የሚቋጭበት ጊዜ ነው” የሚል ጥልቅ ሃሳብ ማእከል ያደረገ መሆኑ የገለጡት የመጽሓፉ መቅድም ደራሲ የሥነ ኤኮኖሚ ሊቅ ስተፋኖ ዛማኚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሉካ ተንቶሪ ጋር ባሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር ከ 2000 ሺሕ ዓመት በፊት ጀምራ በተለያየ ማኅበርሰብ የሚኖረው ሰው ሁሉ መልካም ኑሮ እንዲዋስለት በኤኮኖሚያዊ ረገድ ያለው ግኑኝነት እንዴት ማደራጀት ይኖርበታል የሚለው ጥያቄ ግምት በመስጠት መልስ ለማቅረብ ጥረት ታደርጋለች፣ መልካም ኑሮ በማለት የክርስትናው ማኅበራዊ ትምህርት የሚገልጠው አስተሳሰብ ብዛት የሚለው አድማስ እርሱም እድገት ላይ ያነጣጠረ ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊና መንፈሳዊ ተገናኝነት አድማስ ላይ ያተኮረም ነው ስለዚህ ብፁዕ ካርዲናል ማራዲያጋ በመጽሐፍ ዘንድ እድገት ኤክኖሚያዊ ማህበራዊ-ሰብአዊና መንፈሳዊ አድማስ የሚከተል መሆኑ ያብራሩታል” ካሉ በኋላ ብፁዕ ካርዲናል ማራዲያጋ በዓለም እየተረጋገጠ ስላለው ዘረፈ ብዙ ትሥሥርነት ችግር ስቃይና ሃብት ለዓለማዊ ትሥሥር እድገት አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል ዓላምዊ ወድማማችነት ትሥሥር በማረጋግጥ መሆኑም በማብራራት፣ ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለማዊነት ትሥሥር ወቅታዊ ሁነት ሳይሆን ከጥንት ጀምራ የተናገረችበት ከመሆኑም ባሻገር፣ ግቡን እንዲመታ እንዴት መመራት እንዳለበትም ታስተምራለች፦ “የዓለም ሃብት ለሁሉም ማዳረስ የሚለው ውሳኔ ለብቻው መፍትሔ አይሆንም፣ ምክንያቱ ማካፈል መመጽወት ቁራሽ እንደ ማቅረብ ተድርጎ ሊታይ ስለ ሚችልም ነው። በምጽዋት እይኖርም፣ ፍትህ በሚለው ኣሴት መመራት አለበት፣ የግብረ ሠናይ ማኅበር መጽዋች ወይንም ቍራሽ አቅራቢ ሳይሆን ነቢያዊ ይዞታ ያለው ነቢያ ድምጽ በመሆን በፍጻሜ የሚሆነው ሁነት ከወዲሁ የሚመሰክር ነው። ይኽ ደግሞ ክርስቲያናዊ ሥልጣኔ የሚባለው ነው። ብፁዕነታቸው ይኸንን ነቢያዊ ብቃት ከጥልቅ እምነት ጋር የተጣመረ መሆኑ በማብራራት፣ ክርስትያን ተስፋ የሚያደርገው እቅዶች ስለ ሚወጥን ሳይሆን ጥንታዊው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ቃል የገባውን ስለ ሚያስታውስና ስለ ሚኖር መሆኑ በመጽሓፉ በማብራት ይመስከሩታል ብለው ብፁዕ ካርዲናል ማራዲያጋ ስለ ፍትህና መደጋገፍ ወይንም ትብብር በተመለከተም፦ “ከዚህ በፊት እርሃብ በመሠረታዊ የተፈጥሮ ሃብት እጥረት አማካይነት የሚኖር ሁነት ተብሎ ነበር የሚገለጠው፣ አሁን ግን ከኤኮኖሚና የገንዘብ ሃብት መዋቅር ጋር ግኑኝነት ያለው ሆኖ፣ ለሁሉም ጥቅም ከመጣር ይልቅ ጠቅላላው ሃብት ዝቅ እድርጎ ከመገመቱ የሚመነጭ ነው። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት እርሃብን ለመዋጋትና ለማጥፋት እነዚህን መዋቅሮች ማረም ያስፈልጋል፣ የኤኮኖሚም ሆነ የፖለቲካ መዋቅሮች ፈጽመው ገለልተኞች አይደልሙ፣ ይኽም የሚከተሉት ሕግና መዋቅሩ ይመሰክረዋል። ማለትም ለአድልዎ የሚመራ ደንብ እንደሚከተሉ ያለው ሓቅ ይመሰክረዋል። ይኽንን ማረም ድኽነት ለመቅረፍ መሠረታዊ መንገድ መከተል ማለት መሆኑ በመጽሓፉ ብፁዕነታቸው በትክክል ያብራሩታል” ሲሉ የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.