2013-11-25 16:09:34

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የንኡሳን ክርስቲያን ማኅበር አባላት ተቀብለው መሪ ቃል ለገሠ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉት 35 የንኡሳን ክርስቲያን ማኅበር አባላት የሚገኙባቸው ከ 47 አገሮች የተውጣጡ በጠቅላላ 500 የሚገመቱ የዚሁ ማኅበር አባላት እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ያካሄዱት የቃለ እግዚአብሔር ስርዓተ አምልኮ ፍጻሜ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር በመገናኘት መሪ ቃል መረከባቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለኔዮ ካተኩመናል ማኅበር አባላት መቼም ቢሆን የዚያ ታማኝና የማይከዳው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእኛ ላይ የሆነው እይታውን አደራ እንዳይዘነጉ የሚያሳስብ ሃሳብ ላያ ያነጣጠረ መሪ ቃል ከመለገሳቸው በፊት ኅዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ምሥጢረ ጥምቀት ለመቀበል ከተዘጋጁት 35 የማህበሩ አባላት ከክርስቶስ ጋር እንዴት እንደ ተገናኙትና በቤተ ክርስቲያን ከቤተ ክርስቲያን ጋር በሕይወታቸው ተቀብለው ምሥጢረ ጥምቀት ለመቀበልና የንኡሳን ክርስቲያን ማኅበር አባላት ለመሆን የወሰዱት ውሳኔ በማስመልከት የተሰጠው ምስክርነት ማዳመጣቸው ማሶቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጣችሁ ብትሆኑም አንድ የሚያደርገን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚለው የእግዚአብሔር ፍላጎት ያለው መሆናችን ነው። ይኽ ደግሞ አንድ ያደርገናል፣ የሚሰማን የሕያው እግዚአብሔር ጥማት የጎደለብን ወይንም በዘልማድ አኗኗር የምንኖረው የረካን ሆነን ቢሰማን እንሳሳታል፣ ዘወትር ኅዳሴ የሚጠይቅ ሕይወት ነው። ስለ ኢየሱስ ከተናገሩዋችሁ ከመሰከሩላችሁ ኢየሱስን አውቃችሁ፣ ነገር ግን የተነገራችሁ ብቻ ሳይሆን እናንተም በሕይወታቸው ተመክሮ በማድረግ ከቀሰማችሁት ፍቅር አማካኝነት በእግዚአብሔር ጸጋ ምሥጢረ ጥምቀት ለመቀበል የወሰናችሁ ናችሁ፣ የከበባችሁ በዙሪያችሁ የሚለፈለፈውን ድምጽ እምቢ በማለት የዚያ ብቸኛው የሕይወታችን ትርጉም የሆነው የጌታ ድምጽ በመለየትና በማዳመጥ ምሥጢረ ጥምቀት ለመቀበል እነሆኝ ያላችሁ ናችሁ” እንዳሉም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አስታወቁ።
እነዚህ 35 የንኡሳን ክርስቲያን ማኅበር አባላት እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የእምነት ዓመት መዝጊያ በዓለ ዕለት እምነትን በመቀበል በእምነት በር ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት መወሰናቸው በቤተ ክርስቲያን እምነትን ተቀብለው ለመኖር የወሰዱት ውሳኔ ጸጋነቱን የሚያመለክት ቅዱስ አጋጣሚ መሆኑ ማሶቲ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.