2013-11-25 16:10:11

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለአረጋውያን ኅሙማን የኅክምና እንክብካቤ ለዝምታ ለስቃይ ሥፍራ ሳይሆን በሰብአዊ ክብር ጥበቃ ሃብታም ሥፍራ ይሁን


RealAudioMP3 ከ 57 አገሮች የተወጣጡ በጠቅላላ 700 ተጋባእያን ቤተ ክርስቲያን ለአረጋውያን ህሙማን አገልግሎት፣ በአእምሮ መሰናከል በሽታ የተጠቁትን መንከባከብና ተገቢ ሕክምና መስጠት” በሚል ርእስ ሥር ለጉባኤ የጠራው ጳጳሳዊ የጤና ጥበቃና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ተንከባካቢ ምክር ቤት አዘጋጅነት እ.ኤ.አ. ከህዳር 21 ቀን እስከ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደው 28ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት፣ ተጋባእያኑ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራችነስኮ በጳውሎስ ስድስተስኛ የጉባኤ አደራሽ ተጋናኝተው መሪ ቃል ተለግሶላቸው መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።
ቤተ ክርስቲያን አረጋውያን ለኅብረተሰብ አስፈላጊነታቸው ግዴታዊ መሆኑ በቃልና በተግባር ለኅብረሰብ አብነት ሆና መገኘት እንደሚጠበቅባት ያሳሰበው ዛሬም እንደ ጥንቱ አረጋውያን በቤተ ክርስቲያን ዋና ተወናያን ናቸው የሚለው ጥልቅ ሃሳብ አዘል የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምዕዳን፦ “አረጋውያን የሕይወት ተዘክሮና ጥበብ ለሌሎች ለማውርስ ለማስተላለፍ በውስጣቸው ይዘውት የሚጓዙ በመሆናቸው በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ሙሉ ሲታፌ ያላቸው ናቸው፣ የሰው ልጅ ሕይወት ከማንኛው የአድልዎ ራእይ ውጭ በእግዚአብሔር እይታ ዘወትር ክብር አቀብ ነው። በስነ ሕይወት ስነ ሕክምና የሚሰጠው የቆየው የጤና ጥበቃ እንክብካቤ በሰብአዊ ክብር ነጻነት ጥበቃ ሃብታም የሆነ ሥፍራ እንጂ የዝምታ ስቃይን ሰቆቃ ሥፍራ መሆን የለበትም፣ ምክንያቱም ዝምታው ወደ ስቃይ ሊለወጥ ስለ ሚችልም ነው። በጤና ጥበቃ የሕክምና እንክብካቤ የሚደረግላቸው ኅሙማን ሌላው በሚያቀርበው መዘጋትና ዝምታ ተከበው ሲኖሩ ይታያል” ካሉ በኋላ በመቀጠል፦ “አረጋውያን በቤተ ክርስቲያን በቤተሰቦቻቸው በሚሳተፉበት በተለያየ ቦታ ክርስቶስንና ወንጌሉን ለማሳወቅ የጌታ ምስክርኖች ሆነው ለመኖር የተጠሩ ለመሆናቸው ጌታችን ኢየሱስ በሕጻንነቱ በቤተ መቅደስ ለይተው ያወቅቱ ሁለት አዛውንቶ እነርሱም በደስታና በተስፋ እንዳበሰሩት ያረጋግጥልናል ይኸንን መዘንጋት አይገባም። ስለዚህ አረጋውያን አዛውንቶች በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በሙላት ለመሳተፍ የተጠሩና የዚህ ተልእኮ ቀንደኛ ተወናያን ናቸው” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተጋባእያኑ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ጳጳሳዊ የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎችና ኅሙማን ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ የመሩት የጸሎትና የአስተንትኖ መርሃ ግብር መከናወኑ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.