2013-11-22 14:36:55

የብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ አዲስ መጽሐፍ
“አዲስ የብሥራት ቃል ላንተ”፦ ቃለ እግዚአብሔር፣ የብርሃን ምሥጢር ማእከል


RealAudioMP3 የአገረ ቫቲካን ኅየንተ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ሊቀ ካህናት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ “አዲስ የብሥራት ቃል ላንተ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሐፍ በቫቲካን ማተሚያ ቤትና በኤለዲቺ ማተሚያ ቤቶች ታትሞ ትላትና ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕነታቸው በዕለተ ሰንበትና በዓበትይ በዓላት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴዎች ያሰሙት ስብከት በማሰባሰብ የደረሱት መጽሐፍ ብዕር የወለደው ሳይሆን ከልብና ከጸሎት የመነጩ ቃላቶች ያካተተ መሆኑ መጽሓፉን ለንባብ ለማብቃት በተካሄደው ጉባኤ እንደተሰመረበትም የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኤልቪራ ራጎስታ ገለጡ።
ብፁዕ ካርዲላን አንጀሎ ኮማስትሪ በዚህ አጋጣሚም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ስለ እግዚአብሔር ስለ ቃለ እግዚአብሔር የሚያወሳ መጽሐፍ ጉልበትን አጥፎ ከመንበርከክ የሚመነጭ ነው። የገበያ ምርት አይደለም፣ የእግዚአብሔር ቃል ምሥጢረ ብርሃን ነው፣ ስለዚህ ይኽ ብርሃን በውስጣችን እንዲገባ የልብ በር መክፈት የሚለው ቅድመ ሁኔታ ይጠይቃል፣ ስለዚህ ብርሃኑን ተቀብሎ ለማስፋፋት ጉልበትን አጥፎ መንብርከክ ያስፈልጋል ካሉ በኋላ በምንኖርበት ዓለም የመልካም ፈቃድ፣ የቅንነት የየዋህነት የምህረት መብራት የተቃጠለበት ሆኖ ነው የሚታየው፣ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ይኸንን የጠፋውና የተቃጠለው መብራት ዳግም ህያው እንዲሆን ያደርጋል፣ የእግዚአብሔር ቃል፣ መልካም ውብ ደስተኛ ሕይወት እንድንጎናጸፍ ያደርገናል፣ የጠፋው ብርሃናችን ዳግም አድሶ የሚያበራ ነው ብለዋል።
በዚህ አጋጣሚም ብፁዕነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1979 ዓ.ም. እናት ብፅዕት ተረዛ ዘካልኵታ የሰላም ኖበል ሽልማት እንደ ተቀበሉ ከተለያዩ ዓለም ለተወጣጡ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው እንዳበቁ፣ እንድ ጋዜጠኛ እርስዎ ማድረ ተረዛ 70 ዓመት እድሜ አገባደዋል፣ ሌሎችን በመደገፍ ስለ ሌሎች በማሰብ የኖሩት ዕድሜም ነው፣ ሆኖም ግን ዓለም አሁንም አልተለወጠም ስለዚህ መልካም እየሠሩ መኖር ምን ጥቅም አለው ዓለም እንደሆነ እንደምናየው ነው፣ በማለት አንድ ጋዜጠኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ልጄ እኔ ዓለምን ለመለወጥ የሚል ፍላጎትም ሆኖ አቅርቦቱ የለኝም፣ ዓለንም ለመለወጥ ይገባኛል የሚል ትዕቢት የለኝም፣ እኔ የምፈልገው በውኃ ላይ የእግዚአብሔርን ምስል የሚያንጸባርቅ ንጹህ ጠብታ ሆኜ ለመገኘት ነው። ስለዚህ ይህ ፍላጎት ትንሽ ይምስልሃልን፣ አንተም ይላሉ ለጠየቃችው ጋዜጠኛ ይኽ ንጹሕ የእግዚአብሔር ምስል የሚንጸባረቅ ንፁዕ ጠብታ ለመሆን ሞክር ሁለት እንሆናለ፣ ልጆችና ሚስት አለህ ወይ ብለው ይጠይቁትን እርሱም አዎ ሶስት ልጆፍ አሉኝ ሲል፣ ማድረ ተረዛም እንተም ለልጆችህን የእግዚአብሔር ምስል የሚንጸበረቅበት ንጹሕ ጠብታ እንዲሆኑ አስተምራቸው ሁለት የነበርን ስድስት እንሆናለን፣ ንጹሕ ጠብታ የበዛን እንደሆን የቆሸሸውን ውቅያኖስ እናነጻለን ሲሉ የሰጡት መልስ ብፁዕ ካርዲናል ኮማስትሪ አስታውሰው ማድረ ተረዛ የእግዚአብሔር ቃል የሚንጸባረቅባቸው እናት ናቸው፣ የእግዚአብሔር ቃል ማንጸባር እንድንችል ለዚህ መጠራታቸው የሚያወሳ ጸሎትና እምነት የወለደው መጽሓፍ ነው።
የጌታ ቃል በሕይወትህ እንዲገባ ስትፈቅድ የእርሱ ምርህረት እንደሚያስፈልግህ ጠንቅቀህ ትገነዘባለህ፣ እንደ አብነትም ቅዱስ ጴጥሮስን ጠቅሰው፣ የእግዚአብሔር ቃል መቀበል ምህረቱን ለመለመና ለመለወጥ ብሎም ቃሉን ለማበሰር ያነቃቃል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.