2013-11-22 14:32:58

ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ፦ በአእምሮ መሰናከል በሽታ የተጠቁትን መንከባከብ


RealAudioMP3 ጳጳሳዊ የጤና ጥበቃና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ተንከባካቢ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከህዳር 21 ቀን እስከ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ ከ 57 አገሮች የተወጣጡ በጠቅላላ 700 ተጋባእያን የሚሳተፉበት “ቤተ ክርስቲያን ለአረጋውያን ህሙማን አገልግሎት፣ በአእምሮ መሰናከል በሽታ የተጠቁትን መንከባከብና ተገቢ ሕክምና መስጠት” በሚል ርእስ ሥር የተመራው 28ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የዚህ 28ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተጋባእያን በሙሉ ከቅዱስ አባታችን መሪ ቃል ለመቀበል በሚያካሂዱት ግኑኝነት የሚጠናቀቅ መሆኑ የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዚሞውስኪ እ.ኤ.አ. ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይኽ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በአዲሱ የሲኖዶስ አዳራሽ ዓውደ ጥናቱን ለመክፈት ያረገው መስዋተ ቅዳሴ የመሩና ጉባኤው ባሰሙት ንግግር ያስጀመሩት ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ፦ የጥፋጭ ሞት ምርጫ ወይንም ውሳኔ የዓለማችን አቢይ ሓፍረት ነው” በሚለው ሃሳብ ላይ በማተኮር የማኅበራዊ ለውጥ ክስተቶች የበለጸገው ሃብታሙ ዓለም በእርጅና የተጠቃ ማለትም እኔነት ማእከል ያደረገ ባህል በመሆኑ በሚያስከትለው የወሊድ ቁጥር ማነስ ምክንያት በእድሜ የገፉው ሕዝብ የሚኖርበት የቤተሰብ ዋነኛው ትርጉም እያጣ ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ የታመመው ለገዛ እራሱ የሚተውበት በእድሜ የገፋው ተገሎ በአረጋውያን ማደሪያ ማእከሎች ውስጥ ትቶ መኖር የተስፋፋበት፣ ተነጥሎ የሚኖረው አዛውንት ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቃው ዜጋ የቤተሰብ እንክብካቤ ማጣት ለሞት ባህል ምክንያት እየሆነ ጣፋጭ ሞት የሚል ውሳኔ እያጋባ ከዚህ ዓለም በሞት የመለየት ምርጫ እንደ መፍትሄ አድርጎ ለመኖር ምርጫ እያስገደደ መሆኑ ገልጠው በእውነቱ የጣፋጭ ሞት ውሳኔ የዓለማችን አቢይ አፍረት ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ። በእድሜ መግፋት ከጥበብ ጋር የተያያዘ ሆኖ አዛውንት ጥበብ የተካነ ነው ተብሎ ይገለጥ እንደነበር ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ፣ በአሁኑ ወቅት ሸክም የውድቀት ምልክት ተደርጎ እየታየ፣ ሰብአዊው ትርጉሙ አምራችነት ከሚለው አመለካከት ጋር በማጣመሩ ምክንያት፣ እድሜ መግፋት ውድቀት እንደሆተ ተድርጎ እንዲኖር እያስገደደ ነው። ስለዚህ አዛውንቱ እኔ በኅብረተሰብ ዘንድ ቦታ አለኝ ወይ፣ በማለት ጥቅምና አስተዋጽኦ መሠረት ገዛ እራሱ እንዲመዝን መዳረጉንም ገልጠው፣ ሸክም ነኝ ወደ ሚለው የማጠቃለያ ሃሳብ በማዝገም ጣፋጭ ሞት መፍሔ ነው ለሚለው ለሞት ባህል አሜን እንዲል ያደርገዋል በመቀጠልም ብፁዕነታቸው፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊን በማስታወስም በክርስቶስ ሕይወት ሱታፌ የሕይወት ትርጉም ነው። በክርስቶስ ሕይወት ሱታፌ በድህነት እቅድ መሳተፍ ማለት ነው። ስቃይን በእምነት መኖር የላቀው የወንጌል አብሳሪነት ተግባር ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ገለጡ።
ከባድ ስቃይና ሕመም መሠረታዊ የሥነ ሕልውና ጥያቄ ነው። ስለዚህ ወደ ተስፋ መቍረጥ ወይንም ወደ ጌታ በጥልቅ ለመቅረብ ይደግፈናል፣ ስለዚህ የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎችና በተለያዩ የሕክምና ቤቶች የሚገኙት መንፈሳዊ መሪዎች ካህናት የተሸከሙት ኃላፊነት ከዚህ አኳያ ቀላል አንዳልሆነ ለመረዳቱ አያዳግትም፣ በጠና ለተማመውና ለአረጋውያን ቅርብ መሆን ለባለንጀራህና ለጌታ ቅርብ ትሆን ዘንድ ያነቃቃል፣ ከትዕግሥት ወደ ተስፋ የሚመራ ሕይወት እንዲኖር ይደግፋል፣ ካሉ በኋላ ምሥጢረ ንስኃና ቅብአተ ኅሙማን ላይ በማተኮርም ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ሥልጣናዊ መሪ ቃል ለማብራራት በእድሜ የገፋው ወይንም ገና መድሃኒት ባልተገኘለት የተጠቃው ሰው በአሁኑ ወቅት ለፈውስ ሙከራ አለ ገደብ ለሚለው ውሳኔ ወይንም ጣፋጭ ሞት ለሚለው አደጋ ተጋልጦ ይገኛል፣ ቤተ ክርስቲያን እነዚህ ሁለት መንገዶች ሰብአዊው ፍጡር ወደ ፍጻሜው መቃረቡ ላይ ያተኮረ ለምድራዊ ሕይወት ፍጻሜ በተስፋ ቃል የመሸኘት ድጋፍ ማቅረብ በሚል ውሳኔዋ አማካኝነት የሞት ባህል ትቃወማለች፣ ይኽ ደግሞ የገዳይና ተገዳይ አደጋ ያስወግዳል እንዳሉ ዲኒኒ አመለከቱ።







All the contents on this site are copyrighted ©.