2013-11-20 15:35:53

ጋና፦ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል


በጋና በመከሰት ላይ ያለው ኅብረሰብአዊ ለውጥ ግምት በመስጠት በአገሪቱ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አስፈላጊ መሆኑ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከህዳር 8 ቀን እስከ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ፍጻሜ ባወጣው የመግለጫ ሰነድ ተመልክቶ እንደሚገኝ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ጋና ሰላም የሰፈነባት ያላት ኤኮኖሚ ጎልማሳና ሃይማኖተኛ አገር መሆንዋ ብፁዓን ጳጳሳቱ በፍጻሜው የመግለጫ ሰነድ በማስታወስ፣ ይኸንን ሁሉ በማመዛዘንና በአገሪቱ እየተስከሰተ ያለው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ጥብቅ ግኑኝነትና መለወጥን የማይደገፍ ማኅብራዊ ኤኮኖሚያዊ ባህላዊ ለውጥ ግምት በመስጠት የዓለማውያን ምዕመናን ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚጠይቅ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው እንዳሉ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ በአገሪቱ ባህል የነበረው እርሱም አረጋውያንን የመንከባከብ የማክበር እንግዳ የመቀበል ድኻን የመርዳት የአሳቢነትና ሙስናና ምግባረ ብልሽት እምቢ የሚል እሴቶች ቀስ በቀስ እየተዘነጋ እኔነትና ስግብግብነት የሚል አዝማሚያ በመስፋፋት ላይ በመሆኑ፣ ይኸንን እሴቶችን የሚያገል ጎጂ ባህል ለማስወገድ የሚያነቃቃ የሚመራ የአገሪቱ አወንታዊ ባህል ቀጣይነት እንዲኖረው የሚደግፍ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ መርሃ ግብር ያለው አስፍፈላጊነት እንዳሰመሩበት አስታውቀዋል።
ሕግ በመጣስ በምግባረ ብልሽት በማታለል በማጭበርበር አቋራጭ መንገድ በመከተል የገንዘብ ሃብት ለማካበት የሚደረገው ሩጫ የቤተሰብ ክቡር ዋጋ ግድ ላለ መስጠት ለሚከጅል ልማድ እጅ መስጠት፣ የድኾችን ስቃይና መክራ ማባባስ መሆኑና ይኸንን ሁኔታ ለመቃወም ብሎም ኅብረሰብ የሚያዛባ ባህል ለማረም የሚደግፍ የሚያነቃቃ የዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አስፈላጊ ነው በማለት፣ ሁሉም ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም እንዲያተኵር በማሳሰብ ብፁዓን ጳጳሳቱ ለአገራቸውና ለመንግስታቸው ለሕዝባቸው ጭምር ከመጸለይ እንደማይቆጠቡ ማረጋገጣቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.