2013-11-20 15:33:12

ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ፦ በአእምሮ መሰናከል በሽታ የተጠቁትን መንከባከብ


ጳጳሳዊ የጤና ጥበቃና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ተንከባካቢ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከህዳር 21 ቀን እስከ ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚጠናቀው ከ 57 አገሮች የተወጣጡ በጠቅላላ 700 ተጋባእያን የሚሳተፉበት “ቤተ ክርስቲያን ለአረጋውያን ህሙማን አገልግሎት፣ በአእምሮ መሰናከል በሽታ የተጠቁትን መንከባከብና ተገቢ ሕክምና መስጠት” በሚል ርእስ ሥር የተመራው 28ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እንደሚያካሂድ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የዚህ 28ኛው ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተጋባእያን በሙሉ ከቅዱስ አባታችን መሪ ቃል ለመቀበል በሚያካሂዱት ግኑኝነት የሚጠናቀቅ መሆኑ የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዝግይሙንት ዚሞውስኪ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታውቀዋል።
ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በዓለም በአእምሮ መሰናከል በሽታ የተጠቁት ብዛት 35 ሚሊዮን ሲሆን በዚሁ በሽታ ሳቢያ በአንድ ዓመት ውስጥ 8 ሚሊዮን የሚገመቱት ህሙማን የሞት አደጋ እንደሚያጋጥማቸው ይህ አደገኛው በሽታ ቀስ በቀስ የአእምሮ ሙሉ ብቃት በማኮላሸት ለሞት የሚዳርግ መሆኑና፣ ብዙውን ጊዜ በእድሜ የገፉት አረጋውያን የሚያጠቃ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምንኖርበት ማሕበረሰብ የሚያገል ሳይሆን በተለይ በጠና የታመሙትን በጠና ድክነት የተጠቁትን በእቅፉ የሚያኖር የሚያስብ የሚንከባከብ መሆን አለበት በማለት ያሰሙት ጥሪ ብፁዕነታቸው አስታውሰው፦ የትም ይሁን በማንኛውም ወቅትና ሥፍራ ለሕይወት መቆም ነው። ከአምራቹ የኅብረተሰብ ክፍል ውጭ የሆነው ኢአምራች ለመሆን በተለያየ ምክንያት ተገዶ ጥገኛ የሆነው ሰው ተነጥሎ እንዲኖር የሚገፋፋው ባህል እንዲሁም ጽንስ በማስወረድ ብሎም ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቃውን የኅብረተሰብ ክፍል በጣፋጭ ሞት ለሞት የሚዳርግ ስልት አማካይነት የሚፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር የሚያስፋፋው የሞት ባህል በሕይወት ባህል ለማግለል ተግቶ መገኘት አስፈላጊ ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።
“በወጣቱና በአዛውንት (አረጋውያን) የኅብረተሰብ ክፍል መካከል ትብብርና መደጋገፍ መቀራረብ እንዲኖር ቤተ ክርስቲያን በዚሁ ዘርፍ በምታቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካይነት የአግላይነት ባህል በመዋጋት፣ ለዚህ ባህል መሠረትም ቤተሰብ ነው። ስለዚህ ሁሉም የቤተሰብ አባል አለ ምንም ሁነት የቤተሰብ አባልነት መብቱ ተጠብቆለት ተከብሮ እንዲኖርና ፍጥረት በትርፍ ማካበት ሥነ አመክንዮ ሥር መመዘን መለካት አይገባም፣ ስለዚህ አለ ምንም ጥቅማ ጥቅም በነጻ ማፍቀር፣ በእድሜ መግፋት ምክንያት በሚያጋጥመው የሕይወት ኮሳሳነት ሕይወት ያለው የላቀው ክብሩ ማሳነስ ወይንም ይህ የላቀው ክብር እንደሌለው አድርጎ መመልከቱ የሞት ባህል ነው” እንዳሉ ጂሶቲ አስታውቀዋል።
በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የኢጣሊያ የአእምሮ ስንኩላን ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር ሊቀ መንበር የሥነ ህክምና ሊቅ ጋብሬላ ሳልቪኒ ፖሮ፦ “የምንኖርበት ዓለም ሚዛን አምራችነት ወይንም በኤኮኖሚ ረገድ የተሳትፎ ብቃት የሚል በመሆኑ ምክንያት በተለያየ በሽታ በተለይ ደግሞ ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቃው የማግለል ባህል መዋጋት የሁሉም ኃላፊነት ነው። ስለዚህ ማንም በማንኛውም ዓይነት በሽታም ይሁን የኤክኖሚ ደረጃ ይገኝ መቼም ቢሆን ሰው ነው። ስለዚህ ሰብአዊ ክብሩ ባህርይ እንጂ አጋጣሚ አይደለም” እንዳሉ የገለጡት ጂስቶ አያይዘው የኢጣልያ የሥነ አእምሮ ስንኩልነት በሽታ ሊቅ ጋብሪኤለ ካርቦነ በበኩላቸውም፦ “የአእምሮ መሰንከል በሽታ ነው። ስለዚህ ከቤተሰብ ጀምሮ ብሎም በኅብረተሰብና በሁሉም የህክምን መስጫ ጣቢያዎች ይኽ ግንዛቤ እንዲኖርና የመንከባከብ ባህል በማስፋፋቱ መርሃ ግብር ሁሉም መትጋት ይኖርበታል” እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.