2013-11-20 15:29:41

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በኢጣሊያ ለሰበካ ለላቲና አዲስ ጳጳስ ሰየሙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ላቲና ተራቺና ሰዘና ፕሪቨርኖ ከተሞች ለሚያጠቃልለው ሰበካ ጳጳስ እንዲሆኑ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታን መሰየማቸው የቅድስት መንበር በግለጫ አስታወቀ።
ብፁዕ አቡነ ክሮቻታ በኢጣሊያ ማዛራ ደል ቫሎ ሰበካ እ.ኤ.አ. መጋቢት 16 ቀን 1953 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን፣ በማዛራ ደል ቫሎ በወቅቱ በነበረው ንኡስ ዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ገብተው እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸው በማጠናቀቅ በሮማ ጳጳሳዊ ግረጐሪያና መንበረ ጥበብ የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ትምህራታቸው አጠናቀው እ.ኤ.አ. ከ 1497 እስከ 1548 ዓ.ም. በሕይወት የነበረው ኢጣሊያዊ የቋንቋ ባህልና እድገት ተማራማሪ የሥነ ጥንታዊነትና የፍልስፍና ሊቅ የግሪክና እብራይስጥ ቋንቋ ተማራማሪ በትረንቶ ጉባኤ የተሳተፈው አጎስጢኖስ ስተውኮ ምርምር በጥልቀት በማጤን “ክርስትናና ቲዮሎጊያ በአቆስጢኖስ ስተውኮ” የሚል ጥልቅ የማስመረቂያ አጽሓፋቸው በማቅረብ በከፍተኛ ደረጃ በቲዮሎጊያ ሊቅነት ማስመስከራቸው ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ብፅዕነታቸው የቲዮሎጊያ ሥነ መሠረት ለቲዮሎጊያ መናብርተ ጥበብ የሚያገለግል ቤተ ክርስቲያን በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. በፒየመ ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ የበቃው መጽሓፍ የደረሱ በፓሌርሞ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ የሚታተመው ቲዮሎጊያ በተሰየመው መጽሔት የተለያዩ የቲዮሎጊያና ፍልስፍና እንዲሁም ሥነ ቤተ ክርስቲያን በተመለከቱ የጥናት ጽሑፎች ያሳተሙ በክርስትናና በሌሎች ሃይማኖቶች መካከል ስለ ሚከናወኑት ግኑኝነቶች ጥልቅ ጥናት ያካሄዱ መሆናቸው ጠቅሶ እ.ኤ.አ. ሰነ 29 ቀን 1979 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት ከተቀበሉ በኋላ እ.ኤ.አ. ከ 1983 እስከ 1986 ዓ.ም. በማዛራ ደል ቫሎ ሰበካ የትምህርተ ክርስቶስ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ተጠሪ፣ ከ 1989 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. የማርሳላ እናት ቤተ ክርስቲያን ቆሞስና ሊቀ ካህናት፣ የካቶሊካዊ ተግባር መንፈሳዊ መሪ ረዳት፣ በሲቺሊያ ክፍለ ሃገር የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መምህር በማዛራ ደ ቫሎ የሥነ ሃይማኖት ተቋም የቲዮሎጊያ ሥነ መሠረትና የሥነ ክርስቶስ መምህር በመሆን በማገልገል ላይ እያሉ፣ እ.ኤ.አ. ሓምሌ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የኖቶ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ማዕርገ ጵጵስና እንደተቀብለው እ.ኤ.አ. መስከረ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ እንዲሆኑ መመረጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
ብፁዕነታቸው የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚና ቅድስት ካተሪና ዘሲየና ሃይማኖታዊ ማኅበር ሊቀ መንበር በኢጣሊያ ተካሂዶ በነበረው አምስተኛው ብሔራዊ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አመራር ኮሚቴ አባል በመሆን እንዳገለገሉም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቲዮሎጊያ ሥነ ግብረ ገብ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ኦልሶን በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የፎርት ዎርዝ ሰበካ ጳጳሳ እንዲሆኑ እንደሰየሙዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።







All the contents on this site are copyrighted ©.