2013-11-18 13:34:12

የር.ሊ.ጳ የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ም እመናን ጋር የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት በዕለቱ ቃለ ወንጌል ተመርኵዘው “በሃይማኖታዊ ስደቶች ስለሚሰቃዩ ክርስትያኖች እንጸልይ! የውሸት ነቢያት እንዳያሳስቱንም እንጠቀቅ” ሲሉ ያለነው ጊዜ የምስክነትና እስከ መጨረሻ መታገስ የሚጠይቀበት መሆኑን አሳስበዋል፣ ያለነው ጊዜ ቢከብድም በብርታትና በተስፋ መጋፈጥ እንዳለብን የጠሩ ቅዱስነታቸው ጸልተ መል አከ እግዚአብሔር ካሳረጉ በኋላ መድኃኒተ ነፍስ ያሉት መቍጠርያና የመለኮታዊ ምሕረት ምስል ያለበት ትንሽ ስጦታ በአደባባዩ ለተገኙ ሁሉ እንዲሚታደል ከገለጡ በኋላ ለነፍሳችን መንፈሳዊ ጤንነት እንድናገኝ በየዕለቱ በግልና በቤተ ሰብ ጸሎተ መቍጠርያን በመድገምና በመለኮታዊው ምሕረት መማጠን እንዳለብን አሳስበዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓት ትናንትና የተነበበው የወንጌል ክፍል ከሉቃስ የተወሰደ ሲሆን ስለኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መውደምና ስለ የዓለም ዕልቂት የሚናገር ከምዕራፍ 21 “አንዳንዶቹም ስለ መቅደስ በመልካም ድንጋይና በተሰጠው ሽልማት እንዳጌጠ ሲነጋገሩ። ይህማ የምታዩት ሁሉ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ የማይቀርበት ዘመን ይመጣል አለ። እነርሱም። መምህር ሆይ፥ እንግዲህ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ይሆን ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ጠየቁት። እንዲህም አለ። እንዳትስቱ ተጠንቀቁ፤ ብዙዎች። እኔ ነኝ፥ ዘመኑም ቀርቦአል እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ እነርሱን ተከትላችሁ አትሂዱ። ጦርንና ሁከትንም በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ አስቀድሞ ይሆን ዘንድ ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም። በዚያን ጊዜ እንዲህ አላቸው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ ታላቅም የምድር መናወጥና በልዩ ልዩ ስፍራ ቸነፈር ራብም ይሆናል፤ የሚያስፈራም ነገር ከሰማይም ታላቅ ምልክት ይሆናል። ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤ ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል። ሰለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤ ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና። ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤ በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤ በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ።” የሚል ነበር፣ ቅዱስነታቸው እነኚህ ቃላት ዛሬም ቢሆን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለምንኖር እንደሚመለከትና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገን እንዲህ ሲሉ አሳስበዋል፣
“ዛሬም ቢሆን ኢየሱስን በመተካት የዚህ ዓለም መሪዎች አስመሳይ ቅዱሳኖች ጠንቋዮችም ሳይቀሩ የሰው ልጅ ልብና አእምሮ ወደገዛራሳቸው ለመሳብ የሚሞክሩ የውሸት አዳኞች አሉ፣ በተለይ ደግሞ ወጣቶች በዚሁ ወጥመድ ለማግባት የሚታገሉ አሉ፣ ለዚህም ነው ኢየሱስ አትከተልዋቸው በማለት የሚያስጠነቅቀን፣ ይህ ብቻ ሳይሆን ጌታ በውግያዎችና በአብዮቶች እንዳንደነግጥ በማሳሰብ ይረዳናል እንዲያው የተፈጥሮ አደጋዎችም ይሁን ወረርሽኝና የተለያዩ ሕመሞች ቢመጡም ኢየሱስ ከየውሸት ነቢያትና የውሸት የኅልቀተ ዓለም ራእዮች ነጻ ያወጠናል፣ እንደ ክርስትያኖችና እንደቤተ ክርስትያን መጠን ስለኢየሱስ ብዙ ስቃይና መከራ እንዲሁም ስደት እንደሚያጋጥመን አስቀድሞ ነግሮናል፣ ሁል ግዜ ደግሞ በእግዚአብሔር እጆች እንዳለን ይገልጥልናል፣ በእምነታችን ምክንያትና ስለወንጌል የምንቀበላቸው ጥላታዎች የምስክርነት ዕድል የሚሰጡን ሆነው በበለጠው ወደ እርሱ እንድንጠጋና ሁሉን በእርሱ እጅ እንድንተው በመንፈሱና በጸጋው ኃይል እንድንጠጋ ዕድል ይሰጠናል፣
“በእምነታቸው ምክንያት በስደት የሚሰቃዩ ወንድማሞቻችንና እኅቶቻችን ክርስትያኖችን እናስታውስ፣ እጅግ ብዙ ክርስትያኖች እየተሰቃዩ ነው ያሉት፣ እንዲያው ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን ስደት የባሰ ይመስላል፣ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ነው ያለው፣ እኛም በጸሎትና በፍቅራችን እንድንሸኛቸው ይሁን፣ በሚያሳዩት ብርታትና በሚሰጡት ምስክርነት እናደንቃቸዋለን፣ እነኚህ ወንድማሞቻችንና እኅቶቻችን የሆኑ ክርስትያኖች በተለያዩ ክፍለ ዓለማት ለኢየሱስ ታማኝ በመሆናቸው ነው የሚሳቀዩት ያሉት፣ ከልባችን የተነሳ ሰላምታ እናቅርብላቸው ሲሉ ትምህርታቸውን ከደመደሙና የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ካሳረጉ በኋላ የነፍስ መንፈሳዊ መድኃኒት ያሉትን ጸሎተ መቍጠርያና የመለኮታዊ ምሕረት መቍጠርያ ለመድገም የሚቻልበትን መቍጠርያ ለህዝብ እንደሚታደልና እንዲጠቀሙት በማሳሰብ እንዲህ ብለዋል፣ “አንዲት የመቍጠርያ ጸሎት ማሳረጊያ መቍጠርያ አለች በዚህ መቍጠርያ ለእመቤታችን በጸሎተ መቍጠርያ ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስትቶስ ደግሞ በመለኮታዊ ምሕረት መቍጠርያ በማሳረግ ልንለምናቸው እንችላለን፣
ይህ ለነፍሳችን መንፈሳዊ እርዳታ የሚሰጥና ፍቅሩንና ምሕረቱን እንዲሁም ወንድማማነትን ለሁሉ ለማዳረስ ይጠቅመናል፣ እንድትወስዱት ይሁን አትርሱት ይጠቅማችኋል፣ የልብ መድኃኒት ይገኝበታል ለነፍሳችንም ይሁን ለመላው ሕይወታችን መድኃኒት ነውና ሲሉ ከተናገሩ በኋላ በአደባብዩ ለነበሩ ሁሉ ታደለ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.