2013-11-16 14:59:42

ር.ሊ.ጳ ፍራንሲስ የጣልያን ቤተ መንግስት ይፋ ጉብኝት ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና ረፋድ ላይ ኲሪናለ ማለት ጣልያን ቤተ መንግስትን ይፋ ጐብኝተዋል ። ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ እንደተሰየሙ ቤተ መንግስት ጣልያን ሲጐበኙ ይህ የመጀመርያ ግዝያቸው ናቸው ።ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቤተ መንግስት ጣልያን እንደደረሱ የጣልያን መንግስት ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ እና የመንግስት ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።ርእሰ ብሔር ናፖሊታኖ ለፓፓ ፍራንቸስኮ እንኳን የደህና መጡ ንግግር አድርገዋል።ጉብኝቱ በደስታ እንደሚመልከቱት እና ሐዋርያዊ እረኝነታቸው የሚደነቅ እና የሚመስገን እንደሆነ ጠቁመው በጣልያን መንግስት እና በቅድስት መንበር መካከል ያለው ግንኙነት መልካም መሆኑ አስገንዝበዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ለተደረገላቸው ግሩም አቀባበል አመስገነው ርእሰ ብሔሩ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ያላቸውን መልካም አስተያየት አምስግነዋል።ታሪካዊ ቤተ መንግስት ኲሪናለ መጐብኘታቸው ጥልቃ ደስታ እንደሚሰማቸው ያመለከቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የምድራዊ የቤተ ሰቦቼ ሀገር ጣልያን በመንፈስ እና በሐሳብ በየቤቱ በማንኳኳት የቅዱስ ወንጌል ቃል ማብሰር ደስ ይለኛል ብለዋል ።የአርጀንቲና ዜጋ የሆኑ ፓፓ ፍራንቸስኮ አያታቸው ከሰሜን ጣልያን ከፒየሞንተ ክልል ወደ አርጀንቲና የተዘዋወሩ እንደሆኑ ይታውቃል ።በቅድስት መንበር እና በጣልያን መንግስት መካከል ላተራነንሰ የተስየውው ስምምነት አውስተው ስምምነቱ ከጥቂት ወራት በኃላ 50 ዓመቱ እንደሚረግጥ አስታውሰዋል ።ስምምነቱ በቅድስት መንበር እና በጣልያን መንግስት ለጋራ እድገት እና ትብብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም በተጨማሪ ገልጠዋል።በዓለም ዙርያ የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ ስራ እጦት አስከትሎ ህዝብ ለችግር ማጋለጡ ያወሱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳሳቢው ወቅት በሰላም እንዲቀረፍ ቤተ ክርስትያን በበኩልዋ አስተዋጽኦ ለመድረግ ዝግጁ መሆንዋ አመልክተዋል።
በዚሁ ጉዳይ የቤተ ክርስትያን ዋነኛ ሚና የእግዚአብሔር ምሕረት መመስከር እና መጻኢ ግዜ የተስፋ ግዜ እንዲሆን በዓለም ህዝቦች መካከል ትብብር መቀስቀስ እንደሆነም ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ተናግረዋል ። ቤተ ክርስትያን የተስተካከለ ማሕበራዊ ሥርዓት እና ፍትሕ እንዲኖር አበክራ እንደምትሰራ ቅድስነታቸው በተጨማሪ ገልጠዋል።ንግግራቸው በማያያዝም በጣልያን ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በደቡባዊ ጣልያን በደሴት ላምፐዱሳ ባካሄዱት ጉብኝት ከጦርነት ከጭቆና እና ድኽነት ለማምለጥ ከአፍሪቃ ሀገራት ወደ ኤውሮጳ የሚፈልሱ ስደተኞች የሚያጋጥማቸው የሕይወት ህልፈት እና ሥቃይ እና እንግል በቅርብ መገንዘባቸው እና ሐዘን እንደተሰማቸው ጠቅሰው ከነሱ ሰብአዊ ትብብር ማድረግ ግድ ይላል በማለት ለርእሰ ብ ሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ገልጠውላቸዋል።በሌላ በኩል ደግሞ ከተቸገሩ ስድተኞች ጋር ትብብር የሚያሳዩ የመንግስት ተቋማት የተራድኦ ድርጅቶች እና ግለ ሰቦች በማየቴ ደስታ ተሰምቶኛል በማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አመልክተዋል።በደቡባዊ ጣልያን ደሴት ሳርደኛ እና በአሲሲ ዘ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ባካሄድዋቸው ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ለማሕበራዊ ችግር የተጋለጡ ቤተ ሰቦች እና ማሕበረ ሰቦች ማስተዋላቸው ጠቅሰው ለድኽነት ሰለባ ልሆኑ የሀገሪቱ ማሕበረ ሰቦች ሁነኛ እገዛ እንደሚያሻቸውም ፓፓ ፍራንቸስኮ አስገንዝበዋል ።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቤተ ሰብ የማሕበረ ሰብ እና ሕብረተ ሰብ መሠረት መሆኑ ጠቅሰውም ለቤተ ሰብ ሁለ ገባዊ እንክብካቤ እንደሚያስፈልግ እንደማያጠያይቅ ገልጠዋል ።የጣልያን መንግስት ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ፓፓ ፍራንቸስኮ በጣልያን ቤተ መንግስት ተገኝተው ያደረጉት ንግግር አመስግነው ፡ ቅድስነትዎ በቅድስት መንበር እና ጣልያን መንግስት መካከል ያለውን ግንኙነት መልካም መሆኑ ጠቁመው ፡
የመንግስት ዓለማውነት እና ልዑላውነት የቤተ ክርስትያን ነፃነት እና ልዑላውነት እንደተጠበቁ ሆነው በጋራ ለሰብአዊ እድገት የሚካሄደው ስራ አለፈታ ነው እላለሁ ብለዋል ።የጣልያን እድገት እና ጸጥታ ብሔራዊ አንድነት ምርኩስ ያደረገ እንደሆነም ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ ገልጠዋል። 150ኛ የጣልያን ብሔራዊ አንድነት በ20011 ተከብሮ እና ተዘክሮ መዋሉ አይዘነጋም ።ይሁን እና የወቅቱ የጣልያን መንግስት ርእሰ ብሔር ጆርጅ ናፖሊታኖ አያይዘው እንዳመለከቱት ፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰፈነው የኤኮኖሚ ቀውስ በተለያዩ የዓለም ክልሎች በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ግጭቶች የሥነ ሰብእ መዛባት ለዓለማችን እየተፈታተኑ ናቸው ።በኤውሮጳ ሕብረት የጋራ ሕገ መንግስት መሠረት ሰብአዊ ግርማ ክብር መቻቻል ፍትሕ እና ትብብር እንዲዳብር ሕብረቱ በጋርዮሽ በመራመድ ላይ እንደሚገኝ ርእሰ ብሔሩ አመልክተዋል።ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ በማያያዝ ቅድስነትዎ የፖሊቲካ ተዋንያንእርስዎ በየግዜው ከሚያስተላልፉት መልእክት ብዙ ነገር ለመቅሰም ይችላሉ ማለት ባህል ላይ የተመረኮሰ ግንኙነት እስዎ እንዳሉት ውይይት ውይይት ማድረግ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ መገንዘብም ይቻላል ።የጣልያን ፖሊቲካ በየሐሳብ ግትርነት ጅሆ ስለ ሚያዝ ጥሩ አየር መተፈንስ አዳጋች እየሆነ መጥተዋል ብለዋል ያሉት ጆርጆ ናፖሊታኖ ቅዱስ አባታችን ላደረጉት ጉብኝት በእጅጉ አመስግንዎታለሁኝ ብለዋል።ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጣልያን ሲጐበኙ ይህ የመጀመርያ ግዝያቸው ቢሆንም ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ በተሰየሙበት ግዜ እና ባለፈው ወሀ ሰነ ቫቲካን ላይ ከርእሰ ብሔሩ ጋር ተገናኝተው ነበር ።ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ፓፓ ፍራንቸስኮ ትናትና ረፋድ ላይ ቤተ መንግስት ጣልያን በገበኙበት ግዜ ከሀገሪቱ የፓርላማ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ፕረሲዳንቶች እና ከየፓርላመንቱ ባለ ሙያዎች ተገናኝተዋል። በዚህም የኲሪናለ ጉብኝታቸው ፋጻሜ ሁነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.