2013-11-13 18:51:01

የ.ር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ;


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን መካከል በመገኘት ሰላምታ ካቀረቡና ከባረኩ በኋላ ትምህርታቸውን እንዲህ ሲሉ በቡራኬ ጀምረዋል፣ ለዕለቱ ትምህርት መግቢያ የሚሆንም ከማርቆስ ወንጌል 16 “እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል” የሚለው ጥቅስ በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ይህንን ትምህርት አቅርበዋል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! በዕለተ እሁድ እምነታችን ለመመስከር ዘወትር በምንደግመው ጸሎተ ሃይማኖት “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢአት - ለሥሬተ ኃጢአት በሚሆን በአንዲት ጥምቀት ብቻ አምናለሁ” እንላለን፣ ይህ ሓረግ በጸሎተ ሃይማኖት ውስጥ የምናገኘው የአንድ ምሥጢር መግለጫ ነው፣ ስለምሥጢረ ጥምቀት ብቻ ይናገራል፣ እንደእውነቱም ከሆነ ጥምቀት የእምነትና የክርስትያናዊ ሕይወት መግቢያ በር ነው፣ ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስ ለሐዋርያቱ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል” (ማር 16፤15-16) በማለት ይህንን ስልጣን አስረከባቸው፣ የቤተ ክርስትያን ተል እኮ ስብከተ ወንጌል እና በምሥጢረ ጥምቀት አማካኝነት ኃጢአትን ማስተሰረይ ነው፣ ነገር ግን ወደ ጸሎተ ሃይማኖት ቃላት መለስ ብለን ያየን እንደሆነ መግለጫው በሶስት ነጥቦች ሊከፈል ይችላል፤ አምናለሁ! አንድ ጥምቀት ብቻ! ለሥሬተ ኃጢአት የሚሉ ነጥቦች ናቸው፣ 1. በመጀመርያ አምናለሁ! የሚለው ቃል ምን ማለት ይሆን! በታላቅ ሥነ ሥርዓት የሚደገም ቃል ሆኖ የሚያመልክተውም የምሥጢረ ጥምቀት ታላቅነትን ነው፣ ስለሆነም እኛ እነኚህን ቃላት በምንደግምበት ጊዜ እውነተኛ ማንነታችንን ማለት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን እናጋግጣለን፣ በሌላ አነጋገር ምሥጢረ ጥምቀት የአንድ ክርስትያን መታወቂያ ወረቀት የመወለዱ ተግባር የሚያረጋግጥ ነው፣ በቤተ ክርስትያን ውስጥ የመወለድ ሂደት ነው፣ እናንተ ሁላችሁ የትውልድ ዕለታችሁን ታውቃላችሁን! ሁላችሁ ሁላችን በየዓመቱ የትውልድ ዕለታችሁን ታከብራላችሁ፣ ከአሁን በፊትም አቅርቤው የነበርኩት አንድ ጥያቄ ላቅርብላችሁ እወዳለሁ ምናልባት ሌላ ግዜ እደግመዋለሁ፣ ከእናንተ የጥምቀት ዕለቱን የሚያስታውስ ማን አለ! እጁን ያንሳ! እጅግ ጥቂት ናችሁ፣ ጳጳሳቱን ግን ኃፍረት እንዳይሰማቸው አልጠይቃቸውም! ዛሬ ወደ ቤት ከተመለሳችሁ በኋላ መቼ ነው የተጠመቅኩት በማለት ቀኑን ፈልጉት፣ የጥምቀት ቀን የሁለተኛ ልደት በዓል ነው፣ ስለዚህ በየዓመቱ ሁለት የልደት ቀኖች ታከብራላችሁ አንዱ በሥጋ የተወለዳችሁበት በዚህ ዓለም ሕይወት የጀመራችሁበት ሁለተኛው ደግሞ በቤተ ክርስትያን በምስጢረ ጥምቀት ዳግም የተወለዳችሁበት፣ ይህንን ታደርጉታላችሁን! እንዳትረሱ የቤት ሥራችሁ ነው፣ መቼ በቤተ ክርስትያን እንደተወለዳችሁ ዕለቱን ካወቃችሁ በኋላም ጌታን የቤተ ክርስትያኑ በሮችን ስለከፈተላችሁ አመስግኑት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ምሥጢረ ጥምቀት በሥሬተ ኃጢአት ላይ ካለን እምነት ጋርም የተሳሰረ ነው፣ ምሥጢረ ኑዛዜም ወይም ንስሓም እንደ ዳግም ጥምቀት ነው ለዚህም ምሥጢረ ንስሓ ሁሌ ወደየመጀመርያው ንጹሕ ፍጥረት በመምለስና በማሳደስ ዳግም እንድንወለድ ያደርገናል፣ በዚህም ምሥጢረ ጥምቀት የምንቀበልበት ቀን የሕይወት ዘመናችን ሁሉ የሚከተለን ዘወትርም በምሥጢረ ንስሓ እየተደገፈ የሚጓዝ የኑሮ ዘመናችን መነሻ ነው፣ ይህ ጉዞ መልካም ጉዞ ነው ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ስለምንጓዝ፤ የመላው የኑሮ ዘምናችን ጉዞም ነው፣ እርዳታ የሚያገኘውም ከምሥጢረ ንስሓ ነው፣ አንዳንዴ ለኑዛዜ መሄድ ሊከብደን ይችላል ነገር ግን ድካሞቻችን ኃጢአቶቻችን በመናዘዝ ምሕረት እናገኛለን ይህ ብቻ ሳይሆን ግን ወዲያውኑ በዚሁ ምህረት የጥምቀታችን መሓላም ብናሳድስ እንዴት ቆንጆ በሆነ ነበር፣ በዚህም ምስጢረ ኑዛዜ በምንፈጽምበት ጊዜ እንደ የጥምቀት በዓል ማክበር በሆነ ነበር፣ እንዲህ በማደረግም ወደ ምስጢረ ኑዛዜ መሄድ ክበድና ኃፍረት ሳይሆነ የበዓል ስሜት ሊኖረው ይችላል፣ ኑዛዜ ለተጠመቁት ሁሉ የግድ ያስፈልጋል ምክንያቱም ያ በጥምቀት በአምሳል የተቀበሉት ነጭ ልብስ እንዳይቆⶥሽ የቆሸሸም እንደሆነ እንደገና በማጠብ ንጽሕናውን ለመጠበቅ በዚህም የክርስትና ክብርን እንጠብቃለን፣
    ሁለተኛ ነገር አንዲት ጥምቀት ብቻ የሚለው ነው፣ ይህ መግለጫ ያ ቅዱስ ጳውሎስ የሚያሳስበንን ሃሳብ ያስታውሰናል፣ “አንድ ጌታ ብቻ አንድ እምነት ብቻ አንዲት ጥምቀት ብቻ” (ኤፈ 4፤5) ይላል፣ ጥምቀት የሚለው ቃል በውኃ መጥለቅን ያመልክታል፤ እንደእውነትም ይህ ምስጢር እውነተኛ መንፈሳዊ መጥለቅን ያመለክታል፣ ይህ መጥለቅ የት ነው የሚከናወነው! በመዋኛ ቦታ! አይደለም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት መጥለቅን ያመልክታል፣ ምሥጢረ ጥምቀት በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት መስጠም ነው፤ በዚህም ከእርሱ ጋር እንደአዲስ ፍጥረት እንነሳለን (ሮሜ 6፤4)፣ የእንደገና መወለድና በብርሃኑ የመብራት መታጠብን ይገልጣል፣ ዳግም መወለድ ከውኃና ከመንፈስ መወለድን ያመለክታል፣ ከዳግም መወለድ በቀር በመንግሥተ ሰማያት መግባት አይቻልምና (ዮሐ 3፤5) በብርሃን መፍካት ደግሞ በምሥጢረ ጥምቀት የሰው ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በብርሃኑ ይሞላልና “የሰው ልጆችን የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን” (ዮሓ 1፤9) አብርቶ የኃጢአት ጨለማን ያወጋዳልና፣ ለዚህም ነው በምሥጢረ ጥምቀት ሥርዓት ለሕጻኑ ወላጆች የሻማ ብርሃን የሚታደለው ይህንን መብራት ለማመልከት ነው፣ ምሥጢረ ጥምቀት ውስጣችንን በኢየሱስ ብርሃን ያበራናል፣ በዚሁ ስጦታ ኃይል ምሥጢረ ጥምቀት ብርሃን እንዲያው የተቀበልነው እምነት ብርሃን! ብርሃን ለወንድሞቻችን በትለይ ደግሞ በጨለማ ለሚኖሩና በሕይወታቸው አድማስ የዚሁ ብርሃን ጩራዎች ለማይገቡዋቸው ብርሃን ይሆናል፣
    ወደ ገዛ ራሳችን መለስ ብለን ምሥጢረ ጥምቀት ለኔ የታሪክ ጉዳይ ነውን ማለት ቀደም ብየ እንደጠየቅህዋችሁ ለዛሬ ለቤት ሥራ የሰጡኋችሁ ቤታችሁ ስትመለሱ ለመጀመርያ የምታደርጉት መቼ እንደተጠመቃችሁ ቀኑን ማወቅና እግዚአብሔርን ማመስገን እንዳልክዋችሁ ያለፈ ታሪክ ፍጻሜ ነው ወይንም አሁን ያለሁበትና በየጊዜው ለምሆነው የሚመለከት ሕያው ፍጻሜ ነው? ጌታ ኢየሱስ በደሙ በትንሣኤው በሚሰጥህ ኃይል ብርታት ይሰማሃል ወይ! ወይስ ኃይለቢስ ሆኖ ይሰማሃል? ያም ሆነ ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ግን ኃይል ይሰጣል፣ በምሥጢረ ጥምቀት የበራህ ሆኖ ይሰማሃል ወይ? ኢየሱስ የሚሰጠንን ብርሃን ያልተቀበልህና ያልተጠቀምክበት እንደሆነ የጨለማ ሰው ነህ? ይህንን አስተንትኑ፣ የምሥጢረ ጥምቀት ስጦታዎችን በመቀበል ብርሃን መሆንና ለሁሉም ማብራት እንዳለባችሁ አስትንትኑ፣

በመጨረሻም “ለስሬተ ኃጢአት የተሠራ” ስለሚለው ስለሶስተኛ ነጥብ ጥቂት ላብራራ፣ ለስሬተ ኃጢአት በተሠራች አንድ ጥምቀት አምናለሁ” የሚለው የእምነት አንቀጽ እንድታስታውሱት ይሁን፣ በምስጢረ ጥምቀት ሁሉ ኃጢአት ይደመሰሳል፣ የአባታችን አዳም ኃጢአትም ይሁን በግል የፈጸምናቸው ኃጢአቶች ሁሉ ከኃጢአት ቅጣቶቻቸው ይደመሰሳሉ፣ በምስጢረ ጥምቀት የአዲስት ሕይወት በር ይከፈታል፣ ይህ ሕይወት ባለፈው ኃጢአት ክብደት አይነካም ነገር ግን በዚህ ምድር እያለን የመንግሥተ ሰማይ መልካምነትን እንድናጣጥም ያደርገናል፣ ይህ እግዚአብሔር በሕይወታችን በምሕረቱ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት ለድህንነታችን ነው፣ ይህ የደህንነት ጣልቃ ገብነት ሰብ አዊ ባህርያታችንና ደካማነታችንን ጨርሾ አይደመሠውም፣ ስለዚህ ሁላችን ደካማዎች ነን ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን፣ ሆኖም ግን በተሳሳትንበት ጊዜ ይቅርታና ምሕረት የመጠየቅ ኃላፊነትም ያለብሰናል፣ ይህም ቆንጆ ነው! ሁለት ጊዜ ወይም ሶስት ጊዜ ወይንም አራት ጊዜ ልጥመቅ አልችልም ሆኖም ግን ወደ ምሥጢረ ንስሓ መሄድ እችላለሁ! ወደ ምሥጢረ ንስሓ በሄድኩም ጊዜ ይህንን የምሥጢረ ጥምቀት ጸጋ አሳድሳለሁ፣ ልክ ዳግም እንደምጠመቅ ዓይነት ነው፣ ጌታ ኢየሱስ እጅግ መልካምና ርኅሩኅ በመሆኑ እኛ ይቅር ከማለት አይደክምም እና ይምረኛል፣ ይህንን አስታውሱ፣ ምሥጢረ ጥምቀት የቤተ ክርስትያን መግቢያ በርን ይከፍትልናል፣ የተጠመቅሁበት ቀንን ለመፈለግ የሄድሁ እንደሆነ ነገር ግን በድክመቴ ምክንያት ውየህንም በኃጢአቴ ምክንያት የቤተ ክርስትያኑ ተዘግቶ ያገኘሁት እንደሆነ ምሥጢረ ንስሓ ዳግም ይከፍትልኛል ምክንያቱም ምሥጢረ ንስሓ እንደ ዳግም ጥምቀት ሆኖ በጌታ ብርሃን ወደፊት እንድንራመድ ኃጢአቶቻችንን ሁሉ ደምስ ሶ ብርሃን ይሰጠናልና፣ እንዲህ በማድረግ ደስተኞች ሆነን ወደፊት እንጓዝ ምክንያቱም ሕይወታችን ከጌታችን በሚመጣው ጸጋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በደስታ መኖር አለባትና እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.