2013-11-13 16:01:13

ብፁዕ አቡነ ዙፒ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እራስን መቆጣጠርንና ግልጽነትን ዳግም ለመኖር እንድንችል ይደግፉናል


RealAudioMP3 “ማታለልና ማምታታት ባለበት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ የለም…አስመሳይ ክርስቲያናዊ ሕይወት እጅግ ይጎዳል፣ እጅግ ያሰቃያል፣ ሁላችን ኃጢአተኞች ነን፣ ሆኖም ግን ሁላችን በምግባረ ብልሽት የተጠቃንና ሙስኞች አይደለንም።” የሚል ጥልቅ ሃሳብ ያጠቃለለ ከትላትና እ.ኤ.አ. ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እንደ ተለመደው ጧት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ሁሉም ቃልና ሕይወት ያዋሃደ ያጣመረ እውነተኛ ህይወት እንዲኖር የሚል ዕለታዊ ሕይወትና ትምህርተ ወንጌል ያጣመረ ቃልና ሕይወት በማዋሃድ እንዲኖር የሚልና ባንድ እጃቸው ከመንግሥት በመስረቅ በሌላው እጃቸው ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚረዱ ዓይነት ሕይወት አደራ እንዳይኖር የሚል ምዕዳን አዘል ስብከት ማሰማታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በዚሁ ርእሰ ጉዳይ ሥር የሮማ ሰበካ ረዳት ኅየንተ የቅዱስ ኤጂዲዮ ካቶሊካዊው ማኅበር ቤተ ክርስቲያናዊ መንፈስ ደጋፍ ብፁዕ አቡነ ማተዮ ዙፒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እራስን መቆጣጠርንና ግልጽነትን ዳግም መልሰን ለመኖር እንድንችል ይደግፉናል” የተምታታ ሕይወት አስመሳይነት አታላይነት የሚኖር ሕይወት ቤተ ክርስቲያንን ስለ ምረዳ በሚል ተግባር ሥር ደብቆ መኖር አይቻልም፣ ከሕዝብና አገር መስረቅ ቤተ ክርስቲያንን መርዳት አብሮ የሚሄድ ተግባር አለ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በስፋት እንደገለጡትና ይኽ ደግሞ ኅሊናየን ለማስተኛት የሚል የተሳሳተ ልምድ ጨርሶ መወገድ እንዳለበት የሚያሳስብ ሥልጣናዊ ጥሪ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እግዚአብሔር ታጋሽ ታማኝ መኃሪ ይቅር ባይ ነው ሆኖም ግን ገዛ እራስ ለእርሱ ክፍት ሳይኮን የምህረቱ ተቀባይ ብቻ መሆን አይቻልም፣ ምክንያቱም ውስጣችንን እኛነታችንን ከገዛ እራሳችን በላይ የሚያውቅ አባት ነውና፣ ስለዚህ አስመሳይነት ምግባረ ብልሽትና ሙስና ለእግዚአብሔር ምኅረት እምቢ ማለት ነው። እግዚአብሔር የማይምር ሆኖ ሳይሆን እኛ በተሳሳተ ግብራችን ምህረቱን ሳንቀበል ስለ ምንቀር ነው ቅዱስ አባታችን ይኸንን ነው በጥልቀት የሚያብራሩት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.