2013-11-13 16:06:14

በፍልስፍና በሥነ ምርምርና በቲዮሎጊያ መካከል ያለው ውይይት


RealAudioMP3 ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ “በፍልስፍና በሥነ ምርምርና በቲዮሎጊያ መካክል ውይይት የሚቻል ነው” በሚል ርእስ ሥር የፍጥረት ጅማሬና ፍጻሜ የዘፍጥረት አናስር የሁሉም ነገር ጅማሬና ፍጻሜ የተሰኙት የተለያዩ የጥናት ዘርፎች መልስ ሊሰጡበት የሚሞክርባቸው መሠረታውያን ጥያቄዎች ላይ የሚወያይ ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ገለጡ።
ነገሮች ከምን መጡ፣ ለምን ሁሉ ነገር ጅማሬ ያለው ሆነ፣ ጅማሬና ፍጻሜ የሚሉት መሠረታውን ጥያቄዎች ጥንታውያን የነበሩ ያሉ የሚኖሩ በተለያየ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አማክኝነት የተለያየ መልስ ሊሰጥባቸው እንደሚሞከር በተካሄደው ዓውደ ጥናት አስተምህሮ የሰጡት የቫቲካን የሥነ ሕዋ የምርምርና ታዛቢ የጥናት ማእከል የሥነ ቅርጸ ነገሮች ምርምር ኅልዮ ሊቅ ኣባ ጋብሪኤለ ጆንቲ፦ “እስካሁን ድረስ በሥነ ምርምር ዘርፍ የፍጥረት አናሥር በተመለከት ግብራዊ መልስ ለመስጠት ከተደርጉት ሙከራዎች ውስጥ በሥነ ምርምር መስክ የተሻለ መልስ ሆኖ የተገኘው የሥነ ቆስሞስ ቅርጽ በተመለከተ የእድገት ለውጥና መስፋፋቱ ለማብራራት የሚሞክረው ቢግ ባንግ ተብሎ የሚጠራው ኅልዮ ነው፣ መሬት በአንድ ወቅት ግለትና ሙቀን ከዛም ቅዝቃዜ ተከስቶባት ሆኖም ግን ይኽ ለእድገትና ለመስፋፋት ምክንያት ሲሆን ለዚህ ክስተት የተጋለጠው የመጀመሪያው ፊዚካዊ ቅጽበታዊ ሁነት በተመለከተ ኅልዮ ግን እስካሁን ድረስ የለም፣ የተለያዩ ሥነ ምርምራዊ መላ ምቶች ይቀርባሉ ነገር ግን የሁሉም መላ ምት ኅልዮ ግን እስካሁን ድረስ አልተገኘም” ካሉ በኋላ አያይዘው፦ “አንድ የሥነ ምርምር ሊቅ የሚከተለው ኃይማኖት የሚሰጠው ማብራሪያ ሳያገል ነገር ግን ጥልቅ ምርምር ከማድረግ የማይቆጠብ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፣ ምርምርና እምነት የሚጋጩ አይደሉም፣ እንዳውም እምነት ያለው ተመራማሪ ቅድመ እምነቱ የሆነው ማብራሪያ የማግኘት ብቃት እምነት ከሌልው ተመራማሪ የላቀ ነው” ሲሉ በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የሥነ መሠረት ቲዮሎጊያ ትምህርት ዘርፍ ዋና አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር ሚከሊና ተናቸ በበኩላቸውም፦ ሥነ ምርምርና ቲዮሎጊያ ማብራሪያ ለመስጠት ጥረት የሚያደርጉ ነገሮችን ለመተንተን የሚሞክሩ በአንድ እውነት ላይ ሊደረስ እንዲቻል የሚጥሩ ናቸው፣ ሆኖም ግን የላቀው አርግጠኛነት የትኛው ነው። አንድ እውነት እውነት ከሆኑ ሌላው የምርምር ዘርፍ የሚቀርበውን እውነት አያገልም፣ ምክንያቱ ያለው የጋራ አካፋይ የሆነው እውነትን የመፈለጉ ባህርይ ያገናኛቸዋልና፣ ሕይወት ለማብራራትና የበለጠ ሕይወት እንዲኖር ቲዮሎጊያ ፍልስፍናና ሥነ ምርምር በየፊናቸው ጥረት የሚያደርጉ ናቸው ያላቸው እውነትን የመፈለጉ ጥሪ ያወያያቸዋል’ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማጆረ ገለጡ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.