2013-11-13 15:53:01

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እግዚአብሔር ሲቆጣ ይንከባከባል እንጂ አይጎዳም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው ጧት በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት፦ “ልክ እንደ አንድ ሕፃን እጆቹን በአባቱ እጆች ላይ በማኖር የሚኖረው ሙሉ መተማመን እኛም ልክ እንደዚሁ ገዛ እራሳችን ለእግዚአብሔር እንስጥ፣ ጌታ መቼም ቢሆን ለብቻችን አይተወንም፣ ሲቆጣ ይንከባከበናል እንጂ አይጎዳንም” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ስክበት ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ከመጽሐፍፈ ጥበብ የተወሰደውን ስለ መፈጠራችንን የሚያወሳው አንደኛ ምንባብ ተንተርሰው፦ “ሁላችን በሞት እናልፋለን፣ ሆኖም ግን የዲያቢሎስ ሆኖ በሞት ማለፍና በእግዚአብሔር እጆች ማለፍ ገጠመኝ የተለያየ ነው። ከመጀመሪያ ጀምሮ በእግዚአብሔር እጆች ነን የሚለው እውነት ደስ ያሰኘኛል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውብ የሆነ ምስል በመጠቀም ፍጥረት ይገልጥልናል፣ ይህ ውብ ምስል ደግሞ እግዚአብሄር በእጆች ከተቦካ ጭቃ ፈጠረን፣ ከአመድ የእርሱ አርአያና አምሳያ በማኖር ፈጠርን፣ የእግዚአብሔር እጆች ናቸው የፈጠሩን፣ ልክ እንደ አንድ የእጅ ግብረአዊ ሙያተኛ የእጆቹ ሥራ ነን። የፈጠሩን እጆቹ ለብቻችን ትተዉን አያውቁም አይተዉንም” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ቅዱስ አባታችን አንድ አባት የልጁን እጆች ይዞ በመምራት እንደሚጓዝ ሁሉ እግዚአብሔር እጃችንን ይዞ በመምራት የሚጓዝ መሆኑ ሲገለጡ፦ “አንድ አባት ከልጁ ጋር በመጓዝ፣ በእግር መራመድን ያስተምራል፣ እግዚአብሔር እንደዚሁ ነው፣ በስቃይ በሐዘን በመከራ የመሩን እጆቹ ናቸው የሚያባብሉን የሚያጽናኑን ያፈቅረናል፣ በእጆቹ ሲንከባከበን ምህረቱንም ይሰጠናል ይቅር ይልልናል፣ ኢየሱስ ቅንዋቱን ወደ አብ በማድረስ የተሰቃየው አካሉን ለአብ ያሳያል፣ ለእኛ የተከፈለው ዋጋ፣ የእግዚአብሔር እጆች ስለ ፍቅር የተሰቃየው አካሉና ቅንዋቱ ቤዛችን ነው” እንዳሉ ያመለክታል።
“በጠና የታመሙትን ህሙማንን የነኩት የኢየሱስ እጆችን እናስብ። የእግዚአብሔር እጆች ናቸው፣ ይፈውሳሉ ያድናሉም፣ እግዚአብሔር በጥፊ የሚመታ ነው ብሎ ለመገመቱ በእውነቱ ያዳግታል፣ አዎ ይቆጣናል ሆኖም ቅን ቁጣው በመንከባከብን እንጂ ጉዳት እያደርስብንም፣ አባት ስለ ሆኖ ሲቆጣ በመንከባከባችን ነው የሚቆጣው። የቅን ሰዎች መንፈስ በእግዚአብሔር እጆች ላይ ናቸው፣ የፈጠሩንን የእግዚአብሔር እጆችን እናስብ፣ ዘለዓለማዊ መዳንን ሰጠን፣ በሕይወት ጎዳና እጆቹ ይመሩናል፣ ልክ እንደ አንድ ሕፃን ልጅ እጆቹ በአባቱ እጆች ላይ ተማምኖ እንደሚያኖር ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጆች ለእኛም እንደዚሁ ነው። አስተማማኝ እጆች ናቸው” በማለት ያሰሙትን ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቅለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.