2013-11-11 15:47:55

እኩልነትና ወንድማማችነት ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ የሚደፍ መሣሪያ


RealAudioMP3 ጳጳሳዊ የሥነ ግኑኝነት መላ ዓለም አቀዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም” በሚል ርእስ ሥር ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የደረሱት በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመቅድም ጽሑፍ የተኖርበት መሆኑ ከወዲሁ ሲገለጥ። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዓለም አቀፍ ደረጃ ተከስቶ ያለው ቀውስ ኢፍትሃዊነት የመሳሰሉት የተለያዩ መሠረታዊ የሰብአዊ መብትና ክብር ረገጣ፣ በማኅበራዊ በሃይማኖታዊና በባህላዊ ጉዳይ የሰው ልጅ ተሳትፎ አሰናካይ የሆኑትን ለያይ አጥሮች እንድናስወግድ ያነቃቃናል ብቻ ሳይሆን ግድ ይለናል ስለ ሰላምና እድገት የሚናገሩ ሳይሆን የሰላም መሣሪያና ማንም የማያገል ሁሉን ያጠቃለለ ሰላምና እድገት ለማረጋገጥ የሚተጉ ሆነን መገኘትን የሚል ህሳብ ያካተተ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የግኑኝነት መላ አገልግሎት እንጂ የጦር መሣሪያ የጦርነት የግል ብሔራው ጥቅም የሆነው ለተለያዩ አደጋ ለሚያጋልጥና አስከፊ ጠባሳ ጥሎ ለሚያልፈው አመክንዮ ብዙሃንን የሚያገል ድኽነትንና መረሳትና ተገሎ ለመኖር ለሚገፋፋ የኢፍትሃዊነት መሣሪያ መሆን የለበትም፣ በእሴቶች በጋራ አስተሳሰብ ላይ የጸና የጋራ ኑሮ መቃወስ ለግኑኝነት መላ አሉታዊ አጋጣሚና ብሎም ተጋርጦ ነው። አሉታዊ አጋጣሚነቱ በሕዝቦች መካከል መቀራረብ መከባበር ለማጽናት ተጋርጦነቱ ደግሞ የሁሉ አገሮች ሕዝቦች ባህላዊ መለያና ክብርና ሰብአዊ ነጻነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ለማድረግ የሚያስችል መሆን ስላለበት ነው በማለት በመቅድም ጽሑፋቸው ገልጠው፣ አሉታዊ የሆነው የዓለማዊነት ትሥሥር ገጽታውን የግኑኝነት መላ የሚያሰናክል መሆኑ በማብራራት ይኽ ደግሞ የግኑኝነት መላ ያለው ነቢያዊ ገጽታውና ጥሪውን የሚያነቃቃ ነው። የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ እንዲቻል የግለኝነት አመክንዮ ማስወገድ በሚለው ዓላማ የሚራመድ በሰው ልጅ በኑባሬ ያለው መንፈሳዊ ባህርይ የሚያከብርና አቢይ ግምት እንዲሰጠው የሚልና በዚሁ ረገድ መንገዱንም ጭምር የሚያመለክት አገልግሎት መሆኑ በማብራራት በተለይ ደግሞ ጳጳሳዊ የሥነ ግኑኝነ መላ ከዚህ አንጻር ሲታይ ያለው ጥልቅና አቢይ ኃላፊነት ለመረዳት የሚቻል ነው ብለው፣ ቸልተኝነት በግል ጥቅም ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፋዊ ግኑኝነትና ትብብር ተወግዶ ለሁሉም እርባና ላይ የጸና ግኑኝነት እንዲኖር የሚደግፍ ነው ብለዋል።
በመጨረሻም ኢፍትሃዊነት ፍትሃዊነት በማነቃቃት ማስወገድ ያለው አስፈላጊነትም አብራራተው ከዚሁ ጋር በማያያዝ የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 የነበረው ጳጳሳዊ የግኑኝነት መላ በማድነቅ ቤተ ክርስቲያን ካለ ምንም ገደብ ማገልገል ከሚለው እምነትና ተግባር የመነጨ በሳል ሕይወታቸውና አመለካከታቸው በዓለም አቀፍ ግኑኝነት ያስጨበጠው ውጤት ለእኔ ለተከታይ ጴጥሮስ አብነት ነው፣ ታሪክ የሚለካው በመስቀል እውነት ነው፣ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ በባህል በጥበብ የተካኑ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የደረሱት መጽሐፍ ይኸንን ያሰመረ የአሕዛብ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ የኖረው ውስጣዊው ኃይል ላይ የጸና የቤተ ክርስቲያን መልካሙን ሁሉ፦ እኔ ግን ዓለም ለእኔ ከሞበት እኔም ለዓለም ከሞትሁበት ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ የምመካበት ነገር የለኝም” (ገላ. 6,14) ከሚለው ከመስቀል ኃይል በመነጨ እምነት የሚያነቃቃ መጽሓፍ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.