2013-11-11 15:41:52

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስቲያን ሁሌ ታዳሽ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሮማ ካቴድራል የሁሉም በጠቅላላ የመላ ዓለም አቢያተ ክርስቲያን እናት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ቅዱስ ዮሓንስ ዘ ላተራኖ ባሲሊካ የተባረከበተ ዕለት የምታስብበተ ቀን መሆኑ በማስታወስ፦ በዕለቱ ምንባብ ከነቢይ እዝቅኤል መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 45 ከቤተ መቅደስ የሚፈሰው ወራጅ ውኃ የእግዝአብሔርን ከተማ ደስ የሚያሰኝ መሆኑና ይኽ ፈሳሽ ውኃ የቤተ ክርስቲያንን ሕይወት የሚደግፍ መሆኑ በማብራራት፣ ቀጥለውም ሁለተኛይቱ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ለቆረንጦስ ሰዎች የማእዘን እራስ የሚለውን ቃል ጠቅሰው ሲያብራሩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የጸናችበት የማእዘን እራስ ነው ብለው፣ በመጨረሻውም የዕለቱ ወንጌል የቤተ መቅድስ መንጻት ትእምርት የሆነውን እርሱም ቤተ ክርስቲያን ካለ ማቋረጥ ዕለት በዕለት የምትታደስ መሆንዋ የሚያረጋግጥና ይኽ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አባላት ኃጢአተኞች ስለ ሆኑና እንዲህ በመሆኑም ዘወትር መለወጥ ያስፈልጋቸዋል ከሚለው እውነት የመነጨ ነው። ይኽ ቤተ ክርስቲያን ዘወት ታዳሽ የሚያስብላት መሠረታዊው ምክንያት መሆኑ ገልጠው፣ በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት ስብከት ቤተ ክርስቲያን የጸጋ ውኃ የሚፈስባት የእግዚአብሔር ቤት እንድትሆን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የጸናች ሆናም ትገኝም ዘንድ ምእመናን ስለ እርሷ እንዲጸልዮ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.