2013-11-11 15:39:21

ሁሙማን መንፈሳውያን ነጋድያን ወደ ሉርድና ወደ ተለያዩ ቅዱሳት ሥፍራ የሚያጓጉዘው የኢጣሊያው ብሔራዊ ማኅበር ዝክረ 110ኛው ዓመተ ምሥረታው ምክንያት ቅዱስ አ.ር.ሊ.ጳ. ያሰሙት መልክእት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. Unitalsi-ሁሙማንና መንፈሳውያን ነጋድያን ወደ ሉርድ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራና ወደ ተለያዩ ቅዱሳት ሥፍራዎች የሚያጓጉዘው የኢጣሊያው ብሔራዊ ማኅበር” አባላትና በዚሁ ማኅበር የሚረዱት በከባድ የማይድን በሚባለው በሽታ የተጠቁት ህሙማን በጠቅላላ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል ማሰማታቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን ለማኅበሩ አባላት በጠቅላላ ህሙማንና አካለ ስንኩላንን የሚያስተናግድ እይታና በርኅራሄና በቸርነት በእቅፍ የሚያኖር እጆች የታደላችሁ እንጂ እንደ ማንኛው እንዲሁ ግብረ ሠናይ የተነጠለው አዛኝነት ወይንም ምንም ለምድረግ አልችልም የሚለው እጅ መስጠት የማይቻላችሁ ናችሁ” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ መለስ ብለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወደ ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ በመግባት መሪ ቃል ከመለገሳቸው ቀደም በማድረግ እዛው የተገኙት የማይድን በሚባለው በሽታ የተጠቁትን ሁሉ አንድ በአንድ ሰላም እያሉ በመሳም ተስፋን እምነትና ፍቅር በማነቃቃት የቤተ ክርስቲያን ቅርበትና ትብብር ማረጋገጣቸው ገልጠው፦ “ወቅታዊው ባህላዊ ማህበራዊ ይዘት አካላዊ ድክመት እንደ አንድ ችግርና እንቅፋት ብቻ በመመልከት ምን ይደረግ እየተባለ ግብር ሠናይ የተነጠለው አዛኝነትና ምንም ነገር ለማድረግ እይቻልም ብሎ ለመደበቅ የሚከጅለው ወይንም ህሙማንን አካለ ስንኩላንን የሚነጥል ነው። የኡኑታልሲ ማኅበረ አባላት ይኽ ዓይነት ማኅበራዊ ባህላዊ ይዘት የሚቃወም በማኅብረተሰብ በቤተ ክርስቲያንና በማኅበራችሁ ጭምር ነቢያው ምልክት ለመሆን የተጠራችሁ ናችሁ” በማለት ባስደመጡት መልእክት ጠቅሰው፣ የእናንተ የዚህ ማኅበር አባላት አገልግሎት ሰባአዊነት ፍቅርና ረጂነት ከሚል ሃሳብ የመነጨ ሳይሆን የሚሠዋው ወንጌላዊ ፍቅር እርሱም የአጽናኝ አገልግሎት ከሚለው ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ተነቃቅታችሁና ተገፋፍታችሁ በስቃይና መካራ ፊት ፊቱን ደብቆ ከማይጓዘው የደጉ ሳምራዊ አብነት የምትከትሉ ናችሁ፣ ስለዚህ ፊትን አዙሮ የአለ መጓዝ እሴት የተካናችሁ ናችሁና በዚሁ ተግባር ወደ ፊት በሉ ቀጥሉበትም” እንዳሉ ደ ካሪሊስ አስታወቁ።
“የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ኅሙማን በጠቅላላ ትብብርና ድጋፍ የሚጠባበቅ የኅብረሰብ ክፍል ሆናችሁ እንዳይሰማችሁ ካለ ምንም ጉድለት በሙላት በቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ተልእኮ ስያሜ ያላችሁ እንደ ሆናችሁ ሊሰማችሁ ይገባል፣ የእናንተ ጽሞና የተካነው በጽሞና የሚናገረው ቃል ከሚነበነበው ቃል በላይ ጥልቅና ድምጹ የጎላ ህልውናና ጸሎታችሁ ዕለት በዕለት ለዓለም ድኅነት መሥዋዕት ከሆነው ከሱቁል ኢየሱስ ስቃይ ጋር ሱታፌ ያለው ነው። ለማኅበረ ክርስቲያን ልዑል መንፈሳዊ ሃብት ናችሁ፣ የቤተ ክርስቲያን እጹብ ድንቅ ሃብት መሆናችሁ ሊያሳፍራችሁ አይገባምካሉ በኋላ የኢየሱስ እናት የሆነቸውን ቅድስት ድንግል ማርያም ልክ ልጅዋ በመስቅል ላይ እያለ ከመስቀሉ ሥር ሆና ትመለከተው እንደነበር አስታውሰው፦ ቅድስት ድንግል ማርያም የሚያስፈልገንን ሁሉ ታውቃለች፣ እኛን ትንከባከባለች፣ ስለ እኛ ታማልዳለች፣ ትጸልያለች፣ በተለይ ደግሞ በስቃይና በመከራ በድካም አለ አጽናኝ በምንገኝበት ወቅት በኃጢአት በምንገኝበት ወቅት ቅርባችን በመሆን ስለ እኛ ትጸልያለች ታማልዳለችም፣ ለዚህም ነው በመቁጸሪያ ጸሎት ለእኛ ለኃጢአተኞች ትጸልይ ዘንድ የምንለምናት” ብለው ለሁሉም ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.