2013-11-08 14:34:52

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ የጠፋውን የሚፈልግ የእግዚአብሔር ትሁት ፍቅር የምኅረት ደስታ ነው


RealAudioMP3 የእግዚአብሔር ደስታ የጠፋችውን በግ መፈለግ ነው። ስለዚህ ይኽ ደግሞ ለጠፉት ሁሉ የሚፈልግ የፍቅሩ ትህትና መሆኑ የሚያረጋግጥ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደ ተለመደው በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ህንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት በስፋት ማብራራታቸው የቅድሴውን ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን በላቲን ሥርዓት መሠረት የዕለቱ ምንባበ ወንጌል እርሱም ጠፍቶ የተገኘው በግና ጠፍቶ የተገኘው የወርቅ መሐለቅ ምሳሌዎችን ማእከል በማድረግ የፈሪሳውያንና ጸሐፍቶች አቋምና ያልተገባ ጠባያቸውን ጠቅሰው። ኢየሱስ የሚፈጽመው የሚያከናውነው ተግባርና እንቅፋት ሆኖባችው ይኽ ሰው አደጋ ነው፣ ከጸሐፍትና ቀራጮች ኃጢአተኞች ጋር በማእድ አብሮ ይቀመጣል፣ ነቢይነትን በማርከስ እግዚአብሔርን ያስቀይማል የሚለውን አስተሳሰባቸውና ንግግራቸውን ኢየሱስ የአስመሳይነት እርምታ ብሎ ሲገለጠው ለፈሪሳውያን ማጉረምረም በአንድ ደስ የሚያሰኝ ምሳሌ አማካኝነት ይመልሳል። በዕለቱ አጭር ምንባበ ወንጌል ደስታና ኃሴት አራት ጊዜ ተደጋግሞ ተጽፏል፣ ሶስት ጊዜ ደስታ አንድ ጊዜ ፍስሐ የሚሉት ቃላት እናገኛለን፣ እናንተ ባደረግሁት ሁሉ ትቀየማላችሁ ትሰናከላላችሁ፣ አባቴ ግን ደስ ይሰኛል፣ በዚህ ምንባብ ማእከላዊው መልእክት የአብ ደስታ የሚል ነው። ይኽ ደግሞ ማጣትን እርሱም የፈጠረውን ሁሉ ሊከስር የማይፈልግ መሆኑ ነው የሚያመለክትልን፣ ስለዚህ ላለ ማጣት ሁሌ መፈለግ የሚል ነው፣ የሚፈልግ እግዚአብሔር ሁሉም የሚፈልግ ከእርሱ ርቀው የሚገኙትን የሚፈልግ፣ ልክ እንደ አንድ እረኛ የጠፋውን በግ እንደሚፈልግ ማለት ነው” ካሉ በኋላ የእግዚአብሔር ሥራ ለመፈለግ መውጣት የሚል መሆኑ ሲያብራሩ፦ “የእርሱ የሆኑትን ማጣትን የማይቀበል የሚቻለውና በመታግስ በዝምታ የሚቀበለው ጉዳይ አይደለም። የጠፉትን ለመፈለግ የሚወጣ እግዚአብሔር ነው። ማጣትን የማይታገስ አብ ነው። እስከ ፍጻሜው ድረስ የሚፈልግ የጠፋውን እስከ ሚያገኘው ድረስ የሚፈልግ፣ ልክ እንደዛች የወርቅ መሐለቅ የጠፋባት ኩራዝ በማብራት ቤትዋን ሁሉ በትእግሥት በመጥረግ በጥንቃቄ የምትፈልግ ሴት የሚፈልግ እግዚአብሔር ነው። ይኸንን የጠፋውን ልጄ አጥቼው አልቀርም፣ ከስሬው አልቀርም፣ ላጣው አልፈልግም፣ እንግዲያውስ ይኽ ነው እግዚአብሔር አባታችን፣ ዘወትር ካለ ማቋረጥ የሚፈልግ ነው” እንዳሉ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።
“የእግዚአብሔር ደስታ የኃጢአተኛው ሞት ሳይሆን የኃጢተኛው ሕይወት ነው፣ ያ በኢየሱስ የተቀየመውና ያጉረመርም የነበረው ሕዝብ ምንኛ እሩቅ ነበር። ያ ሕዝብ ምንኛ ከአብ ልብ የራቀ ነበር። አዎ ሃይማኖተኛ ሰው መሆኑ ለእነርሱ ጥሩ ሰዎች ሁሌ በጥንቃቄ መጓዝን አዋቂነትን ጨዋ መሆንን ጨዋ ተመስሎ መታየትን፣ ይኽ ደግሞ አስመሳይነት ነው። በአስመሳይነት ዘንድ ማጉረምረም፣ የእግዚአብሔር ደስታ ግን የፍቅር ደስታ ነው። አባት ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ…ይኸንን ያንን ፈጽሚያለሁ….እንላለን፣ እርሱ ደግሞ አዎን እኔ ግን አፈቅርሃለሁ ነው የሚለን። ልፈልግህ እወጣለሁ ወደ ቤትና ቤትህም ይዤህ እመለሳለሁ፣ አባታችን ይኽ ዓይነቱ አባት ነው። እናስተውል” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.