2013-11-07 11:37:14

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንድምን አደራችሁ!
ባለፈው ዕለተ ሮብ ስለቅዱሳን ሱታፌ ቅዱሳን በሆኑ ሰዎች መካከል ያለ ውህደት መሆኑን ገልጬ ነበር፣ ማለትም በአማኞች መካከል ያለው አንድነት ነው፣ ዛሬ የዚህ አር እስት ሌላውን ገጽታ ለማብራራት እወዳለሁ፣ የምታስታውሱ ከሆነ ባለፈው ትምህርተ የቅዱሳን ሱታፌ የሚለው ሁለት ቅርጫፎች እንዳሉት አንደኛው በመካከላችን ያለው አንድነት ሆኖ በዚሁ ማኅበረ ክርስትያን እናቆማለን ሌላው ደግሞ የመንፈሳዊ ነገሮች ውህደት ቅዱሳት ነገሮች ማለት ነው፣ እነኚህ ሁለት ገጽታዎች እርስ በእርስ ጥብቅ ትስ ስር ያላቸው ስለሆኑ በክርስትያኖች መካከል ያለው አንድነት በመንፈሳውያን ነገሮች በመሳተፍ ያድጋል፣ በትለይ ምሥጢራትን ልዩ ስጦታዎች ወይንም ካሪዝማ እና ምግባረ ሠናይን የተለመለከትን እንደሆነ በአዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ቍ.949-953 በሰፊው ይገልጠዋል፣ እኛ የምናድገው እያንዳንዳችን መንፈስ ቅዱስ በሰጠን ልዩ ስጦታ በአንድነት በምግባረ ሰናይ በምሥጢራት በመሳተፍ ነው፣
ከሁሉ በላይ ደግሞ በምሥራት መሳተፍ ያስፈልጋል፣ ምሥጢራት በመካከላችን ያለውን ተግባራዊና ጥልቅ ውህደትን እውን በማድረግ ይገልጣሉ፤ ምክንያቱም በምሥጢራት አማካኝነት አዳኝ የሆነውን ክርስቶስን እናገኛለን በኢየሱስ አማካኝነት ደግሞ በእምነት ወንድሞቻችን የሆኑትን እናገኛለን፣ ምሥጢራት ለማለቱ የሚደረጉ ሥርዓቶች አይደሉም፣ የክርስቶስ ኃይል ናቸው፤ በምሥጢራት ኢየሱስ ክርስቶስ አለ፣ መሥዋዕተ ቅዳሴ ስናሳርግ በቅዱስ ቍርባን ውስጥ ሕያው ኢየሱስ አለ፤ ሁላችንን ሰብስቦ እግዚአብሔርን የሚያከብ ማኅበር የሚያደርገን ሕያው የሆነው ኢየሱስ ነው፣ እያንዳንዳችን በምስጢረ ጥምቀት በምስጢረ ሜሮን እና በምስጢረ ቅዱስ ቍርባን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ እንሆናለን ከመላዋ የአማንያን ማኅበር ጋርም አንድ እንሆናለን፣ ባንድ በኩል ምሥጢራት የምትሰራ ቤተ ክርስትያን ስትሆን በሌላው በኩል ደግሞ ቤተ ክርስትያንን የሚያንጽዋት አዳዲስ ልጆች በመውለድ በቅዱስ የእግዚአብሔር ሕዝብ በመሰብሰብ እና አባልነታቸውን በማጽናት ቤተ ክርስትያን የሚያደርግዋት ምሥጢራት ናቸው፣ በምሥጢራት ድኅነት ከሚሰጠን እና ለሌሎች ይህንን ድኅነት ለማዳረስ ሂዱ ብሎ ጥሪ ከሚያቀርብልን ከክርስቶስ ጋር የምናደርገው እያንዳንዱ ግኑኝነት ያ ለማየት የቻልነው የነካነው ያገኘነው የተቀበልነው ሁሉ እውነትና የሚታመን መሆኑን ይገልጥልናል ምክንያቱም እርሱ ፍቅር ነውና፣ በዚህ መሠረት ምሥጢራት ሰባክያነ ወንጌል እንድንሆን ይገፋፉናል፣ ይህም ወንጌል ለሁሉ የማዳረስ ኃላፊነት ሆኖ አስቸጋሪ በሆኑ አከባቢዎችም ሳይቀር ወንጌልን መስበክ ምስጢራንትን እየተሳተፉ የመኖር ሕይወት ቀጥተኛ ውጤት ነው፣ ይህም ደህንነትን ለሁሉ ለመስጠት በሚሻው በእግዚአብሔር የሚጀመረውን የደህንነት ተግባር መሳተፍ ነው፣ የምስጢራት ጸጋ በውስጣችን ያለው ኃያልና ደስተኛ እምነት ይመግባል፣ ይህ እምነት በእግዚአብሔር አስገራሚ ሥራዎች ያደንቀናል እንዲሁም ከዚህ ዓለም ጣዖቶች እንድንቃወም ያስችለናል፣ ስለዚህ ሱታፌ አስፈላጊ ይሆናል፣ ሕጻናት ተሎ እንዲጠመቁ ተሎ ቅብ ዓ ሜሮን እንዲቀበሉ አስፈላጊ ይሆናል፣ ለምን ያልን እንደሆነ ምክንያቱ እነኚህ ምስጢራት የኢየሱስ በመካከላችን መኖርና እንዲረዳን ስለሚያደርጉ ነው፣ እንዲሁም ኃጢአተኞች ሆነን በሚሰማን ግዜ ወዲያውኑ ወደ ምስጢረ ኑዛዜ መሮጥ አስፈላጊ ነው፣ ምናልባት አባ! ይህማ አይሆንም ፍርሃት ይሰማኛል ቄሱ ይቀጡኛል ያላችሁ እንደሆነ! እንደዛ አይደለም ቄሱ አይቀጣችሁም! በምስጢረ ንስሓ ማንን እንደምታገኙ ታውቃላችሁን? መሓሪና ይቅር ባይ የሆነ ኢየሱስን ነው የምታገኘ! ኢየሱስ ነው የሚጠባበቅህ! ይህ ቅዱስ ምስጢር ነውና! ይህም ቤተ ክርስትያንን በአጠቃላይ ያዳብራል፣
በቅዱሳት ምስጢራት የመሳተፍ ሁለተኛ ገጽታ የስጦታዎች ውህደት ወይም ሱታፌ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች የተለያዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችና ጸጋዎች ይሰጣል፣ ይህ አስደናቂ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ሃብት ለቤተ ክርስትያን ሕንጸት ያለሙ ናቸው፣ ስጦታ ወይም ካርዝም ብርቱ ቃል ነው፣ ስጦታዎች ካሪዝሞች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ናቸው፣ እነኚህ ስጦታዎች የተለያዩ ናቸው፣ መንፈስ ቅዱስ እነኚህን ስጦታዎች ሲሰጠን ደብቀን ልናስቀምጣቸው ሳይሆን ከሌሎች ጋር እንድንካፈላቸው ነው፣ ለሚቀበላቸው ግለሰው ጥቅም የተሰጡ አይደሉም ነገር ግን ለመላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጥቅም ነው የሚሰጡት፣ ምናልባት አንድ ስጦታ ወይም ካሪዝም ለግል ጥቅም ብቻ የዋለ እንደሆነ እውነተኛ ስጦታ መሆኑን መጠራጠር ያስፈልጋል፣ ስጦታዎች ወይም ካሪዝም ልዩ ጸጋዎች ሆነው ለሌሎች በጎ ነገር ለማድረግ የተሰጡ ናቸው፣ ዝንባሌዎች ወይም አስተንፍሶዎች ወይንም ውሳጣዊ ግፊቶች ሆነው ለማኅበረ ክርስትያን አገልግሎት በተወሰኑ በተለዩ ሰዎች ኅሊናና ተመኵሮ የሚወለዱ ናቸው፣ እነኚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች በተለይ የሚሰጡት ለቤተ ክርስትያንና ለተልእኮዋ እድገት ነው፣ እኛ ሁላችን በገዛ ራሳችንና በሌሎች የሚገኙትን ስጦታዎች እንድናከብራቸው የቤተ ክርስትያን ህልውናና ፍርያም ተግባር ጥቅም እንደሚያበረታቱ አድርገን መቀበል አለብን፣ “መንፈስን እንዳታጠፉ” (1ተሰ 5፤19)፣ እነኚህን ቤተ ክርስትያን እንዲያዳብሩ የሚሰጡን እጅግ ቆንጆ የሆኑ የተለያዩ ችሎታዎችና መንፈሳዊ ኃይሎች የሚሰጠንን መንፈስ ቅዱስ እንዳናጠፋ ይሁን፣
በእነዚሁ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ፊት የእኛ ዝንባሌ እንዴት ነው? የእግዚብሔር መንፈስ ለፈለገው እንደሚሰጣቸው እናውቃለንን? እግዚአብሔር እምነታችንንና ለዓለም ያለን ተልእኮን በእነዚህ ስጦታዎች አማካኝነት እንደሚያበረታስ ልብ ብለን እናስባለንን?
ወደ ሶስተኛው ከቅዱሳት ነገሮች መሳተፍ ገጽታ የመጣን እንደሆነ ደግሞ የምግባረ ሰናይ ወይም የፍቅር ሥራ ሱታፌ እንመለከታለን፣ በምግባረ ሰናይ አንድ እንድንሆን የሚያደርገን የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በመጀመርያዎቹ ዘመናት አረሜኖች ክርስትያኖችን ሲያዩ “ እንዴት ይፋቀራሉ! አይጣሉም! እርስ በእርሳቸው አይወቃቀሱም! እንዴት መልካም ነው” ይሉ ነበር፣ ምግባረ ሰናይ እርስ በእርስ መረዳዳት መዋደድ ይህ መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ የሚያኖረው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በክርስትያናዊ ማኅበረሰብ እነኚህ ስጦታዎች አስፈላጊ ናቸው ሆኖም ግን ዘወትር በምግባረ ሰናይና በፍቅር ለመዳበር የሚያገለግሉ መሆን አለባቸው፣ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅር ከሁሉ እንደምትበልጥ የሚያስተምረው (1ቆሮ 13፤1-13)፣ ፍቅር የሌለ እንደሆነ ልዩ የሆኑ ስጦታዎችም ሳይቀሩ ከንቱ ናቸው፣ ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው ሕሙማንን የመፈወስ ስጦታ አለው ሌላም ሌላም ነገር ግን በልቡ ፍቅር አለ ወይ የምግባረ ሰናይ ተግባር አለው ወይ ብለን የጠየቅን እንደሆነ፤ ፍቅር ካለው እሺ ይገስግስ አለበለዚያ የፈጸመው ቢፈጽም ለቤተ ክርስትያን አይጠቅማትም፣ ፍቅር የሌላቸው ስጦታዎች ለቤተ ክርስትያን አያስፈልግዋትም ምክንያት ፍቅር የሌለው ሁሉ ባዶሽ ነውና! ይህ ባዶሽ በግል ጥቅም ይሞላል፣ አንድ ጥያቄ ላቅርብላችሁ እኛ ሁላችን ለገዛ ራሳችን ብቻ የምናፈቅር ብንሆን እንደማኅበር ልንኖር እንችል ነበርን በሰላም ለመኖርስ? እያንዳንዳችን ገዛ ራሱን ብቻ የሚያፈቅር ከሆነ በሰላም ለመር ይቻላልን? ይቻላል ወይስ አይቻልም? አዎ አይቻልም ለዚህም አንድ የሚያደርግ ፍቅር ምግባረ ሰናይ ያስፈልጋል፣ እጅግ ትንሽ የሆነ የፍቅር ተግባራችን ለሁላችን መልካም ውጤቶች አሉት፣ ስለዚህ የቤተ ክርስትያን አንድነትን በእውነት ለመኖር ከተፈለገ የገዛ ራስ ጥቅምን መፈለግ ሳይሆን የወንድማሞቻችን ኃዘንና ደስታን መካፈል ያስፈልጋል (1ቆሮ 12፤26) የደካሞችና የድሆች ሸክምን ለማቃለል ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል፣ ይህ ወንድማማዊ መተባበር ለጣዕመ ነገር ተብሎ በንግግር ብቻ የሚደረግ አይደለም ነገር ግን የክርስትያኖች ሱታፌ ዋና ክፍል ነው፣ ይህንን በእውነት እተግባር ላይ ያዋልነው እንደሆነ እኛ የእግዚአብሔር ቅዱሳት ምስጢራት ሕያው ምልክት ሆነናል ማለት ነው፣ አንዱ ለሌላው እንዲሁም ለሁላቸው ምልክት እንሆናለን፣ ይህ ፍቅር የአድርግልኝ ላድርግልህ ዓይነት ሳይሆን እጅግ ጥልቅ የሆነ በሌሎችን ደስታና ስቃይ ገብተን የእኛ ደስታና ስቃይ እስኪሆኑ ድረስ የሚገፋፋ ፍቅር ነው፣
አብዛኛውን ጊዜ በጣም የደረቅን ግድ የለሾች ወንድማማችነትን ከማስፋፋት ይቅር ተነጥለን ጥላችን ቀዝቃዛነትን ራስ ወዳድነትን እናስፋፋለን፣ በጥላቻ ቀዝቃዛነትና ራስ ወዳድነት ቤተ ክርስትያንን ለማዳበር ይቻላልን? አይመስለኝም፣ አይቻልም! ከመንፈስ ቅዱስ በሚመጣ በፍቅር ብቻ ነው ቤተ ክርስትያንን ልናዳብር የምንችለው፣ እግዚአብሔር በቅዱሳት ምሥጢራቱ በስጦታዎቹና በምግባረ ሰናይ ክርስትያናዊ ጥሪ አችን እንደሚገባ ለመኖር ከእርሱ ጋር አንድ ለመሆን ልባችንን እንድንከፍ ጥሪ ያቀርብልናል፣ አሁን አንድ የፍቅር ስራ ልጠይቃችሁ ፍቀዱልኝ? አትጨነቁ ገንዘብ አልጠይቃችሁም! አንድ የፍቅር ስራ ነው! ወደዚህ ወደ አደባባዩ ከመምጣቴ በፊት አንድ ዓመት ተኩል ዕድሜ ያላት በጸና የታመመች ሕጻን ለማየት ሄድኩኝ እናትዋና አባትዋ እየጸለዩ ናቸው ጌታ ለዚህች ቆንጆ ልጃቸው ጤና እንዲሰጣት እየለመኑ ናቸው፣ ኖአሚ ትባላለች፣ ፈገግታዋ ደስ የሚያሰኝ ነው፧ አሁን አንድ የፍቅር ስራ እናድርግ እኛ አናውቃትም ግን የተጠመቀች ሕጻን ናት ክፍላችን ናት ክርስትያን ናት፣ በጸጥታ ስለእርሷ እንጸለይ እግዚአብሔር በዚሁ ከባድ ጊዜ እንዲረዳትና ጤናም እንዲሰጣት በጸጥታ እንጸልይ በመጨረሻም በሰላመ ገብርኤል መልአክ አብረን እንደግማለን፣ አሁን አብረን እመቤታችን ድንግል ማርያምን ለኖ አሚ ጤና እንድታስገኝልን እንለምናት ለዚሁ የፍቅር ስራ አመሰግናችኋለሁ፣







All the contents on this site are copyrighted ©.