2013-11-06 15:57:41

የቤተሰብ ጉዳይ የሚመክረው ሲኖዶስ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚነካ ጥያቄ በሙላት ለውይይት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በአስፍሆተ ወንጌል ይዘት” ዙሪያ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ሊመክር የተጠራው ጠቅላይ ሲኖዶስ በተመለከተ በቅድስት መንበር የዜናና ኅተምተ ጉዳይ የሚከታተለው ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በአሁኑ ወቅት በመታየት ላይ ያለው ማህበራዊ መንፈሳዊ ቀውስ በቤተሰብ ውስጥ የሚያስከትለው ችግር ለቤተ ክርስቲያን ወቅታዊው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ ከመሆኑም ባሻገር ቤተ ክርስቲያን ይኽ ችግር በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መስክ እንዴት ባለ መልኩ ገጥማ በአስፍሆተ ወንጌል ለመወጣት ለቤተሰብ በሰበካዎችና ቁምስናዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሠረት በተዋጣለት መንገድ ለማገልገል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይላሉ የሲኖዶሱ ቅድመ ዝግጅት ሰነድ ለማጠናቀር ታልሞ የተደረሰው መጠይቃዊ ሰነድ በማስደገፍ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር ያደረጉት የሲኖዶስ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ሎረንዞ ባልዲሰሪ፦ “ሲኖዶሱ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ማሳሰቢያ አማካኝነት በኵላዊት ቤተ ክርስትያን በሁሉም መስክ እውነተኛና ስኬታማ ኁባሬአዊነት እንዲኖር የሚያደርግ እንዲሆንና ይኽ ደግሞ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልዩና ጥልቅ ፍላጎት ነው። ይኽም የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መሥተዳድር ከጴጥሮስ ጋር በቅዱስ ጴጥሮስ መሪነት ሥር የሚል ኁባሬአዊነት በሙላት ለማረጋገጥ ከሚለው የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አመለካክት ጋር ጥልቅ ትሥሥር ያለው ሲኖዶስ ነው” ብለዋል።
ስለዚህ ይላሉ ብፁዕነታቸው፦ “የሲኖዶሱ የሥራ ማስፈጸሚያ ሰነድ በመላ ዓለም ለሚገኙት ብፁዓን ጳጳሳትና የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ይተላለፋል” ብለው የወይለስና እንግልጣር ብፁዓን ጳጳሳት የሲኖዶስ መጠይቅ በድረ ገጽ ታትሞና ይፋ ሆኖ እንዲሰራጭ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ በማስደገፍም፦ “በርግጥ በሁሉም ብፁዓን ጳጳሳትና የሁሉም አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች አማካይነት በነጻነት የሲኖዶሱ ሥራ ማካሄጃ የሚሆነው ሰነድ ለመወጠን መጠይቁ ይተላለፋል የሚሰጡት ምላሽ በተፈለገው መልኩ ለማስተላለፍ ይችላሉ” ካሉ በኋላ፦ “ቤተሰብ ከእግዚአብሔር ፍላጎት የመነጨ በማኅበራዊ ተጨባጭነት የሚጸና ነው። ስለዚህ የማኅበራዊና ሰብአዊ ፍላጎት ያጸናው ሳይሆን በክርስቶስ ጌታ በመለኮታዊ ጸጋ ይዘት ከፍ እንዲል የተደረገ ተጨባጭ ባህርይ ነው” ብለዋል።
የዚሁ የቤተሰብ ጉዳይ የሚመክረው ሲኖዶስ ልዩ ጠቅላይ ዋና ጸሐፊ የቲዮሎጊያ ሊቅ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ በበኩላቸውም፦ “ቤተሰብ የተደቀነበት ፈተና ችግር እክል በጠቅላላ ወቅታዊው ዓለም የሚያቀርብበት ተጋርጦ አጢኖ ይኽም በቤተሰብ ጉዳይ በተመለከተ የሚሰማው የሚባለው የሚቀርበው አዲስ አመለካከት ሁሉ ካል ምንም ፍራት በመወያየት ታማኝነት ባለው ተግባር የእግዚአብሔር ምኅረትና ለእግዚአብሔር ጥሪ በሚሰጠው ምላሽ ያለው ውበት ለመመስከር የተጠራ ሲኖዶስ ነው” ካሉ በኋላ አያይዘውም፦ “በኁባሬአዊነት የሚካሄደው ውይይት ግልጽ ነው። ምክንያቱ የሲኖዶስ የሥራ ሰነድ ግልጽ ነው የሚካሄደው ውይይት ጥልቅ እንደሚሆን የተርጋገጠ ነው። ሆኖም በኁባሬአዊነት የሚሰጠው ሃሳብ መሠረት ድህረ ሲኖዶስ ሥልጣናዊ ምዕዳን የሚሰጡት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ናቸው ስለዚህ ከሳቸው ጋርና በሳቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ መሪነት ሥር የሚከናወን ነው። ብዙኃን ወይንም አብላጫ የብዙሃኑ አስተሳሰብ ይሁን የሚባልበት ሳይሆን የቅዱስ ጴጥርስ ጥልቅ የምርምርና የአስተንትኖ ውሳኔ ይሁን የሚባልበት በሳቸው በመመራት በሚሰጡት ምዕዳንና ምክር ሥር የመላ ቤተ ክርስቲያን በብፁዓን ጳጳት ውሳኔ የሚሰጥበት ኁባሬ ነው ብለዋልብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.