2013-11-06 15:57:32

ሲኖዶስ
የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በአስፍሆተ ወንጌል ይዘት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. እንዲካሄድ የጠሩት ሦስተኛው ጠቅላይ ጉባኤ የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ርእሰ ጉዳይ፦ የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተጋርጦ በአስፍሆተ ወንጌል ይዘት” የሚል እዲሆን ውሳኔ ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ቀደም በማድረግ ባሰራጨው መግለጫ ለመረዳት መቻሉ የሚዘከር ሲሆን ይኽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጠሩት ልዩ ሲኖዶስና የሚከተለው ርእሰ ጉዳይ ወቅታዊው ማህበራዊና መንፈሳዊ መቃወስ ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አቢይ ተጋርጦ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰብ የቤተ ክርስቲያን የወንጌላዊ ተልእኮ እጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑ የተጠራው የዚሁ ሲኖዶስ የሥራ ሰነድ ሲያመለክት፣ አለ ቃል ኪዳን የሚመሠረተው ግብራዊ ጣምራ አንድ ዓይነት ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚጸናው ጥምድ የመሳሰሉት እየተጋባ ያለው አዲስ ዓይነት ጣምራ እንዲሁም ቤተሰብ ለሚለው ቃል የሚሰጠው አዲስ ትርጉም እናት የመቀያየር ይኽም ከማሕጸን ጋር በተያያዘ ጉዳይ ማሕጸን የማከራየት ባህል የሚያስገባው አመለካከት፣ ከተስማማን እንቀጥላለን ካልሆነ እንለያያለን የሚል ቅድመ ሁኔታ የሚያስከትል ዓይነት ጋብቻ የመሳሰሉት አዳዲስ አመለካከቶችን የሚዳስስ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥም ይኽም ምእመናን በእምነት መዛል ምክንያት እየተዛመተ በመሄድ ላይ ያለው የተክሊል ሚሥጢር መዘንጋት አቢይ ግምት የሚሰጥ ሲኖዶስ እንደሚሆነ የተጠራው የሲኖዶሱ ሰነድ ይጠቁማል።
አስፍሆተ ወንጌል በቤተሰብ ባለ ትዳሮች ምንም’ኳ ምድራዊ ሕይወት ፈተና የማይለው ቢሆንም ቅሉ ሚሥጢረ ተክሊል ያለው ውበት መስካሪያን ለመሆን የተጠሩና እናትነትና አባትነት መንፈስ የሚጎላበት በእግዚአብሔር የመፍጠር ባህርይ የመሳተፍ ጥሪ የሚኖርበት የልጆች መንፈሳዊ ሰብአዊ እድገትና ሕንጸት በሙላት የሚረጋገጥበት መሆን አለበት የሚለው የቤተሰብ ባህርያት በጠቅላላ ውይይት የሚደረገበት መሆኑ የገለጠው የሲኖዶሱ የሥራ ሰነድ ለማሰባሰብ የሚደገፍ ሰነድ አክሎ፣ የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ Familiaris Consortio-ቤተሰብአዊ ባልንጀራ (ሸሪክ)” በሚል ርእስ ሥር ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚያትተው ሓዋርያዊ ምዕዳን፦ እግዚአብሔር ቤተሰብ በአርአያውና አምሳያው ፈጥሮ በዚህ መልክ አቅቦም እግዚአብሔር በሰብአዊነት ዘንድ የተባዕትና የአንስት ጾታዊ ጥሪ ይቀርጻል፣ የፍቅርና የሱታፌ ብቃትና ኃላፊነት እንዲታቀብ ያደርጋል” የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብም፦ “ቃል ኪዳናዊ ሚሥጢር አማካኝነት ወንድና ሴት በሚኖሩት በእግዚአብሔር የጸናና የታደለ ውስጣዊ የሕይወትና የፍቅር ሱታፌ አማካይነት ቅዋሜ ያለው ነው” ሲል በዓዋዲ መልእክት Lumen Fidei-ብርሃነ እምነት” ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ሚስጢረ ተኪል ፍቅር ለሁሉ ጊዜ የሚባልበት…መላ አንተነትህን ላፈቀርከው ሰው ለመስጠት ቃል የሚገባበት ቃል የተገባው ለሁሉ ጊዜ የሚል ፍቅር የሚኖርበት ነው” በማለት እንደገለጡት በማብራራትም በጠቅላላ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ግብረ ኖልዎ የተደቀነበት ተጋርጦ ዙሪያ በመወያየት መልስ ለመሰጠት የተጠራ ሲኖዶስ መሆኑ ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.