2013-11-04 17:19:21

ክፋት በእግዚአብሔር ፍቅር ፊት ምንም ኃይል የለውም፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በዚሁ ዓመት ስለሞቱት ካርዲናሎችና ጳጳሳት መሥዋዕተ ቅዳሴ አስርገዋል፣
በዚሁ ቅዳሴ ባደረጉት ስብከት ደግሞ ያለፉትን ካርዲናሎችና ጳጳሳት በማስታወስ “ለጥሪአቸው ታማኝ ሆነው የተገኙና ሁለመናቸውም ለቤተ ክርስትያን አግልግሎት የሰው ሰዎች” መሆናቸውን ካሳሰቡ በኋላ ያበረከቱት አገልግሎት ለሁል ጊዜ በቤተ ክርስትያን ተመዝግቦ እንደሚጠበቅና ነፍሶቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደሆኑ ገልጠዋል፣
የክርስትያን ተስፋ የማይሸነፍ ነው ምክንያቱም የመጣ ቢመጣ የክፋት ኃይል በእግዚአብሔር ፍቅርና በሰው ልጅ መካከል ያለውን ትሥስር ሊያሸንፈው አይችልምና፣ ሞት የጥፋት ወይም የውድቀትና የሽንፈት ድልድይ ሳይሆን ወደ ሕይወት የሚያሸጋግርና ወደ ሕይወት ለመግባት የሚያሳልፍ በር መሆኑንም ገልጠዋል፣ ቅዱስነታቸው ይህንን መተማመን ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ሆነው “ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ። ሲሉ ገልጠውታል፣
“የሰው ልጅ ጠላቶች የሆኑ የሠይጣን ኃይሎችም ቢሆኑ በኢየሱስና እርሱን በእምነት ከሚቀበል መካከል ያለውን ጥልቅ የፍቅር ውህደት ኃይለ ቢስ ይሆናሉ፣ ይህ ታማኝ የፍቅር ሁኔታ እያንዳንዳችን በየእለቱ በምናደርገው የሕይወት ኑሮ ጉዞ በተረጋጋ መንፈስና በኃይል እንድንጓዝ ያደርገናል፣ ምናልባት አንዳንዴ አድካሚና ዘገምተኛ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በዚሁ ፍቅርና ኃይል ሁሉ ብድል አድራጊነት ሊፈጸም ይችላል፣ ይህንን ትሥስር እንዲቋረጥ ሊያደርገው የሚችል የሰው ልጅ ሓጢአት ብቻ ነው ነገር ግን እዚህም ቢሆን እግዚአብሔር ሁሌ ኃጢአተኛ እንዲመለስ እየተጠባበቀና እየፈለገው አግኝቶም ግንኝቱ እንደገና እንዲተሳሰርና አንድ እንዲሆን ይህም በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ከሞት ባሻገርም በልጅና አባት ግኑኝነት ፍጻሜው በማግኘት ግቡን እንዲመታ ይሻል፣ እርግጥ ነው አንድ የምንወደው ሰው ጥሩ አድርገን የምናውቀው ሲሞት ይከብዳል፤ ምናልባትም ሕይወቱ እንዴት ይሆን ይሆናል ከርሱ በኋላ ስራው እንዴት ይሆናል ቤተ ክርስትያንስ አገልግሎቱን እንዴት ትተከዋለች ብለንም እንጨነቅ ይሆናል፣ የዚህ መልስ በመጽሓፈ ጥበብ እናገነዋለን ሁሉም በእግዚአብሔር እጅ ነው ይለናል፣ በታማኝ እጅ መሆንና መኖር ማለትም ለመቀበልም ይሁን ለመከላከልም ይሁን እርግጠኝነት የሚሰጥ ነው፣ ጥልቅ በሆነ ግላዊ ግኑኘትና መተመማመን ይመሰረታል፣
“እነኚህ ቀናተኛ እረኞች ሕይወታቸውን ለጓደኞች አገልግሎትና ለእግዚአብሔር የሰው በእግዚአብሔር እጆች ናቸው፣ ያደረጉት መልካም ነገር ሁሉ ተመዝገቦ ነው ያለው በሞትም አይደመሰስም፣ በደስታና በኃዘን የተፈራረቁ በተስፋና በድካም የተፈራረቁ ሕይወታቶቻቸው እንዲሁም ለመንፈሳዊና ለስጋዊ የመንጋዎቻቸው ደህንነት የነበራቸው ብርቱ ስሜትና በወንጌል የነበራቸው መተማመን ሁሉ በእግዚአብሔር እጆች ናቸው፣ እነኚህ ካርዲናሎችና ጳጳሳት አንድ ሙሽራ ሙሽራዪቱን በሚያፈቅራት ፍቅር ዓይነት ቤተ ክርስትያንን ያፈቀሩና ጥሪ አቸውንና አገልግሎታቸውን ለእርሷ ያበረከቱ ናቸው፣ ለዚህ ፍቅር መልስ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፣ ምንም እንኳ ድካምና ትግል ቢኖርም እነዚህም በእግዚአብሔር እጆች ናቸው፣
“ኃጢአቶችም ሳይቀር ኃጢአቶቻችንም ሳይቀሩ በእግዚብሔር እጆች ናቸው፣ እነኚህ በይቅር ባይነት የሞሉ እጆች እነዛ በቀራንዮ በፍቅር ችንካር የተቸነከሩ ናቸው፣ ስለዚህም ነው ኢየሱስ ቅንዋቶችን በእጁ ተሸክሞ ያኖራቸው ይቅር ባይነቱን ሊያሳስበን ስለፈለገ ነው፣ ተስፋችንና ኃይላችንም ይህ ነው፣ ይህ ብተስፋ የተሞላ እውነት የትንሣኤ ሙታን የዘለዓለም ሕይወት አመልካች ነው፣ ጻድቃን ሁላቸውም ማለትም ቃለ እግዚአብሔርን የሚቀበሉና ለመንፈሱ በትሕትና የሚታዘዙ ሁሉም ለዚህ የተወሰኑ ናቸው፣ ሲሉ ስብከታቸውን ከደመደሙ በኋላ ለሞቱት ብቻ ሳይሆን ገና በሕይወት ስላለን ስለእኛም ጸሎት እንደሚያስፈልግ እንዲህ ሲሉ አሳስበዋስ፣“ጌታ ለዚሁ ግኑኝነት እንዲያዘጋጀን ስለገዛ ራሳችንም እንጸልይ፣ ሰዓቱንና ግዜውን አናውቀውም ግን በእርግጥ ከእርሱ ጋር እንገናኛለን ሲሉ አሳስበዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.