2013-11-04 17:17:11

ከእግዚአብሔር ልብ ሊፍቀን የሚችል ኃጢአት ከቶ አይገኝም! ኢየሱስ እንዲለወጥን እንፍቀድለት፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት አስተምህሮ “ከእግዚአብሔር ልጆች አንድን እንኳ ከእግዚአብሔር ዝክርና ከእግዚአብሔር ልብ ሊፍቅ የሚችል ኃጢአት ወይንም ወንጀል ከቶ አይገኝም!” ሲሉ ስለ እግዚአብሔር አሳቢነትና ፍቅር እንዲሁም ይቅር ባይነት በሰፊው አስተምረዋል፣ በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና የትነበበው የወንጌል ክፍል ከሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ሲሆን ስለዘኬውስ እንዲህ ይላል “ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ። ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው። በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና። ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው። ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው። ሁሉም አይተው። ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ ብለው አንጐራጐሩ። ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው። ኢየሱስም። እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤ የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።” የሚለውን ታሪክ መሠረት በማድረግ በቍመናውም ይሁን በተግባሩ ከሰውና ከእግዚአብሔር ርቆ የነበረው ዘኬዎስ ድኅነት ማግኘቱ እግዚአብሔር እያንዳንዱ ኅጢአተኛ ወደ እርሱ እንዲመልስ ምንኛ ያህል እንደሚፈልግና እንደሚጠባበቀን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ይህ ኢየሱስ ወደኢየሩሳሌም ሲሄድ በኢያሪኮ የተፈጸመው የኢየሱስ ጉዞ የአጠቃላይ የኢየሱስ ሕይወትና ተልእኮ የመጨረሻ ምዕራፍ የያዘ ነው፣ ይህም ከቤተ እስራኤል የጠፉትን በጎች የመፈለግና የማዳን ሥራ ያመለክታል፣ ሆኖም ግን ተል እኮው ፍጻሜ ላይ ሊደርስ ሲል ኢየሱስን ከበው ከነበሩ ሰዎች ጥላቻ ሲነሳ ይታያል፣ ኢየሱስ ግን ይህንን ተልእኮ እላይ በሰማነው ታሪክ የዘኬዎስ መለወጥ ይፈጽመዋል፣ ዘኬዎስ ጠፍታ የነበረች በግ ቀረጥ ሰብሳቢ በመኖሩም በሁሉም ዘንድ የተጠላ ምክንያቱም ከጠላቶቻቸው ከሆኑ ሮማውያን ጋር በመተባበር ከሕዝቡ ቀርጥ እየሰበሰበ ለጠላቶች በመስጠቱ እንደ ሌባና አወናባጅ ይታይ ነበር፣ በዚህም ወደ ኢየሱስ ለመቅረብ ያስፈራው ነበር ሌላው ችግሩ ደግሞ ቁመናው ነበር እጅግ አጭር በመሆኑ ቢያንስ ኢየሱስን በሩቅ ለማየት ወደ ሾላ ያ ወጣ፣ ይህ የበስተውጭ ሁኔታ አስቂኝ ሊመስል ይችላል ነገር ግን በውስጡ ያለው ግፊት ነው ኢየሱስን ለአንድ አፍታ ለማየት የገፋፋው፣ ዘከዎስ ራሱ የዚሁ ጥልቅ ተግባር ትርጉም አያውቅም ነበር በእርሱና በኢየሱስ መካከል የነበረው ርቀትም በእንዲህ ዓይነት የሚቆጭ አልመሰለውም፣ ሲያልፍ እንዲያየው ብቻ ይሻ ነበር፣
“ሆኖም ግን ኢየሱስ በዛፉ አጠገብ በደረሰ ጊዜ በስሙ ይጠረዋል፣ ዘኬዎስ ሆይ! ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ ይለዋል፣ ያ አጭር ሰውየ ያ ሰዎች ሁሉ ያራቁት ከኢየሱስም እጅግ ርቆና እንደማንኛው ጠፍቶ የነበረውን ሰው ኢየሱስ በስሙ ይጠረዋል፣ ዘኬዎስ የሚለው በዛኛው ጊዜ ቋንቋ ቆንጆ ትርጉም አለው፤ ዘኬዎስ ማለትም እግዚአብሔር ይዘክራል ያስታውሳል ማለት ነው፣ በዚህም ኢየሱስ ከበውት የነበሩ ሰዎች አመለካከትና ተቋውሞ በከተማው የሚገኙ ፍጹማን ወይም ስመ ጥር ጋር ከመዋል ከዘኬዎስ ጋር ከአንድ መጸባሓዊ ጋር ለመዋል ወሰነ፣ ምክንያቱም ያኔም ሕሜትና ስም ማጥፋት ነበርና፣ ለዚህም በወንጌል እንደሰማነው ኢየሱስ መልስ ይሰጣቸዋል፣ ዘኬዎስ ጠፍቶ በመኖሩ እርሱም የአብራሃም ልጅ ስለሆነ ከዛሬ ወዲህ በቤቱ በሕይወቱ ደስታ ይገባል ይላቸዋል፣
“ከእግዚአብሔር ልጆች አንድን እንኳ ከእግዚአብሔር መዘክር ወይንም ልብ ሊፍቀው የሚችል ኅብረተሰባዊ ስልጠና ወይንም ሁኔታ ወይንም ኃጢአት ወይንም ወንጀል ከቶ የለም፣ እግዚአብሔር ሁሌ ያስታውሳል ይዘክራል! ከፈጠራቸው ማንንም አይረሳም፣ እርሱ አባት ስለሆኑእ በልጆች ልብ ውስጥ ወደ አባታቸው ቤት የመመለስ ፍላጎት እንዲፈልቅ ሁሌ በፍቅር እየተጠባበቀ ነው፣ የዚህ ዓይነት ፍላጎት እንደተፈጠረም እንዲያው ትንሽ ብልጭታም ይሁን ወዲያውኑ በርኅራኄው በጉኑ በመሆን በይቅር ባይነቱ የንስሓውና ወደ አባት ቤት የመመለሱን ጉዞ ይደግፋል፣ የዘኬዎስ ሁኔታ አስቂኝ ሊመስል ይችላል ሆኖም ግን የድኅነት ተግባር ነው፣
“እኔም ላንተ የምልህ ይህ ነው! በኅልናህ የሚከብድህ ነገር ያለ ሆኖ የሚሰማህ ከሆነ ከአሁን በፊት የፈጸምካቸው ኃጢአቶች ያስፈሩህ እንደሆነ አንዴ ቁም! አትደንግጥ! የሚጠባበቅህ አንድ እንዳለ አስታውስ! ምክንያቱም ይህ ስላተ የሚያስብ አንተን ከማስታወስ አቍሞ አያውቅም ሁሌ ስላንተ እያሰበ ነው ይህም አባትህ ነው እግዚአብሔር ነው የሚጠባብቅህ ያለው፣ ዘኬዎስ እንዳደረገው ወደ ላይ ውጣ ምሕረት ጠይቅ ይህ ፍላጎት ይኑርህ፣ እንዲህ በማድረግህ እንደማትጸጸት አረጋግጥላሃለሁ፣ ኢየኡስ ይቅር ባይ ነው ይቅር ለማለትም ከቶ አይሰለችም፣ እንድታስታውሱት ይሁን ኢየሱስ እንዲህ ነው፣ ስለዚህ ዛሬም እንደዘኬዎስ ኢየሱስ በስማችን እንዲጠራን እንፍቀድለት፣ እኛም ልክ እንደዘኬዎስ ዛሬ በቤትህ እውላለሁ በሕይወትህ ውስጥ እገባለሁ በልብህ ውስጥ እኖራለሁ የሚለንን ጌታ እንስማው፣
“በደስታ እንቀበለው እርሱ ሊለውጠን ይችላል ልባችንን ከድንጋይ ልብ የሥጋ ልብ ሊያደርገው ይችላል ለግል ጥቅማችን ከመሯሯጥ አድኖ ሕይወታችንን የፍቅር ስጦታ ሊያደርጋት ይችላል፣ ለኢየሱስ ይህ ይቻለዋልና ኢየሱስ እንዲመለከተን እንፍቀድለት፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.