2013-11-01 15:51:11

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የእግዚአብሔር እንክብካቤ፣ ለድኾች የክርስቶስ ፍቅር ምልክትና ምስክር ሁኑ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 31 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 200 የቅዱስ ጴጥሮስ ማኅበር አባላት በአገረ ቫቲካን ቅዱስ ቀለመንጦስ የጉባኤ አድራሽ ተቀብለው ማኅበሩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በጠና ድኽነት ለሚገኙት ለምታከናውነው አገልግሎት ደጋፍ መሆናቸውና በዚሁ የግብረ ሠናይ መስክ በሚያከናውኑት ቅዱስ ተግባር እርሱም ከሮማ ጳጳስ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ያላቸው ጽኑ ሱታፌ ምስክር የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በሮማና አካባቢ በድኽነት ለሚገኘው የኅብረተሰብ ክፍል መርጃ በሚል ዓላማ ምጽዋት የማሰባሰቡ መርሃ ግብር ጥንታዊው ባህል በሮማ ሰበካ እግብር ላይ በሚያውል አገልግሎታቸው ከልብ ማመስገናቸው የተካሄደው ግኑኝነት የተከታተሉት የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ ኣኵይላኒ አስታወቁ።
የሚኖረው እውነተኛው እምነት እውነተኛው የፍቅር አገልግሎት ይኽም በግብረ ሠናይ አገልግሎት ለመጠመድ የሚቀሰቅስ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ ያለው የእምነት ዓመት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላት እምነትና በእርሱ መንገድ መጓዝ ያለው ደስታ ዳግም ሕያው ማድረጓንም ሲገለጡ፦ በቤተሰቦቻቸው ውስጥ በትምህርት ቤቶች በቁምስናዎች በሥራ ቦታ በተለያዩ የማሕበራዊ ግኑኝነቶች ጉዳይ በጎዳናዎችም ጭምር ባልተወሳሰበ ምስክርነት የግብረ ሠናይ ሐዋርያት የሆኑት ብዙ ሰዎች አሉ። እነዚህ ወንጌልን በምር ጠበቅ በማድረግ ባሳቢነት የሚኖሩ ናቸው። እውነተኛው የጌታ ሐዋርያት የተለያየው ኅብረቅርጽና ማለቂያ የሌለው ሰብአዊ ድኽነት አድማስ ባደረገ በግብረ ሠናይ የተልእኮ አገልግሎት ተጠምዶ የሚያገለግል ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዚህ የቅዱስ ጴጥሮስ ማኅበር ተግባርና አገልግሎት የቤተ ክርስቲያን የግብረ ሠናይ አገልግሎት ደጋፊ መሆኑ በማስታወስ፣ ምሉ እውቅና በመስጠት ይኽ እ.ኤ.አ. በ 1869 ዓ.ም. የተቋቋመው ማኅበር አባላት ወደ ተናቁት ወደ ተረሱት ከከተሞች ውጭ በሚኖረው በተገለለው ኅብረሰብ ዘንድ ተሠማርተው የሚያገለግሉ ይኽም የአልፎ አልፎና ወይንም ልዩ ተልእኮ የሚል አገልግሎት ሳይሆን ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበልክ በመሆን ላይ ባለው ዕለት በዕለት ቤተ ክርስቲያንን የቤተ ክርስቲያን አባልነት መለያ መኖር ማለት መሆኑ ሲገለጡ፦ “ዕለት በዕለት የተለያዩ ውስጣችንን የሚነኩ ውስጣዊ ጥያቄ የሚያቀርቡ ኅሊናችን የሚነኩ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፣ ይኽ ማለት ደግሞ እያንዳንዳችን ዕለት በዕለት አጽናኞች ለእግዚአብሔር አሳቢነትና ለመልካም ማኃሪነት የሚረዳንና በስቃያችን ሁሉ ሱታፌ ላለው ፍቅሩ ከወደቅንበት የሚያነሳን ብርታት ለሚሆነን አጽናኝነቱ መገልገያ ትሁት መሣሪያዎች መሆን ማለት ነው። ዕለት በዕለት የዚህ የእግዚአብሔር ፍቅርና ተንከባካቢነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተመክሮ ለሚያደርጉ ፈጽመው ይኸንን አሳቢነት ለማይዘነጉ በሕይወታቸው ይኸንን የእዚአብሔር ተንከባካካቢነት ከዚህ ቀደም ፈጽመው ሰምተው ለማያውቁ ሁሉ የዚህ የእግዚአብሔር አሳቢነት ለመመስከር የተጠራን ነን፣ ስለዚህ በምትሰጡት አገልግሎት ምክንያት ላመሰግናችሁ እወዳለሁ” ብለው፦ “በሮማ ከተማ ለሚገኙት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት የሮማ ጳጳስ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለሚያከናውኑት የትብብና የድጋፍ መርሃ ግብር ተባባሪዎች መሆናችሁ የማኅበሩ አባልነት መለያችሁ ነው። ይኸንን አገልግሎት በመለኮታዊ ፍቅር ተከታዮች በመሆን በጸሎትና የእግዚአብሔር ቃል ከማዳመጥና ከመኖር የሚመነጭ ከዚህ ፍቅር በምታገኙት ብርታት ወደ ወንድሞች በመሄድ የምትሰጡት አገልግሎት ትቀጥሉበት ዘንድ አደራ” ብለው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.