2013-10-30 18:53:13

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ሰላም እንደምን አደራችሁ! ዛሬ የእምነታችን እጅግ መልካም የሆነች ነገር በቅዱሳን ሱታፌ አምናለሁ የሚል የጸሎተ ሃይማኖት ክፍል ነው፣ በአዲሱ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ቍጥሮ 948 ላይ ይህ ሁኔታ ሁለት ነገሮች እንድሚያመልክት ይገልጣል፣ በቅዱሳን ነገሮችና በቅዱሳን ሰዎች መካከል የሚሉ እጅግ የተቀራረቡ ትርጉሞች አሉት በማለት ይተነትነዋል፣ በሁለተኛው ትርጉም ለማትኰር እወዳለሁ፣ ይህም እጅግ አጽናኝ ስለሆነ የእምነታችን እውነታዎች ይናገራል፣ ለብቻችን አለመሆናችንን ብቻ አይደለም የሚገልጠው ነገር ግን የክርስቶስ በሆኑ አካሎች ሁሉ የሱታፌ ሕይወት እንዳለ ያረጋግጥልናል፣ ይህ ሱታፌ ከእምነት ይወለዳል፣ ስለሆነም ቅዱሳን የሚለው ቃል ብጌታ ኢየሱስ የሚያኑትን ሁሉ እና በጥምቀት አማካኝነት ከቤተ ክርስትያን ጋር የተውሃሃዱትን ያመለክታል፣ ለዚህም የመጀመርያዎቹ ክርስትያኖች ቅዱሳን ተብለው ይጠሩ ነበር (የሓ 9፤13.32፤41፣ ሮሜ 8፡27፣ 1ኛ ቆሮ 6፤1)
    የዮሐንስ ወንጌል ኢየሱስ ከሕማማቱ በፊት አባቱን በሓዋርያቱ መካከል ውህደት እንዲኖር እንዲህ ሲል እንደተማጠነ ያመልክታል፣ “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።” (17፡21)፣ ቤተ ክርስትያን ጥልቅ የሆነ እውነታዋ ከእግዚአብሔር ጋር ውህደት ነው ይህ ውህደትም በክርስቶስ በእግዚአብሔር አብና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ባለው የፍቅር ውህደት የተመሠረተ ነው እስከ የወንድማሞች ውህደት ይደርሳል፣ ይህ በኢየሱስ ክርስቶስና በእግዚአብሔር አብ መካከል ያለው ግኑኝነት የእኛ ክርስትያኖች የክርስትያኖች ከፍተኛ መተሳሰር ምንጭ ነው፣ ጥልቅ በሆነ መንገድ በዚሁ መተሳሰር የገባን እንደሆነ በዚሁ የቅድስት ስላሴ እጅግ የሞቀ ይፍቅር መተሳሰር የገባን እንደሆነ እውነትም አንድ ልብ ብቻና አንድ ነፍስ ብቻ ለመሆን እንችላለን ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍቅር በእያንዳንዳችን ያሉትን የግል ስሜቶች ቅድመ ፍርዶች እንዲሁም ከበስተውስጥነ ከበስተውጭ በኩል የሚፈልቁ ልዩነቶችን ያቃጥላልና፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ኃጢአቶቻችንንም ያቃጥላል፣
    የፍቅር ምንጭ በሆነው በእግዚአብሔር የተመሠረትን እንደሆነ ከወንድሞች ወደ እግዚብሔር ውህደት ለመድረስ እንችላለን፣ ማለትም ከወንድማማዊ ሱታፌ ከእግዚአብሔር ጋር ሱታፌ እንዲኖረኝ ያደርገኛል ወይም ወደ እግዚአብሔር ውህደት ያሸጋግረኛል፣ እርስ በእርሳችን የተወሃሃድን እንደሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ለመወሃሃድ ያስችለናል ይህም አባታችን ከሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ትሥስር እንዲኖረን ያደርጋል፣ እምነታችን የሌሎች እርዳታ ያስፈልገዋል አንዱ ከሌላው ጋር ስለሚጠጋ መጠጊያ ያስፈልገዋል በተለይ ደግሞ በአስቸጋሪ ግዝያት መጠጊያ አስፈላጊ ነው፣ አንድ የሆንን እንደሆነ እምነት ኃይል ያገኛል፣ አንዱ ሌላውን ሲደግፍ እንዴት መልካም አስደናቂው የእምነት ሂደትም ይህ ነው፣ ይህንን የምልበት ምክንያት ደግሞ በገዛ ራስ ብቻ ተዘግቶ ገለልተኛ መሆን በገዳማትም ሳይቀር ሰርጎ እየገባ ስለሆነ ነው በዚህም ምክንያት አብዛኛውን ጊዜ አንድ እምነት ከሚከተሉ ወገኖቻችን እርዳታን ለመጠየቅ እያስቸገረ ነው፣ እስቲ ወደ ገዛ ራሳችን መለስ ብለን እናሰላስል ከኛ ከሁላችን ከኛ ነው የምለው እስቲ ማን አለ ፍርኃት ያልወረረው እንደ ጠፋ ሆኖ ያልተሰፋው በእምነቱ እስከ መጠራጠር ያልደረሰ ማን አለ? ሁላችን የዚህ ዓይነት ችግር አጋጥሞናል፣ እኔም አጋጥሞኝ ነበር፣ ይህ ችግር የእምነት ጉዞ ክፍል ነው እንዲሁም የሕይወት ኑሮ ጉዞ ክፍል ነው፣ ይህ ሊያደንቀን አይገባም ምክንያቱ የሰው ልጅ ፍጥረቶች ነን ምልክታችን ደግሞ ደካማነትና የተወሰኑ መሆን ነው፣ ሁላችን ቀሰስተኞች ነን ሁላችን ጉድለቶች አሉን፣ በእንዲህ ያለ አስቸጋሪ ጊዜ በእግዚአብሔር እርዳታ መተማመን ያስፈልጋል፣ ይህንንም በውሉዳዊ ጸሎት ሲደረግ በሌላ በኩል ደግሞ የሌሎች እርዳታ ለመጠየቅና ልብን ከፍቶ ችግሮችን ለመካፈል ትሕትና ያስፈልጋል፣ እንዲህ ዓይነት ችግር አለኝ እባክህ አግዘኝ ማለት ያስፈልጋል፣ እስኪ ልጠይቅ ይህንን ስንት ጊዜ አደረጋችሁት? ከሁኔታው በኋላስ ከችግሩ ወጥተናል ወይ እንደገና ከእግዚአብሔርስ ተገናኛችሁ ወይ፣ ከእርሱ ጋር ተዋሃህዳችኋል ወይ? መዋሃድ ማለት አንድ መሆን ማለት ነው ሁላችን አንድ እንሆናለን፣ በዚሁ አንድነት ሁላችን አንድ ትልቅ ቤተሰብ ነን፣ በዚሁ ቤተሰብ ሁላችን አንዱ ለአንዱ እንረዳለን አንዱ ለሌላው መጠጊያ እንሆናለን፣
    አሁን ሌላ ነጥብ ለመመልከት ያህል የቅዱሳን ሱታፌ በዚህ ምድር ከምናደርገው ግኑኝነት ባሽገር ከሞት ባሻገር የሚደርስ ሆኖ ለዘለዓለም የሚኖር ሱታፌ ነው፣ ይህ ሱታፌ ከእኛ ባሻገር ይሄዳል በሚመጣው ሕይወትም ይቀጥላል፣ ይህ ውህደት በምሥጢረ ጥምቀት የሚወለድ መንፈሳዊ ስለሆነ በሞትም አይወድምም ነገር ግን ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስ ምስጋና ይድረሰውና ፍጻሜው በዘለዓለማዊ ሕይወት ይገኛል፣ ገና በዚህ ዓለም ሕይወታችን በምንቀጥል ነጋድያን የሆንን እኛና ሞትን ተሻግረው በዘለዓለማዊ ሕይወት የሚገኙ ወገኖቻችን ጥብቅ የሆነና የማያቋርጥ ትሥስር አለ፣ ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ገና በዚህ ዓለም በሕይወት ያሉ እንዲሁም በመካነ ንስሓ ያሉና ብቃት አግኝተው በመንግሥተ ሰማያት ያሉ ሁላችን አንድ ታላቅ ቤተሰብ እናቆማለን፣

ውድ ጓደኞቼ የእምነት ዝክር ጣፋጭነት ይህ ነው፣ የእኛ የሁላችን ሁኔታ ይህ ነው! ሁላችንን ወንድማሞችና እኅትማሞች የሚያደርገንና በዚሁ ምድራዊ ሕይወታችን የሚሸኘን በሰማያም በሚመጣው ሕይወት የምናገኘው ሌላ ሕይወትም የምናገነው ነው፣ በመተማመንና በደስታ በዚሁ ጐዳና እንጓዝ፣ አንድ ክርስትያን ደስተኛ መሆን አለበት፤ ይህ ደስታ የሚፈልቀው ብዙ የተጠመቁ ወንድሞችና እኅቶች አብረው ከእኛ ጋር የሚጓዙ ስላሉን እንዲሁም በዚሁ እስከ ሰማይ የምናደርገው ጉዞ የሚረዱን ገና በሕይወት ያሉና ቀድመውን ሰማይ ያሉ ወንድሞችንና እኅቶቻችን ለኢየሱስ ስለእኛ ስለሚለምኑልን ደስተኞች ነን፣ በዚሁ ጉዳና በደስታ እንገስግስ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.