2013-10-26 08:48:01

ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት “ወንጌሎች፣ ታሪክና ሥነ ክርስቶስ”


RealAudioMP3 ከመላ ዓለም የተወጣጡ ሊቃውንትና ምሁራን ያሳተፈ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት “ወንጌሎች፣ ታሪክና ሥነ ክርስቶስ በቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ስነ ምርምር ይዘት” በሚል ርእስ ሥር የቫቲካን ጆሰፍ ራትዚንገር ማኅበር ያዘጋጀው እ.ኤ.አ. እስከ ጥቅምት 26 ቀን የሚዘልቀው ዓውደ ጥናት ትላትና እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. መከፈቱ በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጥናት በመከታተል ላይ የሚገኙት የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።
ዓውደ ጥናቱ ከተለያዩ 100 መናብርተ ጥበብ የተወጣጡ 450 ድራሳኖች ያካተተ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የ 2013 ዓ.ም. ራትዚንገር ሽልማት ለቲዮሎጊያ ሊቅ ክርስቲያን ሻለርና ለየውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መጋቤ የሎንዶን ንጉሥ መንበረ ጥበብ መምህር ሪቻርድ ብሪድጅ እንደሚሰጡ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘውም፣ በዚህ የሁለት ቀናት ዓውደ ጥናት ሥነ ኢየሱስ ጥናት በወንጌላውያን መሠረትና ቲዮሎጊያ በዚህ የሥነ ኢየሱስና ሥነ ክርስቶስ ጥናት ይዘት ሥር የተከናወኑት ምርምሮች ርእስ ሥር የተለያዩ አስተምህሮና የሥነ ምርምርና የጥናት ውጤቶች ሰፊ ትንታኔ እንደ ሚሰጥባቸው ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.