2013-10-26 08:46:57

ብፁዕ አቡነ ፓሊያ፦ ልቅ ግላዊ መብትና ክብር ውዳሴ ለቤተሰብ መለያየት ጠንቅ ነው


RealAudioMP3 በኢጣሊያ ርእሰ ከተማ ሮማ ጳጳሳዊ የቤተሰብ ጉዳይ የሚከታተለው ምክር ቤት የዚሁ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የቤተሰብ መብትና ክብር ውሳኔ ሰነድ ህትመት ዝክረ 30ኛው ዓመት ምክንያት “አዳዲስ አድማስ ሥነ ሰብእና የቤተሰብ መብትና ክብር” በሚል ርእስ ሥር የጠራው የሦስት ቀናት አውደ ጥናት በዶሙስ ፓቺስ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ማስጀመሩ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ አዳዲስ አድማስ ሥነ ሰብእና የቤተሰብ መብትና ክብር በሚል ርእስ ተመርቶ የተካሄደው አውደ ጥናት ተጋባእያን እ.ኢ.አ. ጥቅምት 26 ና 27 ቀን 2013 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ መቃብር ለመሳለም መንፈሳዊ ንግደት እንደሚፈጽሙ የቤተሰብ ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፅዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የቤተሰብ መብትና ክብር የውሳኔ ሰንድ በማያሻማ መንገድ እርሱም በዚሁ የውሳኔ ሰነድ አስተዋጽዖ እንደተመለከተውም፦ “መሠረታዊው ሕጉ በሰው ልጅ ኅሊና የታተመ ይኽም በታሪክ ታቅቦ ሊከበርና እንክብካቤ የሚያሻው ነው። ስለዚህ የትላንትና ወይንም የሞቶዎች አመታት ውጤት ሳይሆን ዘመናት ያስቆጠረ ቤተሰብ ሕጋዊ አካል መሆኑ የሚያረጋግጥ በሰብአዊ ፍጥረት በኑባሬ ባለው ባህርይ ላይ የጸና ነው። ለግላዊ ሕይወት መሠረት ነው። አለ ‘እኛ-አካል’ ግንዛቤ ማለትም አለ የቤተሰብ ‘እኔ-አካል’ እውቅና ሊያገኝ ያስቸግራል” ብለው፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ማሕበረሰብአዊ ለውጦች መከሰቱና ሆኖም ይህ ተጨባጭ የለውጥ ክስተት ያ የቤተሰብ መብትና ክብር ውሳኔ መታደስ እንደሚኖርበት ምልክት ቢሆንም ቅሉ የሰነዱ መሠረታዊ ነገሩን የሚነካው እንዳልሆነና መሠረታዊው ነገሩ የትላንትና የዛሬም የነገም ቅዉም ነገር መሆኑ አብራርተው ቤተ-ሰብ ክቡር አካል ጥሪ ባለ መብትና ግዴታ አካል መሆኑ ገልጠዋል።
የምንኖርበት ዘመን ልቅ እኔ-አካል’ ወዳሽ በመሆን ‘እኛ-አካል’ እንዲዘነጋ እያደረገ ከመሆኑም ባሻገር ‘ለማኅበርሰብአዊ አካል’ መወገድ ምክንያት ሆነዋል። ስለዚህ ጸረ ቤተሰብ ይሆናል፣ ለከተሞች ማኅበራዊነት የአገሮች ማኅበራዊነትና ለተለያዩ ማኅበራዊ አካሎች ጭምር ወደ ቀውስ የሚያስገባ ነው። ይኽ ለምን ይሆናል ተብሎ ሲጠየቅ፣ እኔ አካል እንደ ጣዖት ስለ ተመለከ የሚል ይሆናል መልሱ፣ ምክንያቱም ይህ እኔ አካል እንደ ጣዖት አምላኪው ባህል፣ የተቀረው ማሕበራዊ ቅርጽ ያለው ሁሉ ለእኔ አካል መንበረ ጣዖት መሥዋዕት ያደርጋል። ለምሥጢረ ተክሊል እምቢ ማለት ቤተ ሰብ ማግለልና የተቀሩት የተለየ ዓይነት ዝምድናዎች ይሆን ማኅበራዊነትም ጭምር እንደ ሸከም እንዲታሰብ የሚያደርግ በመሆኑም ብቻህ መኖር የበለጠ ነው ወደ ሚለው ወደ ተሳሳተው ባህል ይዳርጋል፣ ይህ ዓይነቱ አመለካከትም የዓለማዊው ቀውስ ምክንያት ነው በማለት አስረድተዋል።
በመጨረሻም ከተለያዩ 70 አገሮች የተወጣጡ ከ 150 ሺሕ እስከ 200 ሺሕ የሚገመቱ ቤተሰቦች የቤተሰብ ሰብአዊ መብትና ፈቃድ ውሳኔ ዝክረ 30ኛው ዓመት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ መቃብር ለመሳለም መንፈሳዊ ንግደት እንደሚፈጽሙና ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል እንደሚቀበሉ ገልጠው፣ ቤተሰብ ችግር አልቦ ማለት ሳይሆን ችግር የሚያጋጥመው ቢሆንም ቅሉ ቤተሰብ ውበትና ጸጋ በመሆኑም ያለው ጥልቅ ደስታ ለመመስከር የሚያከናውኑት መንፈሳዊ ንግደት ነው ብለው፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም የቤተሰብ ጉዳይ ተንከባካቢው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ካሪታስ ለተሰየው የቅድስት መንበር የተራድኦ ማኅበር በኢጣሊያ ቅርጫፍ ጋር በመተባበር የመላ ዓለም ቤተሰብ ድጋፍ ለሶሪያ ቤተሰብ የተሰየመ የሰብአዊና የመፍንሳዊ ድጋፍ መርሃ ግብር መወጠኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.